settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስን ለምን እናነባለን / ለምን እናጠናለን?

መልስ፤


መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ይኖርብናል፣ ምክንያቱም ለእኛ የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ በጥሬው “እግዚአብሔር የተነፈሰው” ነው፣ (2 ጢሞቴዎስ 3፡16)። በሌላ አነጋገር፣ ለእኛ የእግዚአብሔር ዓይነተኛ ቃል ነው። በርካታ ጥያቄዎች አሉ ፈላስፋዎች ያነሧቸው፣ እግዚአብሔርም በቃሉ በኩል መለሰልን። የሕይወት ዓላማው ምንድነው? ከየት ነው የመጣሁት? ከሞት በኋላ ሕይወት ይኖራልን? ወደ መንግሥተ-ሰማያት እንዴት ልገባ እችላለሁ? ምድር ለምን በክፉው ተሞላች? መልካሙን ለማድረግ ለምን እታገላለሁ? ከእነዚህ “ትልቅ” ጥያቄዎች በተጨማሪ፣ መጽሐፍ ቅዱስ በርካታ ተግባራዊ ምክር ይሰጣል፣ በእንዲህ ዓይነቶቹ አካባቢ ከተጓዳኜ ምንድነው የምሻው? ስኬታማ ትዳር እንዴት ሊኖረኝ ይችላል? እንዴት መልካም ጓደኛ ልሆን እችላለሁ? እንዴት መልካም ወላጅ ልሆን እችላለሁ? ስኬት ምንድነው እንዴትስ ላገኘው እችላለሁ? እንዴት ልለወጥ እችላለሁ? የሕይወት ዋና ነገሩ ምንድነው? በጸጸት ወደ ኋላ ሳልመለከት እንዴት መኖር እችላለሁ? በሕይወት ላይ የሚከሰቱትን ፍትሐዊ ያልሆኑ ሁነቶች እንዴት በድል አልፋቸዋለሁ?

መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብና ማጥናት ይኖርብናል ምክንያቱም እሱ ባጠቃላይ ርግጠኛና ያለ ስህተት ስለሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ የተለየ ነው፣ “ቅዱስ” ተብለው ከሚጠሩት መጻሕፍት መካከል፤ እናም እሱ እንዲያው የሞራል ትምህርት የሚሰጥና “እኔን እመኑ” የሚል አይደለም። ይልቁንም፣ እሱን እንድንፈትን ችሎታ አለን፣ እሱ ያሰፈራቸውን በመቶዎች የሚቆጠሩ ዝርዝር ትንቢቶችን በመመርመር፣ የመዘገባቸውን ታሪካዊ ሁኔታዎች በመመርመር፣ እንዲሁም እሱ ያዛመዳቸውን ሳይንሳዊ ሐቆች በመመርመር። መጽሐፍ ቅዱስ ስህተቶች አሉት የሚሉት፣ የራሳቸው ጆሮ ለእውነት ስለ ተደፈነ ነው። ኢየሱስ አንድ ጊዜ ጠይቆ ነበር፣ የትኛው ይቀላል፣ “ኃጢአትህ ተሰረየችልህ፣” ወይስ “ተነሣ፣ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ።” ከዚያም ኃጢአትን ይቅር ማለት አንደሚችል አረጋገጠ (አንድ ባይኖቻችን ልናየው የማንችለው ነገር) ሽባውን በመፈወስ (በዙሪያው ያሉት ባይኖቻቸው ሊያረጋግጡ የሚችሉት)። በተመሳሳይ፣ ለእኛ ዋስትና ተሰጥቶናል፣ ይኸውም የእግዚአብሔር ቃል እውነት መሆኑን፣ መንፈሳዊ አካባቢዎችን ሲያስረዳ፣ በስሜት ሕዋሳታችን ልንረዳው የማንችለውን፣ ራሱን በእውነት በማስቀመጥ በእነዚያ ስፍራዎች ልንረዳው እንችላለን፣ ለምሳሌ ታሪካዊ ርግጠኝነት፣ ሳይንሳዊ ርግጠኝነት፣ እና ትንቢታዊ ርግጠኝነት።

መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብና ማጥናት ይኖርብናል፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር ስለማይለወጥ እንዲሁም የሰው ልጅ ተፈጥሮ ስለማይለወጥ፤ እሱ ለእኛ ጠቃሚ ነው፣ ልክ እንደ ተጻፈበት ጊዜ ሁሉ። ቴክኖሎጂ ሲለዋወጥ፣ የሰው ልጅ ተፈጥሮና ፍላጎት አይለዋወጥም። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪክን እናገኛለን፣ ገጹቹን ማንበብ ስንጀምር፣ ያም ስለ አንድ ለአንድ ግንኙነትም ሆነ ከኅብረተሰቡ ስንነጋገር፣ “ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም” (መክብብ 1፡9)። የሰው ልጅ ባጠቃላይ ፍቅርና ርካታን በሁሉም የስህተት ስፍራዎች መፈለጉን አንደቀጠለ፣ እግዚአብሔር—መልካሙና ግርማ ያለው ፈጣሪያችን— የመጨረሻውን ደስታ እንደሚያመጣልን ይነግረናል። የተገለጠ ቃሉ፣ መጽሐፍ ቅዱስ፣ እጅግ ጠቃሚ ነው፣ ይኸውም ኢየሱስ ስለ እሱ ሲናገር፣ “ሰው በምግብ ብቻ አይኖርም፣ ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ” (ማቴዎስ 4፡4)። በሌላ አነጋገር፣ ሕይወትን በሙላት መኖር የምንሻ ከሆነ፣ እግዚአብሔር አንደፈቀደው፣ የእግዚአብሔርን የተጻፈ ቃል ልንሰማና ትኩረት ልንሰጥ ይገባል።

መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብና ማጥናት አለብን ምክንያቱም በርካታ የሐሰት ትምህርት በመኖሩ፡ መጽሐፍ ቅዱስ የመለኪያውን ዘንግ ይሰጠናል፣ እውነቱን ከስሕተት መለየት እንድንችልበት። እሱ፣ እግዚአብሔር ምን እንደሚመስል ይነግረናል። ስለ እግዚአብሔር የተሳሳተ ምስል ካለን እሱ ጣዖትን ወይም የሐሰት አማልክትን ማምለክ ነው። እሱ ያልሆነውን አንድ ነገር አያመለክን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በርግጠኝነት ወደ መንግሥተ-ሰማያት እንዴት እንደምንገባ ይነግረናል፣ እሱም መልካም በመሆን ወይም በመጠመቅ ወይም በሌላ በምናደርገው አይደለም (ዮሐንስ 14:6፤ ኤፌሶን 2:1-10፤ ኢሳይያስ 53:6፤ ሮሜ 3:10-18፣ 5:8፣ 6:23፣ 10:9-13)። በዚህ መስመር ላይ፣ የእግዚአብሔር ቃል የሚያሳየን እግዚአብሔር የቱን ያህል እንደሚወደን ነው (ሮሜ 5:6-8፤ ዮሐንስ 3:16)። እናም ይሄንን በመማር ነው በምላሹ እሱን ለመውደድ የምንሳበው (1 ዮሐንስ 4:19)።

መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔርን እንድናገለግል ያበቃናል (2 ጢሞቴዎስ 3:17፤ ኤፌሶን 6:17፤ ዕብራውያን 4:12)። ከኃጢአታችን እንዴት እንደምንድን እንድናውቅ ይረዳናል፣ የእሱንም የመጨረሻ መዘዝ (2 ጢሞቴዎስ 3:15)። በእግዚአብሔር ቃል ላይ ማተኮርና ትምህርቱንም ማክበር በሕይወት ስኬትን ያመጣል (ኢያሱ 1:8፤ ያዕቆብ 1:25)። የእግዚአብሔር ቃል በሕይወታችን ኃጢአትን እንድንመለከት ይረዳናል፣ እሱንም ለማውጣት እንድንችል (መዝሙር 119:9፣ 11)። እሱም ለሕይወታችን ምሪት ይሰጠናል፣ ከመምህሮቻችንም ይልቅ ጠቢብ እንድንሆን (መዝሙር 32:8፣ 119:99፤ ምሳሌ 1:6)። መጽሐፍ ቅዱስ የሕይወታችንን ዓመታት ዋጋ ለሌለው እንዳናባክን ይረዳናል፣ እሱም ማብቂያ የለውም (ማቴዎስ 7:24-27)።

መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብና ማጥናት ከማራኪ “ማጥመጃ” ያለፈ እንድናይ ይረዳናል፣ ወደ ጎጂ “መንጠቆ” በኃጢአታዊ ፈተናዎች፣ ስለዚህም ከሌሎች ስሕተት ልንማር እንችላለን፣ ራሳችን ከማድረግ ይልቅ። ልምድ ታላቅ መምህር ነው፣ ነገር ግን ከኃጢአት ወደ መማር ሲመጣ፣ እሱ አስፈሪ መጥፎ መምህር ነው። ከሌሎች ስህተት መማር እጅግ ይሻላል። የምንማርባቸው በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ገጸ-ባሕርያት አሉ፣ አንዳንዶቹ በአዎንታዊም ሆነ በአሉታዊ ሚና ሁነኛ ማሳያነት ያገለግላሉ፣ በሕይወታቸው የተለያየ ጊዜ። ለምሳሌ፣ ዳዊት፣ ጎልያድን ባሸነፈ ጊዜ የሚያስተምረን እግዚአብሔር ከማንም ነገር በላይ እንደሚበልጥ ነው፣ እንድንጋፈጠው ከሚጠይቀን (1 ሳሙኤል 17)፣ ከቤርሳቤህ ጋር ዝሙት እንዲፈጽም ለፈተና ሲሰጥ የሚያሳየው በኃጢአት የሚገኝ የጊዜው ደስታ የረጅም ጊዜ አስፈሪ ጣጣ እንዳለው ነው (2 ሳሙኤል 11)።

መጽሐፍ ቅዱስ ለንባብ ብቻ የሚሆን መጽሐፍ አይደለም። እሱ ለጥናት የሚሆን መጽሐፍ ነው፣ በተግባር ላይ ይውል ዘንድ። አለበለዚያ፣ እሱ ሳያላምጡ ምግብ እንደ መዋጥ ነው፣ እና ከዚያም እንደመትፋት— ምንም ዓይነት የምግብ ጠቀሜታ ሳይገኝበት። መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። እሱም እንደ ተፈጥሮ ሕጎች አሳሪ (አስገዳጅ) ነው። ላንፈልገው እንችላለን፣ ነገር ግን ያንን የምናደርገው በገዛ ራሳችን ውሳኔ ነው፣ ልክ የስበትን ሕግ ባንፈልገው እንደምንሆነው። እሱም እጅግ አብዝቶ ሊጋነን አይችልም፣ መጽሐፍ ቅዱስ የቱን ያህል ለሕይወታችን ጠቃሚ እንደሆነ። መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት የወርቅ ማዕድንን ከመቆፈር ጋር ሊነጻጸር ይችላል። ጥቂት ጥረት እንደነገሩ ካደረግን “በወንዝ ውስጥ በድንጋዩጋ ከተጓዝን፣” ጥቂት ብናኝ ወርቅ ብቻ እናገኛለን። ነገር ግን ወደ ውስጥ ጥልቀን በመቆፈር ጥረት ካደረግን፣ ለጥረታችን የተሻለ ሽልማት እናገኛለን።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስን ለምን እናነባለን / ለምን እናጠናለን?
© Copyright Got Questions Ministries