settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጦርነት ምን ይላል?

መልስ፤


ብዙ ሰዎች በዘጽ 20፡13 ላይ ‹‹አትግደል›› ተብሎ የተጻፈውን በማንበብ ይሳሳታሉ፡፡ ይህን ቃል ስለ ጦርነት ሊጠቀሙበት ይፈልጋሉ፡፡ የሆነው ሆኖ ግን የዕብራይሰጡ ቃል በቀጥታ ሲተረጎም ‹‹ሆን ብሎ ሌላውን ሰው በጥላቻ ለመግደል ማሰብ እና መግደልን ነው›› እግዚአብሔር በመደጋገም እስራኤላዊያንን ከሌሎች ህዝቦች ጋር እንዲዋጉ ትዕዛዝን ሰጥቶአቸዋል፡፡ (1 ሳሙ 15:3; ኢያሱ 4:13). እግዚአብሔር የሞት ቅጣትን ለተለያዩ ጥፋቶች አዞአል (ዘጽ 21:12, 15; 22:19; ዘሌ 20:11). ስለዚህ እግዚአብሔር በሁሉም አቅጣጫ ሙሉ በሙሉ መግደልን አልተቃወመም የተቃወመው በግፍ መግደልን ወንጀልን ነው፡፡ መግደል መቼም ቢሆን መልካም ነገር ሊሆን አይችልም፤ ግን አንዳንድ ጊዜ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ በምድር ላይ ኃጢያት የሞላባቸው ህዝቦች ሞልተዋል (ሮሜ 3:10-18 ) ጦርነት ሊከሰት ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ኃጢያት የሞላባቸው ሰዎች ትልቅ ጥፋት በንጹሃን እንዳያደርሱ መከልከያው ብቸኛው መንገድ ጦርነት ብቻ ነው፡፡

ሌላው በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ እስራኤላዊያንን አዘዛቸው፤ ‹‹ ምድያማውያንን ተበቀል ከዚያም በኋላ ወደ ወገኖችህ ትከማቻለህ። (ዘዑ 31:2). በዘዳ 20:16-17 :- ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ ከሚሰጥህ ከእነዚህ አሕዛብ ከተሞች ምንም ነፍስ አታድንም›› እንዲሁም 1 ሳሙ 15:18:- እግዚአብሔርም፦ ሄደህ ኃጢአተኞቹን አማሌቃውያንን ፈጽመህ አጥፋቸው፥ እስኪጠፉም ድረስ ውጋቸው ብሎ በመንገድ ላከህ።›› በትክክል እግዚአብሔር ሁሉንም ጦርነቶች አይቃወምም፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ጋር ሁልጊዜም ሃሳቡ አንድ ነው (ዮሐ 10:30), እናም ጦርነት በብሉይ ኪዳን ያለ የእግዚአብሔር ብቻ የሆነ ሃሳብ ነው ልንል አንችልም፡፡ እግዚአብሔር አይለወጥም (ሚኪ 3:6; ያዕ 1:17)::

የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት በተለየ ሁኔታ የሚሆን የኃይል ተግባር ነው፡፡ ራዕ 19፡11-12 ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የሚደረገውን የመጨረሻ ጦርነት ይገልጻል፤ አሸናፊው የጦር መሪ ጦርነትን ፍርድን ‹‹በፍትህ›› ያደርጋል ቁ.11፡፡ በደም ቁ.13 እና በጭካኔ፡፡ ወፎቹ የሚቃወሙትን ሁሉ እርሱን የተቃወሙትን ስጋን ይበላሉ ቁ.17-18 ለጠላቶቹ ምንም ርህራሄ የለውም ሁሉንም ያሸንፋል ቁ20 ‹‹በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።›› አሳልፎ ይሰጣል፡፡

አግዚአብሔር ፈጽሞ ጦርነትን አይደግፍም ብሎ ማለት ስህተት ነው፡፡ ኢየሱስ ሰላም አስከባሪ አይደለም፡፡ በክፉ ሰዎች በተሞላ አለም አንዳንድ ጊዜ የባሰ ክፋት እንዳይሆን ጦርነት አስፈላጊ ነው፡፡ ሂትለር በሁተኛው የአለም ጦርነት ባይሞት ሌሎች ስንት ሚሊዩኖች ይገደሉ ነበር? የአሜሪካን ሲቪል ጦርነት ባይደረግ ምን ያህል ጥቁር አሜሪካውያን በባርነት ይሰቃዩ ነበር?

ጦርነት መጥፎ ነገር ነው፡፡ አንዳንድ ጦርነቶች ከሎሎቹ ይልቅ ‹‹ፍትህ›› አላቸው ነገር ግን ጦርነት ሁልጊዜም የኃጢያት ውጤት ነው፡፡ (ሮሜ 3:10-18) በተመሳሳይ ሁኔታ . መክ 3:8 ሲናገር ‹‹ለመውደድ ጊዜ አለው፥ ለመጥላትም ጊዜ አለው ለጦርነት ጊዜ አለው፥ ለሰላምም ጊዜ አለው። ኃጢያት ጥላቻ ክፋት በሞላበት አለም (ሮሜ 3:10-18) ጦርነት ሊከሰት የሚችል ነገር ነው፡፡ ክርስቲያኖች ጦርነትን መፈለግ አይኖርባቸውም እግዚአብሔር በስልጣን ላይ ያስቀመጠውን ባለስልጣንም መቃወም የለባቸውም (ሮሜ 13:1-4; 1ጴጥ 2:17):: በጦርነት ጊዜ ማድረግ የሚገባን አስፈላጊ ነገር እግዚአብሔር ለመሪዎቻችን የእርሱን ጥበብ እንዲሰጣቸው፤ የጦር ሰራዊቱ እንዲጠበቅ፤ አፋጣኝ መፍትሄ ልግጭቱ እንዲሰጥ፤ በጦርነቱ ውስጥ ለተጎዱ ልንጸልይ ይገባል (ፊሊ 4:6-7)::

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጦርነት ምን ይላል? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries