settings icon
share icon
ጥያቄ፤

እግዚአብሔር ኢየሱስን ሲልከው ለምን ላከው? ከዛ በፊት ለምን አላከውም? ከዛ በኋላስ ለምን አልሆነም?

መልስ፤


‹‹ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤›› (ገላ 4፡4)፡፡ ይህ ጥቅስ እግዚአብሔር አባት ለጁን ጊዜው ሲደርስ እንደላከው ይነግረናል፡፡ በዙ ነገሮች በመጀሪያው ክፍለ ዘመን ሆነዋል ቢያንስ በሰዋዊ ምክንያት ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት ተቀባይነት ያለው ጊዜ ነው፡፡

1) በዚያን ጊዜ መሲህ እንደሚመጣ በአይሁድ ዘንድ ትልቅ መጠባበቅ ነበር፡፡ የሮማዊያን እስራኤልን መግዛት አይሁዶች የኢየሱስን መምጣት እንዲናፍቁት አደረጋቸው፡፡

2) ሮማዊያን አብዛኛውን የአለም ግዛት በአንድ በስራቸው አድርገው ነበር፤ ለብዙ ምድር የአንድነት ትርጉምን ይሰጣቸው ነበር፡፡ እንዲሁም በአንጻራዊነት ግዛቱ ሰላማዊ ነበር፤ በጓጓዝ ይቻል ነበር፤ የመጀሪያዎቹ ክርስቲያኖች ወንጌል ለማሰራጨት ጠቅሞአቸዋል፡፡ እንደዘህ ያለ የመጓጓዝ ነጸነት ከዚያ በፊት በነበረው ዘመን አልነበረም፡፡

3) ሮማዊያን በውትድርናው ሲያሸንፉ ግሪኮች በባህል አሸንፈው ነበር፡፡ የተለመደ የግሪክ ቋንቋ( ከመሰረታዊው የግሪክ ቋንቋ የሚለይ) የንግድ ቋንቋ ነበር በግዛቱ ሁሉ ይነገር ነበር ወንጌልን ለተለያዩ ህዝቦች በአንድ በተለመደ ቋንቋ ማስተላለፍ ተችሎ ነበር፡፡

4) በዙ የውሸት አማልክቶች ከሮማዊያን ሊያድኑአቸው ስላልቻሉ በዙዎች እነዚያን አማልክቶች ማምለክ ትተው ነበር፡፡ በተመሳሳይ ጊዜ በዙ ባህል ያለባቸው ከተሞች የግሪክ ፍልስፍና እና የወቅቱ ሳይንስ ሌሎችን በመንፈሳዊነት ባዶ አስቀርተዋቸዋል በተመሳሳይ መንገድ የኮምኒስት ክህደት መንግስታትን ዛሬ መበንፈስ ባዶ እንዳደረጋቸው፡፡

5) የጊዜው ሚስጥራዊ ሃይማኖት አዳኝ አማልክት ላይ የሚያተኩረው እና አምላኪዎቹን የደም መስዋእት የሚጠይቀው ይሄ የክርስቶስን ወንጌል አንድ ጊዜ የሚጨረሻ መስዋእት የቀረበበት መሆኑ በእነርሱ ዘንድ የሚታመን ያደርገዋል፡፡ ግሪኮች በነፍ ኢሟችነት ያመናሉ (በስጋ ግል አይደለም)፡፡

6) ከክፍለ ሃገር የሆኑት የሮማዊያን ሰራዊት ቅጥረኛ ወታደሮች እነዚህ ሰዎች ለሮማ ባህል እና አስተሳሰብ አስተዋወቁ (ለመሳሌ ወንጌልን) በረቀት ያሉ ያሉ ክፍለሃገሮችን ሊደረስ ያልቻሉትን፡፡ በብሪታንያ ቀደም ያለው የወንጌል መግቢያ መንገድ በዚያ ስፍራ የነበሩ ወታደሮች አማካኝነት ነው፡፡

ከላይ የምንመለከተው አረፍተ ነገር ሰዎች ያን ጊዜ በሚያዩበት ጊዜ የሚኖራቸው እይታ ላይ የተመሰረተ ነው፤ ለምን ያ ጊዜ ኢየሱስ ለመምጣቱ የተመረጠ ጊዜ እንደሆነ ሰዎች ያስቀመጡት ግምት ነው፡፡ እናውቃለን የእግዚአብሔር መንገድ የእኛ መንገድ አይደለም (ኢሳ 55፡8)፤ ይህንን ጊዜ ልጁን ለመላክ የመረጠበት ምክንያት ሊሆንም ላይሆንም ይችላል፡፡ የገላቲያ ምዕራፍ 3እና 4 አውድ ስንመለከት እግዚአብሔር በአይሁድ ህግ ላይ ለመሲሁ መምጣት መሰረት እንደጣለ ምስክር ነው፡፡ ህጉ ለሰዎች የኃጢያታቸው ጥልቀት ምን ያህል እንደሆነ ያሳያቸዋል (በዛ መንገድ ህጉን መጠበቅ አልቻሉም ነበር) ስለዚህም ፈውሱን ከመሲሁ ለመቀበል የበለጠ ተዘጋጅተው ሊሆን ይችላል (ገላ 3፡22-23፤ ሮሜ 3፡19-20)፡፡ ወደ መሲሁ ለመመራት ህጉ ራሱ ይፈርድባቸው ነበር (ገላ 3፡24)፡፡ ይህንን ለመሲሁ በተነገሩ በብዙ ትንቢቶቹ በኩል በኢየሱስ ፈጽሞታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ይህ የመስዋዕት ስርአት ስለ ኃጢያት የመስዋእቱን አስፈላጊነት የሚጠቁመው ይሁን እንጂ ደግሞ በቂ ሊሆን የማይችለው ነው (የትኛው መስዋዕት ሌላ ጊዜ ሌላ ተጨማሪ ይፈልጋል)፡፡ የብሉይ ኪዳን ታሪክ የኢየሱስ ክርስቶስን ማንነት እና ስራ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርአቶች በአሎች እና ድርጊቶች ስለው ያሳዩናል (እነደ አብርሃም ይስሐቅን ለመሰዋት ያሳየው ፈቃደኝነት፤ ወይም የማለፍ በአል ከግብጽ ሲወጡ የተደረጉ ዝርዝር ነገሮች፤ የመሳሰሉት)፡፡

