settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ታላቁ መከራ ምንድነው? ታላቁ መከራ በሰባት ዓመታት ማብቃቱን እንዴት እናውቃለን?

መልስ፤


ታላቁ መከራ መጻዒው የሰባት ዓመት ጊዜ እግዚአብሔር እስራኤልን የሚቀጣበትና የማያምነውን ዓለም ፍርድ የሚያጠናቅቅበት ነው። ቤተ ክርስቲያን እሷም በጌታ ኢየሱስ አካልነትና ሥራ ባመኑ የተሠራች፣ ከኃጢአት ቅጣት ለመዳን፣ በታላቁ መከራ ጊዜ አይኖሩም። ቤተ ክርስቲያን ከምድር ትወሰዳለች፣ መነጠቅ ተብሎ በሚታወቀው ሁነት (1 ተሰሎንቄ 4:13-18፤ 1 ቆሮንቶስ 15:51-53)። ቤተ ክርስቲያን ከሚመጣው ቁጣ ትጠበቃለች (1 ተሰሎንቄ 5:9)። በቅዱስ ቃሉ ሁሉ ላይ፣ ታላቁ መከራ በሌሎች ስሞች ይጠቀሳል፣ ለአብነትም የጌታ ቀን (ኢሳይያስ 2:12፤ 13:6-9፤ ኢዩኤል 1:15፤ 2:1-31፤ 3:14፤ 1 ተሰሎንቄ 5:2)፤ መከራ ወይም ታላቁ መከራ (ዘዳግም 4:30፤ ሶፎንያስ 1:1)፤ ታላቁ መከራ፣ እሱም እጅግ የከፋውን የሰባቱን ዓመት ጊዜ ሁለተኛ አጋማሽ የሚያመለክት (ማቴዎስ 24:21)፤ የመከራ ጊዜ ወይም ቀን (ዳንኤል 12:1፤ ሶፎንያስ 1:15)፤ የያዕቆብ መከራ ጊዜ (ኤርምያስ 30:7)።

ዳንኤል 9፡24-27 መረዳት አስፈላጊ ነው፣ የመከራውን ዓላማና ጊዜ ለመረዳት። ይህ ምንባብ ስለ 70 ሳምንታት ይናገራል፣ እሱም “የአንተን ሕዝብ” በመቃወም በሚል የታወጀውን። የዳንኤል ሕዝብ አይሁድ ናቸው፣ የእስራኤል ሕዝብ፣ እናም ዳንኤል 9፡24 የሚናገረው ጊዜ እግዚአብሔር የሰጠው፣ “ዓመፃን ይጨርስ፥ ኃጢአትንም ይፈጽም፥ በደልንም ያስተሰርይ፥ የዘላለምን ጽድቅ ያገባ፥ ራእይንና ትንቢትን ያትም፥ ቅዱሰ ቅዱሳኑንም ይቀባ ዘንድ።” እግዚአብሔር “ሰባ ሱባዔ” ያወጀው እነዚህን ነገሮች ሁሉ ለመጨረስ ነው። ይህ የ70 ሰባቶች ዓመት ነው፣ ወይም 490 ዓመት። (አንዳንድ ትርጉሞች የሚያመለክቱት የዓመታትን 70 ሳምንታት ነው።) ይህ በሌለኛው የዚህ ምንባብ ክፍል ተረጋግጧል፣ በዳንኤል ላይ። ቁጥር 25 እና 26፣ ዳንኤል የተነገረው መሲሕ እንደሚገደል ነው፣ ከ“ከሰባት ሰባቶች እና እና ስልሳ ሁለት ሰባቶች” በኋላ፣ (69 ባጠቃላይ)፣ ኢየሩሳሌምን ዳግም ለመገንባት አዋጅ ከወጣ በኋላ። በሌላ አገላለጽ፣ የዓመታቱ 69 ሰባቶች (483 ዓመታት) ኢየሩሳሌምን ዳግም ለመገንባት አዋጅ ከወጣ በኋላ፣ መሲሕ ይታረዳል። የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ጸሐፊዎች እንዳረጋገጡት 483 ዓመታት አልፈዋል ኢየሩሳሌምን ዳግም ለመገንባት ካለው ጊዜና ኢየሱስ እስከ ተሰቀለበት። ብዙዎች ክርስቲያን ሊቃውንት፣ በፍጻሜ ዘመን አተያያቸው (መጻዒ ነገሮች/ ሁነቶች)፣ ከላይ የተመለከተው መረዳት ነው ያላቸው፣ በዳንኤል 70 ሰባቶች ላይ።

