settings icon
share icon
ጥያቄ፤

እግዚአብሔር ለምን መልካሙንና ክፉውን የምታስታውቀውን ዛፍ በኤደን ገነት አስቀመጠ?

መልስ፤


እግዚአብሔር መልካሙንና ክፉውን የምታስታውቀውን ዛፍ በኤደን ገነት ያስቀመጠው እግዚአብሔር ለአዳምና ለሔዋን እርሱን የመታዘዝን ወይም ያለመታዘዝን ምርጫ ሊሰጣቸው ነው፡፡ አዳምና ሔዋን መልካሙንና ክፈውን የምትለየውን ዛፍ ከመብላት ውጪ የፈለጉትን እንዱያደርጉ ነጻነት ነበራቸው፡፡ ዘፍ 2፡16-17፣ ‹‹እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።›› እግዚአብሔር አዳምና ሔዋንን ምርጫን ባይሰጣቸው እንዱሰሩ የተፈለገውን ብቻ ለማድረግ እንደተዘጋጁ ሮቦቶች ይሆኑ ነበር፡፡ እግዚአብሔር አዳምና ሔዋንን ውሳኔዎችን መወሰን እንዲችሉ በመልካሙን በክፉው መካከል መምረጥ እንዱችሉ ‹‹ነጻ›› የሆኑ ፍጡራን አድርጎ ነው የፈጠራቸው፡፡ አዳምና ሔዋን በእውነት ነጻነት ያላቸው እንዲሆኑ የግድ ምርጫ እንዲኖራቸው ያስፈልግ ነበር፡፡

በመሰረቱ ዛፉ ወይንም የዛፉ ፍሬ ፍሬው ምንም ክፋት አልነበረበትም፡፡ ፍሬው በራሱ በውስጡ ምንም አይነት ተጨማሪ እውቀት ሊሰጣቸው የሚችል አልነበረም፡፡ ፍሬው ቫይታሚን ሲ ወይንም ፋይበር ሊኖረው ይችላል መንፈሳዊ ምግብነት ግን አልነበረውም፡፡ ሆኖም ባለመታዘዝ የሄዱት እርምጃ መንፈሳዊ ጉዳት ነበረው፡፡ ያ ኃጢያት አይናቸውን ለክፋት ከፈተው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ክፉ ምን እንደሆነ አወቁ፤ ሃፍረት ተሰማቸው፤ ከእግዚአብሔርም መደበቅ ፈለጉ፡፡ ያለመታዘዝ ኃጢያታቸው ወድቀትን ወደ ህይወታቸው ብሎም ወደ አለም አመጣ፡፡ ለአዳምና ለሔዋን እግዚአብሔርን በመቃወም ባለመታዝ ፍሬውን መብላት ያስገኘላቸው ክፉውን እንዲሆም ራቁትነታቸውን ማወቅ ነው፡፡(ዘፍ 3:6–7).

እግዚአብሔር አዳምና ሔዋን ኃጢያተኛ እንዲሆኑ አይፈልግም ነበር፡፡ እግዚአብሔር የኃጢያት ውጤቱ ምን እነደሚሆን አስቀድሞ ያውቅ ነበር፡፡ እግዚአብሔር አዳምና ሔዋን ኃጢያትን እንደሚያደርጉና ክፉ እንደሚመጣ ቅጣት ሞትም ወደ አለም እንደሚመጣ አስቀድሞ ያውቅ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ሰይጣን እንዲፈትናቸው በምርጫቸው በሰይጣን እንዲገፋፉ ፈቀደ፡፡ አዳምና ሔዋን በራሳቸው ነጻ ፈቃድ እግዚአብሔርን ባለመታዘዝ የተከለከሉትን ፍሬ መብላትን መረጡ፡፡ በውጤቱም ክፉት፤ ኃጢያት፤ መከራ፤ በሽታና ሞት ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በዓለም ሁሉ ሆነ፡፡ የአዳምና የሔዋን ወሳኔ እያንዳንዱ ሰው ሲወለድ በፍጥረቱ ኃጢያተኛ እንዲሆንና ለኃጢያት ዝንባሌ እንዲኖረው አደረገ፡፡ የአዳምና የሔዋን ውሳኔ በመጨረሻ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሞትልን በመስቀል ላይ ደሙን ስለእኛ እንዲያፈስ አደረገው፡፡ በክርስቶስ በማመን ኃጢያት ከሚያስከትለው ውጤት እንዱሁም ፈጽመን ከኃጢያት ነጻ መሆን እንችላለን፡፡ ጳውሎስ በሮሜ 7፡24-25 የሚለውን አብረን ማለት ማሰተጋባት እንችላለን ‹‹እኔ ምንኛ ጎስቋላ ሰው ነኝ! ለዚህ ሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ያድነኛል? በኢየሱስ ክርስቶስ በጌታችን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።››

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

እግዚአብሔር ለምን መልካሙንና ክፉውን የምታስታውቀውን ዛፍ በኤደን ገነት አስቀመጠ?
© Copyright Got Questions Ministries