በመጨረሻ ክርስቶስ የመጣው የተነገረው ትንቢት በሚፈጽምበት ጊዜ ነው፡፡ ዳን 9፡24-27 ‹‹ሰባ ሳምንት›› ወይንም ስለሰባዎቹ ‹‹ሰባቶች›› ይናገራል፡፡ ከአውዱ እነዚህ ‹‹ሳምንቶች›› ወይንም ‹‹ሰባቶች›› ሰባት አመታትን ያመለክታሉ ሰባት ቀናትን አይደለም፡፡ ታሪክን ልንፈትሽ እና መስመር ዝርዝር የመጀሪያዎቹ ስልሳ ዘጠኝ ሳምንቶች ልናስቀምጥ እንችላለን (ሰባ ሳምንቶች የሚፈጸሙት በመጪው ጊዜ ነው)፡፡ የሰባዎቹ ሳምንታት የኋልዮስ ቆጠራ የሚጀምረው ‹‹ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ›› (ቁ. 25)፡፡ ይህ ትእዛ በአርጤክሰስ ሎንጊማኑስ በ445 ከክርስቶስ ልደት በፊት ነው የተሰጠው፡፡ (ነህ 2፡25) ተመልከቱ፡፡፡ ከሰባት ‹‹ሰባቶች›› በኋላ 62 ‹‹ሰባቶች›› ሲደመር ወይም 69 ×7 አመት ትንቢቱ ሲያስቀምጥልን ‹‹ከስድሳ ሁለት ጊዜ ሰባትም በኋላ መሢሕ ይገደላል፥ በእርሱም ዘንድ ምንም የለም የሚመጣውም አለቃ ሕዝብ ከተማይቱንና መቅደሱን ያጠፋሉ ‹‹ ፍጻሜውም በጐርፍ ይሆናል፥›› (ማለትም ታላቅ ጥፋት ይሆናል) እስከ መጨረሻም ድረስ ጦርነት ይሆናል ጥፋትም ተቀጥሮአል።›› ቁ. 26፡፡ እዚህ ጋር ምንም ስህተት የሌለበት የአዳኑኙን የመስቀል ሞት መጠቀስ እንችላለን፡፡ ከአመታት በፊት በመጽሐፉ ሰር ሮበርት አንደርሰን ዘ ካሚንግ ፕሪንስ በተባለው መጽሐፉ ‹‹The Coming Prince, Sir Robert Anderson›› ስላሳ ዘጠኙን ሳመንታት አስመልክቶ ዝርዝ መረጃ ሰጥቶአል፤ ትንቢታዊ ቀናቶችን ተጠቅሞ፤ አመታቶችን ለመዝለል በመፍቀድ፤ በቀን መቁጠሪያ ስህተት፤ ከክርስቶስ ልደት በፊት ወደ ኤ ዲ በመቀየር የመሳሰሉትን እና ስልሳ ዘጠኝ ሳምንት ኢየሱስ ክርስቶስ በድል ወደ ኢየሩሳሌም መጊቢያ ከመሞቱ አምስት ቀን እንዲያልቅ አስቀመጠ፡፡ አንድ ሰው ይህን የገዜ ቀመር በጠቀምም ባይጠቀምም ነጥቡ ኢየሱስ ስጋ የለበሰበት ጊዜ የሚያርፈው በዳንኤል በዝርዝር ከአምስት መቶ አመት በፊት እንደተነገረው ትንቢት ነው፡፡

የኢሱስ ስጋን የመልበስ ጊዜ ሰዎች ለእርሱ መምጣት በተዘጋጁበት ጊዜ ነበር፡፡ በየዘመኑ ያሉ ሰዎች .. ኢየሱስ በትንቢት የተነገረለት መሲህ እንደሆነ ከበቂ በላይ መረጃ አላቸው የእርሱ ቃሉን መፈጸም ስለመምጣቱ የተነገሩ ትንቢቶቹን በግልጽ ያስቀምጣቸዋል፡፡

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

እግዚአብሔር ኢየሱስን ሲልከው ለምን ላከው? ከዛ በፊት ለምን አላከውም? ከዛ በኋላስ ለምን አልሆነም? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries