settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ዩንቨርሳሊዝም/ዩንቨርሳሊዝም ደኅንነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው?

መልስ፤


ዩንቨርሳሊዝም ሁለም ሰው ይድናል በሎ የሚያምን ትምህርት ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ የሁሉም ሰው መጨረሻ በሰማይ ነው ብለው የሚያምኑ የዩንቨርሳሊዝም ድኅነት አስተሳሰብ ያላቸው ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ መጽሐፍ ቅዱሳዊውን አስተሳሰብ እንዲቃወሙ የሚያደርጋቸው ምናልባት ወንዶችና ሴቶች በሲኦል ለዘልአለም በጥፋት እሳት ይኖራሉ የሚለው አስተሳሰብ ሊሆን ይችላል፡፡ ለአንዳንዶች ይህ የእግዚአብሔርን ጽድቅና ፍርድ ቸል በማለት ስለ እግዚአብሔር ፍቅርና ርኅራኄ የተሰጠ የተጋነነ ትኩረት ነው፤ እና ይህ ደግሞ ደግሞ እግዚአብሔር በሁሉም ህያው ነፍስ ባለው ሁሉ ላይ ምህረት ይኖረዋል ወደሚል እምነት ይወስዳቸዋል፡፡

በመጀመሪያ መጸሐፍ ቅዱስ በግልጥ ያልተዋጁ ሰዎች ለዘለአለም በሲኦል እንደሚኖሩ ይናገራል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ የራሱ ቃል እንደሚያረጋግጠው የተዋጁ ሰዎች በሰማይ የሚያሳልፉት ጊዜ ያልተዋጁ ሰዎች በሶኦል እንደሚያሳልፉት ጊዜ የሚረዝም ነው፡፡ ማቲ 25፡46 እንደሚለው፡- ‹‹እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።›› በዚህ ቃል መሰረት ያልዳኑ ሰዎች ቅጣት ልክ እንደ ጻድቃን ለዘለአለም ነው፡፡ አንዳዶች በሲኦል የሚኖሩ ቀስ በቀስ መኖር እንደሚያቆሙ ያምናሉ ግን ጌታ እራሱ እንደተናገረው ለዘለአለም የሚቆይ ነው፡፡ ማቲ 25፡41 እና ማር 9፡44 ሲኦልን ሲገልጸው ‹‹ዘላለማዊ እሳት›› እና ‹‹የማይጠፋ እሳት›› ይላል፡፡

ይህን የማይጠፋ እሳት አንድ ሰው እንዴት ሊያመልጥ ይቻላል? ብዙ ሰዎች ሁሉም መንገድ ሁሉም ኃይማኖት ወደ ሰማይ እንደሚወስድ ያምኖሉ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር በፍቅርና በምህረት የተሞላ ስለሆነ ሁለም ሰው ወደ ሰማይ እንዲገቡ እንደሚፈቅድ አድርገው ይቆጥራሉ፡፡ እግዚአብሔር በእርግጥም በፍቅርና በምህረት የተሞላ አምላክ ነው፤ ይህም ማንነቱ ነው ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ምድር እንዲልክልንና በመስቀል ላይ ለእኛ እንዲሞት ያደረገው፡፡ ሥራ 4፡12 ሲናገር ‹‹መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።›› ‹‹አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤›› 1ኛ ጢሞ 2፡5 በዩሐ 14፡6፡- ‹‹ ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።›› ዮሐ 3፡16፡- ‹‹በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።›› የእግዚአብሔርን ልጅ እንቢ ብንል ለደህንነት የሚያበቃንን አናገኝም፡፡ (ዮሐ 3፡16፤18፤36)

አንደነዚህ ያሉ ጥቅሶችን ስንመለከት ዩንቨርሳሊዝም አና የዩንቨርሳሊዝም ድኅነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ እምነት እንደሆነ ግልጽ ይሆንልናል፡፡ ዩንቨርሳሊዝም በቀጥታ መጸሐፍ ቅዱስ ከሚለው ጋር ይጋጫል፡፡ ብዙ ሰዎች ክርስቲያኖችን ትእግስት ያጡ ለብቻቸው የተለዩ አንደሆኑ አድርገው ይወቅሳሉ፤ እነዚህ ቃላቶች ግን የራሱ የክርስቶስ ኢየሱስ አንደሆኑ ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ ክርስቲያቲያኖች ይህን ሃሳብ በራሳቸው የፈጠሩት አይደለም፤ ክርስቲያኖች ጌታ የተናገረውን በቀጥታ እንዳለ ነው ያስቀመጡት፡፡ ሰዎች መልዕኩቱን መቃወም ይመርጣሉ ምክንያቱም ሃጢያታቸውን መቃወም መተው ስለማይፈልጉና እግዚአብሔር ደግሞ እንዲያድናቸው ስለሚፈልጉ ነው፡፡ እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ያዘጋጀውን ድኅነት የሚቃወሙ ይድናሉ ማለት የእግዚአብሔርን ቅድስና ፍርድ ማሳነስና ኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ፈንታ መሰዋቱን ቸል ማለት ነው፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ዩንቨርሳሊዝም/ዩንቨርሳሊዝም ደኅንነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው?
© Copyright Got Questions Ministries