settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የድነት እቅድ ምነድነው?

መልስ፤


ተርበሃል? ምግብ ሳይሆን በሕይወትህ ውስጥ የላቀ ነገር ለማግኘት ተርበሃል? በውስጥህ እርካታን ማግኘት ያለቻልክበት ነገር አለ? እንዲያ ከሆነ መልሱ ኢየሱስ ነው! ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም፤ በእኔም የሚያምን ፈጽሞ አይጠማም” (ዮሐንስ ፮፥፴፭)።

ግራ ተጋብተሃል? በሕይወትህ ውስጥ መንገድም ሆነ ዓላማ አጥተሃል? ማብራት ያጠፉብህና ማብሪያ ማጥፊያው ያጣኸው ሆኖ ይሰማሃል? ኢየሱስ እንዲህ ሲል አወጀ፤ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝም የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ ከቶ በጨለማ አይመላለስም” (ዮሐንስ ፰፥፲፪)።

የሕይወት በር የተዘጋብህ ሆኖ ይሰማሃል? ብዙ በሮች ለመክፈት ሞክረህ ከኋላቸው የያዙት ነገር ትርጉም አልባ ሆኖ አግኝተኸዋል? የተሳካ ሕይወት ፍለጋ ላይ ነህ? እንዲያ ከሆነ መንገዱ ኢየሱስ ነው! ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል የሚገባ ሁሉ ይድናል፤ ይገባል፤ ይወጣል፤ መሰማሪያም ያገኛል” (ዮሐንስ ፲፥፱)።

ያመንካቸው ሰዎች በቦታው አይገኝልሁም? ግኑኝነትህ ባዶና ግልብ ሆኖ ይሰማሃል? ሁሉም ሊጠቀሙብህ የወሰኑ ሆኖ ይሰማሃል? እንዲያ ከሆነ መንገዱ ኢየሱስ ነው! ኢየሱስ እነዲህ አለ፤ “መልካም እረኛ አኔ ነኝ፤ መልካም እረኛ ሕይወቱን ስለበጎቹ አሳልፎ ይሰጣል…መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ በጎቼን አውቃለሁ፤ እነርሱም ያውቁኛል” (ዮሐንስ ፲፩፥፳፭-፳፮)።

ከዚህ ሕይወት በኋላ ምን እንዳለ ያሳስበሃል? ለሚዝጉና ለሚበስብሱ ነገሮች ብቻ መኖርህ አንገሽግሾሃል? አንዳንድ ጊዜ ሕይወት ትርጉም የሌለው ሆኖ ይሰማሃል? ከሞት በኋላ ሕይወት እንዲኖርህ ትሻለህ? እንዲያ ከሆነ መንገዱ ኢየሱስ ነው! ኢየሱስ እንዲህ ሲል አወጀ፤ “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚያምን ቢሞት እንኳ በሕይወት ይኖራል፤ በእኔ የሚኖር፣ የሚያምንብኝም ከቶ አይሞትም” (ዮሐንስ ፲፩፥፳፭-፳፮)።

መንገዱ የትኛው ነው? እውነትስ ምንድነው? ሕይወትስ? ኢየሱስም እንዲህ ሲል መልሰ፤ “መንገዱ እኔ ነኝ፤ እውነትና ሕይወትም እኔው ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም” (ዮሐንስ ፲፬፥፮)።

የሚሰማህ ረሐብ መንፈሳዊ ረሐብ ነውና በኢየሱስ ብቻ ነው ሊታገስልህ የሚችለው። ኢየሱስ ብቻ ነው ጨለማውን ሊገፍልህ የሚችለው። እርካታ ላለው ሕይወት ቁልፉ ኢየሱስ ነው። ስትፈልገው የነበረው ጓደኛና እረኛም ኢየሱስ ነው። በዚህም ሆነ በወድያኛው ዓለም ኢየሱስ ሕይወት ነው። ኢየሱስ የድነት መንገድ ነው!

ረሐብ የሚሰማህ፣ ጨለማ ላይ የምትመላለስበትና ለሕይወትህ ትርጉም ያጣህበት ምክንያት ከእግዚአብሔር ጋር በመለያየትህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ሁላችንም በኀጢአታችን ምክንያት ከእግዚአብሔር ጋር መለያየታችን ይነግረናል (መክብብ ፯፥፳፤ ሮሜ ፫፥፳፫)። በልብህ የሚሰማህ ባዶነት እግዚአብሔር በሕይወትህ ውስጥ ስለሌለ ነው። ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት እንዲኖረን ነው የተፈጠርነው። በኀጢአታችን ምክንያት ከዚህ ግንኙነት ርቀናል። ከዚህ የባሰ ደግሞ ኀጢአታችን ከእግዚአብሔር ጋር ለዘለዓለሙ እንድንለያይ ያደርገናል፣ በዚህኛውም በሆነ በወድያኛው ዓለም (ሮሜ ፮፥፳፫፤ ዮሐንስ ፫፥፴፮)።

ይህ ችግር እንዴት ሊፈታ ይችላል? መፍትሄው ኢየሱስ ነው! ኢየሱስ ኀጢአታችንን ተሸከመልን (፪ኛ ቆሮንቶስ ፭፥፳፩)። በኛ ምትክ ኢየሱስ ሞተልን (ሮሜ ፭፥፰)፣ ቅጣታችንንም ተቀበለልን። በሶስተኛውም ቀን ኀጢአትንና ሞትን ድል አድርጎ ኢየሱስ ከሙታን ተነሳ (ሮሜ ፮፥፬-፭)። ለምን ይህን ሁሉ አደረገ? ለዚህ ጥያቄ ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለስ ሰጠ፣ “ስለወዳጆቹ ሕይወቱን አሳልፎ ከመስጠት የሚበልጥ ፍቅር ማንም የለውም” (ዮሐንስ ፫፥፲፫)። ኢየሱስ የሞተልን እኛ ሕይወት እንድናገኝ ነው። ሞቱ ለኀጢአታችን የተከፈለ ዋጋ መሆኑ አወቀን እምነታችንን በኢየሱስ ካደረግን ኀጢአታችን ሁሉ ይታጠብልናል፣ ይቅርታም ይደረግልናል። ከዚያም መንፈሳዊ ረሃባችን ይታገስልናል። መብራትም ይበራልናል። ርካታ ለተሞላ ሕይወትም መንገድ ይሰጠናል። እውነተኛው ጓደኛችንና ጠባቂያችንም እናውቃለን። ከሞት በኋላ ሕይወት እንደሚኖረንም እንረዳለን፤ ይህም ሕየወት በትነሳኤ ለዘለዓለሙ ከኢየሱስ ጋር በሰማይ የሚኖረን ሕይወት ነው!

“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲኖረው እነጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና” (ዮሐንስ ፫፥፲፮)።

እዚህ ባነበብከው ምክንያት ለክርስቶስ ውሳኔ ላይ ደርሰሃል? እንዲያ ከሆነ፣ “ዛሬ ክርሰቶስን ተቀብያለሁ” የሚለውን ቁልፍ ተጫን

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የድነት እቅድ ምነድነው?
© Copyright Got Questions Ministries