settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ክርስቲያን በሌሎች እምነቶችና እና ኃይማኖቶች መቻቻል አለበት?

መልስ፤


በእኛ ዘመን ‹‹መቻቻል›› የሞራል ንጽጽርን የሚያስተዋውቀው እንደ ከፍተኛው ባህሪ ነው? እያንዳንዱ ፍልስፍና ሃሳብ እና የእምነት ስርዓት እኩል ዋጋ አላቸው እኩል ክብር ይገባቸዋል ይላል አንጻራዊነት /relativist/፡፡ አንድን የእምነት ስርዓት ከሌላው በላይ የሚቀበሉ ወይንም ከዛ ሲብስ ፍጹም የሆነ አውነት እውቀት የሚቀበሉ ጠባብ አስተሳሰብ ያላቸው ያልበራላቸው የሌላውን ሃሳብ የማይቀበሉ ናቸው ይላሉ፡፡

ትክክል ነው የተለያዩ ኃይማኖቶች ለየብቻቸው ተለይተው እያስተጋቡ ይሄዳሉ አንጻራዊነት /relativist/ በአይምሮ አስተሳሰባቸው ገጭቶችን ግልጽ ሊያደርጉ ሊያስማሙ አይችሉም፡፡ ለምሳሌ፡- መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል ‹‹ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው፥›› (ዕብ 9፡27) እንደገና ስጋ መልበስን ምስራቃዊ ኃይማኖቶች ቢያስተምሩም፤ አንድ ጊዜ ነው የምንሞተወ ወይንስ ብዙ ጊዜ; ሁለቱም ትምህርቶች አንድ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ አንጻራዊነት /relativist/ በመሰረቱ እውነትን እንደገና ይተረጉማሉ ተጻራሪ ቃላት ብዙ የሚጋጩ ‹‹እውነቶች›› አብረው መኖር የሚችሉበትን ለመፍጠር፡፡

ኢየሱስ እንዲህ አለ ‹‹ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።›› (ዮሐ 14፡6) ክርስቲያኖች እውነትን ተቀበሉ እንደ ሃሳብ አይደለም እንደ አካል፡፡ ይህ እወነትን ማሳወቅ በዚህ ጊዜ ክፍት አይምሮ “open-mindedness” ከሚባለው ክርስቲያኖችን ያርቃል፡፡ ክርስትያኖች የኢየሱስ ክርስቶስን ከሙታን መነሳት በአደባባይ እውቅና ይሰጣሉ፡፡ (ሮሜ 10፡9-10) በትንሳኤ የሚያምን ከሆነ የማያምኑ ሰዎች ኢየሱስ ዳግም እንዳልተነሳ ሲከራኩ እንዴት ነው የክፍት አይምሮ ባለቤት ሊሆን ይችላል? ለአንድ ክርስቲያን ግልጽ የሆነውን የእግዚአብሔር ቃል አስተምህሮ መካድ እግዚአብሔርን መካድ ነው፡፡

እናስታውስ ስለ እምነት ቀደም ብለን ምሳሌ ስንሰጥ መሰረት ጥለናል፤ አንዳንድ ነገሮች (እንደ ክርስቶስ አካላዊ ትንሳኤ ያሉ) ለድርድር የማይቀርቡ ናቸው፡፡ ሌሎች ነገሮች ለክርክር ክፍት ሊሆኑ ይችላሉ ለምሳሌ የዕብራዊያንን መጽሐፍ የጻፈው ምን ነው; ወይንም የጳውሎስን የስጋ መከራ ምንነት /መውጊያ/ ከማያስፈልግ የክርክር አረንቋ ቀዳሚ ባልሆኑ ጉዳዮች መግባትን ማስወገድ አለብን፡፡ (2 ጢሞ 2:23; ቲቶ 3:9).

የክርክር ቃለ ምልልስ ዋና አስፈላጊ በሆኑ አስተምህሮዎች እንኳ ቢሆን ክርስቲያን በጥብቅ ጥንቃቄ በአክብሮት መድረግን መለማመድ አለበት፡፡ በአቋም መለያየት አንድ ነገር ነው፤ ያን ሰው ማንኳሰስ ግን ፈጽሞ የተለየ ነው፡፡ እውነቱን ፈልገው ጥያቄን ለሚጠይቁ ርኅራኄን ለማሳየት እወነትን ለመያዝ መፍጠን አለብን፡፡ እንደ ኢየሱስ በጸጋና በእውነት መሞላት አለብን (ዮሐ 1፡14). ጴጥሮስ መልሱን ስለመያዝ እና ትሁት ስለመሆን ሚዛናዊ ነገር አስቀምጦአል ‹‹ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።›› (1 ጴጥ 3:15)፡፡

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ክርስቲያን በሌሎች እምነቶችና እና ኃይማኖቶች መቻቻል አለበት?
© Copyright Got Questions Ministries