settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የእግዚአብሔር ሉዓዊነትና የሰው ልጅ ነጻ ፍቃድ ለደኅንንት አብረው ይሠራሉ?

መልስ፤


በእግዚአብሔር ሉዓላዊነትና በሰዎች ነጻ ፍቃድና ኃላፊነት መካከል ያለውን ግንኙነት ሙሉ ለመረዳት ያስቸግረናል። እግዚአብሔር ብቻ ነው በእውነት የሚያውቀው፣ እነሱ አንድ ላይ ለእሱ የደኅንነት እቅድ መሥራታቸውን። ምናልባትም ከሌሎቹ አስተምህሮዎች ይልቅ ይሄ ጉዳይ፣ በእጅጉን ጠቃሚ የሚሆነው፣ የእግዚአብሔርን ባሕርይና ከእሱ ጋር ያለንን ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ መረዳት አለመቻላችንን ነው። በሁለቱም ጎኖች እስከ ጽንፍ መሄድ ስለ ደኅንነት የተዛባ መረዳት ያመጣል።

ቃሉ ግልጽ ነው፣ እግዚአብሔር ማን እንደሚድን ማወቁ (ሮሜ 8፡29፤ 1ኛ ጴጥሮስ 1፡2)። ኤፌሶን 1፡4 የሚነግረን እግዚአብሔር “ከዓለም ፍጥረት በፊት” እንደመረጠን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ የሚያስረዳው አማኞች እንደ “ተመረጡ” ነው፣ (ሮሜ 8፡33፤ 11፡5፤ ኤፌሶን 1፡11፤ ቆላስይስ 3፡12፤ 1ኛ ተሰሎንቄ 1፡4፤ 1ኛ ጴጥሮስ 1፡2፤ 2፡9) እና “የተመረጡት” (ማቴዎስ 24፡22፣ 31፤ ማርቆስ 13፡20፣ 27፤ ሮሜ 11፡7፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 5፡21፤ 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡10፤ ቲቶ 1፡1፤ 1ኛ ጴጥሮስ 1፡1)። አማኞች ቀድሞ የተወሰነላቸው የሆኑበት ሐቅ (ሮሜ 8፡29-30፡ ኤፌሶን 1፡5፣ 11)፣ እንዲሁም የተመረጡ (ሮሜ 9፡11፤ 11፡28፤ 2ኛ ጴጥሮስ 1፡10)፣ ደኅንነት ፍጹም ግልጽ መሆኑ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ እንደሚለው፣ እኛ ክርስቶስን እንደ አዳኝ የመቀበል ኃላፊነት አለብን— እኛ ማድረግ የሚጠበቅብን በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ነው፣ እናም እንድናለን (ዮሐንስ 3፡16፤ ሮሜ 10፡9-10)። እግዚአብሔር ማን እንደሚድን ያውቃል፣ እግዚአብሔር ማን እንደሚድን ይመርጣል፣ እኛም ለመዳን ክርስቶስን መምረጥ ይኖርብናል። እነዚህ ሦስት ሐቆች አንድ ላይ እንደሚሠሩ በውስን አዕምሮ ለመረዳት አዳጋች ነው (ሮሜ 11፡33-36)። የእኛ ኃላፊነት የሚሆነው ወንጌልን በመላው ዓለም ማሰራጨት ነው (ማቴዎስ 28፡18-20፤ ሐዋርያት ሥራ 1፡8)። ቀድሞ የማወቁን፣ መምረጡን፣ እና የቅድመ ግብ እውቀቱን ጉዳይ ለእግዚአብሔር ትተን እኛ ወንጌልን ለማዳረስ ታዛዥ መሆን አለብን።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የእግዚአብሔር ሉዓዊነትና የሰው ልጅ ነጻ ፍቃድ ለደኅንንት አብረው ይሠራሉ?
© Copyright Got Questions Ministries