settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ዘለዓለማዊ ሕይወት አለን?

መልስ፤


መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚያመራውን መንገድ በግልጽ ያሳያል። በመጀመሪያ በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት መሥራታችንን ማመን አለብን፤ “ምክንያቱም ሁሉም ኀጢአት ሠርተዋል፤ የእግዚአብሔርም ክብር ጐድሎአቸዋል” (ሮሜ ፫፥፳፫)። ሁላችንም እግዚአብሔርን የሚያሳዝን ሥራ ሠርተናል፤ ለዚህ ሥራችንም ቅጣት ይገባናል። ኀጢአታችን በዘለዓለማዊ እግዚአብሔር ላይ ስለሆነ ቅታችንም ዘለዓለማዊ መሆን አለበት። “የኀጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር ስጦታ ግን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ የዘለዓለም ሕይወት ነው” (ሮሜ ፮፥፳፫)።

ይሁን እንጂ ኀጢአት የሌለበት ኢየሱስ (፩ኛ ጴጥሮስ ፪፥፳፪)፣ ዘለዓለማዊ የእግዚአብሔር ልጅ ሰው ሆነ (ዮሐንስ ፩፥፩፣ ፲፬)፤ በሞቱም ቅጣታችንን ተቀበለልን። “ነግር ግን ገና ኀጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞተ፤ ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያሳያል” (ሮሜ ፭፥፰)። እየሱስ ክርስቶስ መስቀል ላይ ሞተ (ዮሐንስ ፲፱፥፴፩-፵፪)፣ ተገቢያችን የነበረውንም ቅጣት ተሸከመልን (፪ኛ ቆሮንቶስ ፭፥፳፩)። በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተነሣ (፩ኛ ቆሮንቶስ ፲፭፥፩-፬)፣ በኀጢአትና ሞትም ላይ ገዢነቱን አስመሰከረ። “የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ ይባረክ፤ እርሱ ከታላቅ ምሕረቱ የተነሣ በኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት መነሳት ምክንያት ለሕያው ተስፋ የሚሆን አዲስ ልደት” ሰጥቶናልና (፩ኛ ጴጥሮስ ፩፥፫)።

ለመዳን በእምነት ከኀጢአት መራቅና ወደ ክርስቶስ መጠጋት አለብን (የሐዋርያት ሥራ ፫፡፲፱)። እምነታችን በሱ ከሆነ፣ በመስቀል የሞተውንም ለኀጢአታችን ሲል እነደሆነ ከተቀበልን፣ ኀጢአታችን እንደሚሰረይልንና ዘለዓለማዊ ሕይወት በሰማይ እንነደምናገኝ ቃል ገብቶልናል። “በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፉ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና” (ዮሐንስ ፫፥፲፮)። “‘ኢየሱስ ጌታ ነው’ ብለህ በአፍህ ብትስክር፣ እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሳው በልብህ ብታምን፣ ትድናለህ” (ሮሜ ፲፥፱)። ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚወስደን እውነተኛው መንገድ ክርስቶስ በመስቀል በፈጸመው ሥራ ማመን ብቻ ነው! “በእምነት፣ በጸጋ ድናችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ በሥራ አይደለም” (ኤፌሶን ፪፥፰-፱)።

የእየሱስ ክርስቶስን አዳኝነት ለመቀበል ከፈለግን ይህ ቀላል ጸሎት በቂ ነው። ማስታወስ የሚኖርብን ግን ይሄም ሆነ ሌላ ጸሎት በራሱ ብቻ ሊያድነን አይችልም። በክርስቶስ ካመን ብቻ ነው ከኀጢአታችን መዳን የምንችለው። ጸሎቱ የሚረዳን በእግዚአብሔር ያለን እምነት ለመግለጽና ስላዳነንም ምስጋና ለማቅረብ ነው። “እግዚአብሔር ሆይ፤ ኀጢአተኛ እነደሆንኩና ቅጣት እነደሚገባኝ አወቃለሁ። ይሁን እንጂ እየሱስ ክርስቶስ ቅጣቴን እነደተቀበለልኝና በሱ ካመንኩም ይቅርታ እንደሚደረግልኝ አምናለሁ። ከኀጢአት በመራቅ እምነቴን በአዳኝነትህን አኖራለሁ። የዘለዓለማዊ ሕይወት ስጦታ ስለሰጠኸኝ፣ አስደናቂ ለሆነው ጸጋህንና ይቅር ባይነትህን ምስጋናየን አቀርባለሁ! አሜን!”

እዚህ ባነበብከው ምክንያት ለክርስቶስ ውሳኔ ላይ ደርሰሃል? እንዲያ ከሆነ፣ “ዛሬ ክርሰቶስን ተቀብያለሁ” የሚለውን ቁልፍ ተጫን

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ዘለዓለማዊ ሕይወት አለን?
© Copyright Got Questions Ministries