settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ሚስት ለባሏ መገዛት ይኖርባታልን?

መልስ፤


መገዛት በጋብቻ ግንኙነት ውስጥ ጠቃሚ ጉዳይ ነው። እዚህ ግልጽ የሆነ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትእዛዝ አለ፡ “ሚስቶች ሆይ፥ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤ ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና። ዳሩ ግን ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ እንዲሁ ሚስቶች ደግሞ በሁሉ ለባሎቻቸው ይገዙ” (ኤፌሶን 5፡22-24)።

ኃጢአት ወደ ዓለም ከመግባቱ በፊት እንኳ፣ የባል ራስነት መርሕ ነበር (1 ጢሞቴዎስ 2፡13)። አዳም በቅድሚያ ነው የተፈጠረው፣ ሔዋንም የተፈጠረችው የአዳም “ረዳት” እንድትሆን ነው (ዘፍጥረት 2፡18-20)። እግዚአብሔር በርካታ ሥልጣንን በዓለም ላይ መሥርቷል፡ መንግሥታት ፍትሕን በኅብረተሰቡ መካከል እንዲያረጋግጡና ጥበቃ እንዲያደርጉ፤ ፓስተሮች የእግዚአብሔርን በጎች እንዲመሩና እንዲመግቡ፤ ባሎች ሚስቶቻቸውን እንዲወዱና እንዲከባከቡ፤ አባቶችም ልጆቻቸውን እንዲገሥጹ። በሁሉም ጉዳይ፣ መገዛትን ይጠይቃል፡ ዜጋ ለመንግሥት፣ መንጋ ለእረኛው፣ ሚስት ለባል፣ ልጅ ለአባቱ።

“መገዛት”hupotasso፣ የሚለው የግሪክ ቃል ሲተረጎም ግሡ ቀጣይነት ያለው መልክ ነው። ይህ ማለት ለእግዚአብሔር፣ ለመንግሥት፣ ለፓስተር፣ ወይም ለባል መገዛት የአንድ ጊዜ ድርጊት አይደለም ማለት ነው። እሱ ቀጣይነት ያለው ጠባይ ነው፣ ይኸውም የባሕርይ ፈርጅ የሚሆን።

በቅድሚያ፣ ርግጥ፣ ለእግዚአብሔር የመገዛት ኃላፊነት አለብን፣ ይኸውም እሱን የምንታዘዝበት ብቸኛው መንገድ (ያዕቆብ 1፡21፤ 4፡7)። እንዲሁም እያንዳንዱ አማኝ ትሕትና የተሞላው፣ ለሌሎች ለመገዛት ዝግጁ የሆነ ሕይወት መኖር አለበት (ኤፌሶን 5፡21)። ለቤተሰብ ምድብ ስለመገዛት፣ 1 ቆሮንቶስ 11፡2-3 ይላል፣ ባል ለክርስቶስ መገዛት እንደሚኖርበት (ክርስቶስ ለእግዚአብሔር አብ እንዳደረገው) ሚስትም ለባሏ መገዛት ይኖርባታል።

ዛሬ በዓለማችን ብዙ የተዛባ መረዳት አለ፣ በጋብቻ ውስጥ የባልና ሚስትን ሚና በተመለከተ። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሚናዎች እንኳ በሚገባ ተረድተው ሳለ፣ በርካቶች እነርሱን መተዉን መርጠዋል፣ የሴቶችን “ነጻነት” መወገን በሚል እሳቤ፣ በውጤቱም የቤተሰብ አሀድ መለያየትን አስከትሏል። ዓለም የእግዚአብሔርን ዕቅድ ባይቀበል የሚያስደንቅ አይደለም፣ የእግዚአብሔር ሕዝብ ግን በደስታ ያንን ዕቅድ ማክበር አለበት።

መገዛት መጥፎ ቃል አይደለም። መገዛት የዝቅተኝነት ወይም አነስ ያለ ጠቀሜታ ነጸብራቅ አይደለም። ክርስቶስ በቋሚነት ለአብ ፍቃድ ራሱን አስገዝቷል (ሉቃስ 22፡42፤ ዮሐንስ 5፡30)፣ የራሱን ጠቀሜታ ምንም ሳያጓድል።

የዓለምን የተሳሳተ መረዳት ለመቋቋም፣ ሴት ለባሏ ስለመገዛቷ፣ የሚከተለውን ልብ ብለን ማስተዋል ይኖርብናል ኤፌሶን 5፡22-24፡ 1) ሚስት ለአንድ ሰው ራሷን ታስገዛ (ለባሏ)፣ ለወንድ ሁሉ ሳይሆን። የመገዛት ሕግ ሴት በኅብረተሰቡ የሚኖራት ቦታ ድረስ የሚራዘም አይደለም። 2) ሚስት በፍቃደኝነት ለባሏ መገዛት ይኖርባታል፣ ለኢየሱስ ክርስቶስ በግል መታዘዝ። እሷ ለባሏ ትገዛለች፣ ኢየሱስን ስለምትወደው። 3) ሚስት ለባሏ የመገዛቷ ምሳሌ ቤተ-ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምታደርገው ያለ ነው። 4) ስለ ሚስት ችሎታ፣ ተሰጥዖ፣ ወይም ጠቀሜታ ምንም የተባለ ነገር የለም፤ ለገዛ ባሏ የመገዛቷ ሐቅ፣ በምንም መልኩ ዝቅተኛ ወይም አነስተኛ ጠቀሜታ ያላት ነች የሚያስብል አይደለም። ደግሞም ለመገዛት ትእዛዙ ምንም አመላካች እንደሌለው፣ “በነገር ሁሉ” ከሚለው በቀር፣ ተገንዘብ። ስለዚህ፣ ባል ሚስቱ እስከምትገዛለት ድረስ አጠቃላይ ፈተና ወይም የብቃት ፈተናን ማለፍ አይጠበቅበትም። ምናልባት እሷ ከእሱ ይልቅ በብዙ መንገዶች የተሻለች የሆነችበት ሐቅ ሊኖር ይችላል፣ ነገር ግን እሷ የጌታን ትእዛዝ መከተልን ትመርጣለች፣ ለባሏ አመራር በመገዛት። ይህን በማድረግ፣ መልካም ሴት የማያምን ባሏን እንኳ ወደ ጌታ መማረክ ትችላለች፣ “ያለ ቃላት” በተቀደሰ ባሕርይዋ ብቻ (1 ጴጥሮስ 3፡1)።

መገዛት ተፈጥሯዊ ምላሽ መሆን አለበት፣ ለተወዳጅ አመራር። ባል የገዛ ሚስቱን ሲወድ፣ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደወደዳት (ኤፌሶን 5፡25—33)፣ መገዛትም ተፈጥሯዊ ምላሽ ይሆናል፣ ሚስት ለባልዋ። ነገር ግን፣ የባል ፍቅር ምንም ቢሆን ወይም ቢጎድል ሚስት እንድትገዛ ታዛለች፣ “ለጌታ እንደሚሆን” (ቁጥር 22)። ይህ ማለት ለእግዚአብሔር ታዛዥነቷ— የእርሱን ዕቅድ መቀበሏ— ለባልዋ እንድትገዛ ያደርጋታል። “ለጌታ እንደሚሆን” የሚለው ማወዳደሪያ ለሚስት የሚያስታውሰው ተጠያቂ የምትሆንበት ከፍ ያለ ሥልጣን መኖሩን ነው። ስለዚህ ምንም ግዴታ የለባትም የመንግሥትን ሕግ ወይም የእግዚአብሔርን ሕግ ላለመጠበቅ፣ ለባልዋ “በመገዛት” ስም። ራሷን ትክክል እና ሕጋዊ እና እግዚአብሔርን ለሚያከብሩ ነገሮች ታስገዛለች። ርግጥ አላግባብ ለሆኑ ነገሮች አትገዛም— ትክክል ወይም ሕጋዊ ላልሆኑ ወይም እግዚአብሔርን ለማያከብሩ። “የመገዛትን” መርሕ ለመጠቀም መሞከር፣ አላግባብ መጠቀምን ልክ ለማድረግ፣ ቅዱስ ቃሉን መጠምዘዝና ሰይጣንን ማስተዋወቅ ነው።

ኤፌሶን 5 ላይ ያለው የሚስት ለባልዋ መገዛት፣ ባል ግለኛ ወይም ገዥ እንዲሆን አይፈቅድም። የእርሱ ትዕዛዝ እንዲያፈቅር ነው (ቁጥር 25)፣ እሱም በእግዚአብሔር ፊት ኃላፊነት አለበት ትእዛዙን ለመፈጸም። ባል ሥልጣኑን በጥበብ፣ በልግስና፣ እና በእግዚአብሔር ፍርሃት፣ ለእርሱም ምላሽ ለሚሰጥበት መፈጸም ይኖርበታል።

ሚስት በባልዋ ስትወደድ፣ ቤተ-ክርስቲያን በክርስቶስ እንደ ተወደደች፣ መገዛት አስቸጋሪ አይሆንም። ኤፌሶን 5፡24 ይላል፣ “ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ፣ እንዲሁ ደግሞ ሚስቶች በነገር ሁሉ ለባሎቻቸው መገዛት አለባቸው።” በጋብቻ ላይ፣ መገዛት ክብርና አክብሮትን ለባል የመስጠት አቋም ነው (ኤፌሶን 5፡33) እንዲሁም እሱ ያቃተውን ማጠናቀቅ ነው። እሱም የእግዚአብሔር ዕቅድ ነው፣ ቤተሰብ እንዴት መሥራት እንደሚኖርበት።

ተንታኙ ማቴዎስ ሔንሪ ጽፏል፣ “ሴት የተፈጠረችው ከአዳም ጎን ነው። ከራሱ ላይ አልተሠራችም፣ በእርሱ ላይ ትገዛ ዘንድ፣ አልያም ከእግሩ፣ በእርሱ ትረገጥ ዘንድ፣ ነገር ግን ከጎኑ ነች፣ ከእርሱ እኩል ትሆን ዘንድ፣ ከክንዱ ሥር ሆና እንድትጠበቅ፣ ከልቡ አጠገብ ሆና እንድትወደድ።” አፌሶን 5፡19-33 ያለው ለባልና ሚስት የተሰጠው ትእዛዝ የወዲያውኑ ዐውደ-ጽሑፍ በመንፈስ መሞላትን ያካትታል። በመንፈስ የተሞሉ አማኞች በአምልኮት ውስጥ ያሉ ናቸው (5፡19)፣ በምስጋና የተሞሉ (5፡20)፣ እና ተገዥዎች (5፡21)። ጳውሎስ ይሄንን የአስተሳሰብ መስመር ተከትሏል፣ በመንፈስ ሞል የሆነ ሕይወት እና ለሚስቶች አውሎታል፣ ቁጥር 22-24 ላይ። ሚስት ለባልዋ መገዛት የሚኖርባት፣ ሴቶች ዝቅተኛ ስለሆኑ አይደለም (መጽሐፍ ቅዱስ ያንን ፈጽሞ አያስተምርም)፣ ነገር ግን እግዚአብሔር የጋብቻ ግንኙነት እንደዚያ እንዲሆን ስላደረገ ነው።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ሚስት ለባሏ መገዛት ይኖርባታልን?
© Copyright Got Questions Ministries