settings icon
share icon
ጥያቄ፤

በልሳናት መናገር መንፈስ ቅዱስ እንዳለን ማስረጃ ነውን?

መልስ፤


ሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ላይ ሦስት አጋጣሚዎች ይገኛሉ፣ በልሳናት መናገር መንፈስ ቅዱስን ከመቀበል ጋር የተጎዳኙበት— ሐዋ. 2:4፣ 10:44-46፣ እና 19፡6። ሆኖም፣ እነዚህ ሦስት አጋጣሚዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ብቸኛ ስፍራዎች ናቸው፣ በልሳን መናገር መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ማስረጃ ስለመሆኑ። በመላው የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በኢየሱስ አምነው በልሳን ስለመናገራቸው ምንም የተባለ የለም (ሐዋ. 2:41፣ 8:5-25፣ 16:31-34፣ 21:20)። በአዲስ ኪዳን የትም ስፍራ በልሳን መናገር ግለሰቡ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበሉ ብቸኛው ማስረጃ እንደሆነ አስተምህሮት (ትምህርት) የለም። በርግጥ፣ አዲስ ኪዳን ተቃራኒውን ነው የሚያስተምረው። የተነገረን፣ እያንዳንዱ በክርስቶስ አማኝ መንፈስ ቅዱስ እንዳለው ነው (ሮሜ 8:9፤ 1 ቆሮንቶስ 12:13፤ኤፌሶን 1:13-14)፣ ነገር ግን እያንዳንዱ አማኝ በልሳን አይናገርም (1 ቆሮንቶስ 12:29-31)።

ስለዚህ፣ በልሳን መናገር በእነዚህ ሦስት ምንባቦች ላይ የመንፈስ ቅዱስ ማስረጃ ለምን ሆነ? ሐዋ. 2 እንዳሰፈረው ሐዋርያት በመንፈስ ቅዱስ ተጠምቀው እና በእርሱ ኃይል ተሞልተዋል፣ ወንጌልን ለማወጅ። ሐዋርያት በሌሎች ቋንቋዎች (ልሳናት) መናገር እንዲችሉ ተደርገዋል፣ ሰዎች በገዛ ቋንቋቸው እውነትን መካፈል እንዲችሉ። ሐዋ. 10 እንደመዘገበው ሐዋርያው ጴጥሮስ እውነትን ይካፈል ዘንድ አይሁድ ወደ አልሆኑ ሰዎች ተልኳል። ጴጥሮስና ሌሎቹ የጥንት ክርስቲያኖች፣ አይሁድ የሆኑ፣ አሕዛብን (አይሁድ ያልሆኑ ሰዎችን) በቤተ-ክርስቲያን ለመቀበል አስቸጋሪ ጊዜ አሳልፈዋል። እግዚአብሔር አሕዛብን አስችሏቸዋል፣ በልሳን ይናገሩ ዘንድ፣ ሐዋርያት የተቀበሉትን ያንኑ መንፈስ ቅዱስ እንደተቀበሉ ለማሳየት (ሐዋ. 10፡47፣ 11፡17)።

ሐዋ. 10፡44-47 ይህን ይገልጻል፡ “ጴጥሮስ ይህን ነገር ገና ሲናገር ቃሉን በሰሙት ሁሉ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወረደ። ከጴጥሮስም ጋር የመጡት ሁሉ ከተገረዙት ወገን የሆኑ ምዕመናን በአሕዛብ ላይ ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ስለ ፈሰሰ ተገረሙ፤ በልሳኖች ሲናገሩ እግዚአብሔርንም ሲያከብሩ ሰምተዋቸዋልና።በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መልሶ፦ እነዚህ እንደ እኛ ደግሞ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ እንዳይጠመቁ ውኃን ይከለክላቸው ዘንድ የሚችል ማን ነው? አለ።” ጴጥሮስ ኋላ ላይ በዚህ ገጠመኝ እንደጠቀሰው፣ እግዚአብሔር በርግጥ አሕዛብንም እንዳዳነ ማስረጃ ነው (ሐዋ. 15፡7-11)።

በልሳን መናገር ክርስቲያኖች ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኛቸው ሲቀበሉ እና ስለዚህ በመንፈስ ቅዱስ ሲጠመቁ ተስፋ የሚያደርጉት ነገር እንደሆነ የትም ስፍራ አልቀረበም። በርግጥ፣ በአዲስ ኪዳን በሁሉም የመለወጥ መግለጫዎች ላይ ሁለት ብቻ ናቸው፣ በዛ ዐውደ-ጽሑፍ ተመዝግበው የሚገኙት። ልሳናት ተአምራዊ ስጦታ ነበር፣ የተለየ ዓላማ ያለው፣ በተወሰነ ጊዜ። እሱ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ብቸኛው ማስረጃ አልነበረም፣ ፈጽሞም ሆኖ አያውቅም።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

በልሳናት መናገር መንፈስ ቅዱስ እንዳለን ማስረጃ ነውን?
© Copyright Got Questions Ministries