483 ዓመታት እንዳለፉ፣ ኢየሩሳሌምን ዳግም ለመገንባት ከወጣው አዋጅና እስከ መሲሕ ሞት ድረስ፣ ይህ የአንድ ሰባት ዓመት ጊዜ ይተዋል፣ በዳንኤል 9፡24 መሠረት ለመፈጸም፡ “ዓመፃን ይጨርስ፥ ኃጢአትንም ይፈጽም፥ በደልንም ያስተሰርይ፥ የዘላለምን ጽድቅ ያገባ፥ ራእይንና ትንቢትን ያትም፥ ቅዱሰ ቅዱሳኑንም ይቀባ ዘንድ።” ይህ የመጨረሻው የሰባት ዓመት ጊዜ የታላቁ መከራ ጊዜ በመባል ይታወቃል— እሱም እግዚአብሔር እስራኤልን በኃጢአቱ ምክንያት መቅጣቱን የሚጨርስበት ነው።

ዳንኤል 9፡27 መጠነኛ ማብራሪያ ይሰጣል፣ ስለ ሰባቱ ዓመት የመከራ ጊዜ፡ “እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል በርኵሰትም ጫፍ ላይ አጥፊው ይመጣል እስከ ተቈረጠውም ፍጻሜ ድረስ መቅሠፍት በአጥፊው ላይ ይፈስሳል።” ይህ ቁጥር የሚናገርበት ሰው፣ ኢየሱስ “የጥፋት ርኵሰት የሚያመጣ” ያለው ነው (ማቴዎስ 24፡15) እናም “አውሬው” ተብሎ ይጠራል፣ ራዕይ 13 ላይ። ዳንኤል 9፡27 የሚለው አውሬው ለሰባት ዓመታት ቃል ኪዳን ያደርጋል ነው፣ ግን በዚህ ሳምንት መካከል (3 ½ ዓመት ወደ መከራው)፣ ቃል ኪዳኑን ያፈርሳል፣ መሥዋዕቱን በማስቀረት። ራዕይ 13 የሚያስረዳው አውሬው የራሱን ምስል በመቅደስ እንደሚያስቀርጽ ነው፣ መላው ዓለምም እንዲሰግድለት ይጠይቃል። ራዕይ 13፡5 የሚለው ይህ ለ42 ወራት እንደሚቀጥል ነው፣ እሱም 3 ½ ዓመት። ዳንኤል 9፡27 የሚለው ይህ የሚሆነው በሳምንት መካከል ነው፣ ራዕይ 13፡5 የሚለውም አውሬው ይሄንን ለ42 ወራት እንደሚያደርግ ነው፣ አጠቃላይ የጊዜው ርዝመት 84 ወራት ወይም ሰባት ዓመት መሆኑን በቀላሉ መመልከት ይቻላል። ዳንኤል 7፡25ን ደግሞ ተመልከቱ፣ “እስከ ዘመንና ዘመናት እስከ እኩሌታ ዘመን” (ዘመን=1 ዓመት፤ ዘመናት=ሁለት ዓመት፤ የዘመን እኩሌታ=½ ዓመት፤ ባጠቃላይ 3 ½ ዓመት) ደግሞም “ታላቁ መከራ”ን ተመልከቱ፣ የሰባቱ ዓመት የመከራ ዘመን የመጨረሻው አጋማሽ፣ አውሬው ሥልጣን ላይ ሲሆን።

ለታላቁ መከራ ተጨማሪ ማጣቀሻ፣ ራዕይ 11፡2-3፣ እሱም ስለ 1260 ቀናት እና 42 ወራት፣ እና ዳንኤል 12፡11-12፣ እሱም 1290 ቀናት እና 1335 ቀናት የሚናገረው። እነዚህ ቀናት የታላቁን መከራ ማዕከላዊ ነጥብ ያመላክታሉ። በዳንኤል 12 ላይ ተጨማሪዎቹ ቀናት ምናልባት የሕዝቦችን ፍርድ ፍጻሜ አካቶ ይሆናል (ማቴዎስ 25፡31-46) እና የክርስቶስን የሺ ዓመት ንግሥና መቼት (ራዕይ 20፡4-6)።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ታላቁ መከራ ምንድነው? ታላቁ መከራ በሰባት ዓመታት ማብቃቱን እንዴት እናውቃለን?
© Copyright Got Questions Ministries