settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ኢየሱስ የተሰቀለው ዓርብ ነውን? ከሆነስ፣ በመቃብር ውስጥ ሦስት ቀናትን እንዴት ያሳልፋል፣ እሑድ እስከ ተነሣ ድረስ?

መልስ፤


መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ በየትኛው የሳምንቱ ቀናት እንደተሰቀለ በዝርዝር (ቁልጭ ባለ መልኩ) አያስቀምጥም። ሁለቱ በስፋት የሚታወቁት አስተያየቶች ዓርብና ረቡዕ ናቸው። አንዳንዶች፣ ሆኖም፣ ሁለቱንም ዓርብና ረቡዕን አዳብሎ (አቀናጅቶ) በመውሰድ ዕለቱ ኀሙስ ነው ብለው ይከራከራሉ።

ኢየሱስ በማቴዎስ 12፡40 እንዳለው፣ “ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።” ስቅለቱ ዓርብ እንደሆነ የሚከራከሩ፣ እንደሚሉት ተቀባይነት ያለው መንገድ አሁንም ቢሆን ይኖራል፣ ሦስት ቀን በመቃብር ይሆን ዘንድ። በአንደኛው ክፍለ ዘመን የአይሁድ አስተሳሰብ የቀን እኩሌታ እንደ ሙሉ ቀን ይወሰዳል። ኢየሱስ የዓርብ እኩሌታን በመቃብር ከሆነ፣ ቅዳሜ ሙሉ ቀን፣ እንዲሁም የእሑድ እኩሌታ — እናም እሱ በመቃብር ውስጥ ለሦስት ቀናት መኖሩን ግምት ውስጥ መውሰድ ይቻላል። አንደኛው ዋነኛ የዓርብ መከራከርያ የሚገኘው ማርቆስ 15፡42 ሲሆን፣ እሱም የሚያመለክተው ኢየሱስ የተሰቀለው “ከሰንበት በፊት መሆኑን ነው።” ያ የሳምንቱ ሰንበት ከሆነ፣ ማለትም ቅዳሜ፣ እናም ያ ሐቅ ወደ ዓርብ ስቅለት ያመራል። ሌለኛው የዓርብ ክርክር የሚለው እንደ ማቴዎስ 16፡21እና ሉቃስ 9፡22 የመሳሰሉት ቁጥሮች የሚያስተምሩት ኢየሱስ በሦስተኛው ቀን እንደሚነሣ ነው፤ ስለሆነም፣ ሙሉውን ሦስት ሌሊትና ቀናት የግድ በመቃብር ውስጥ መቆየት አያስፈልገውም። ነገር ግን አንዳንድ ትርጉሞች “በሦስተኛው ቀንን” ይጠቀማሉ፣ ለእነዚህ ቁጥሮች፣ ሁሉም ግን አያደርጉም፣ እናም ሁሉም “በሦስተኛው ቀን” በሚለው አይስማማም፣ እነዚህን ቁጥሮች በተሻለ ለመተርጎም። ከዚህም በላይ፣ ማርቆስ 8፡31 ኢየሱስ ከሦስት ቀናት “በኋላ” ይነሣል ይላል።

የኀሙስ ክርክር የሚያያዘው ከዓርብ እይታ ጋር ሆኖ፣ የሚከራከረውም ባብዛኛው በወቅቱ በርካታ ሁነቶች ነበሩ (አንዳንዶቹ እስከ ሃያ ያደርሱታል) ሁነቶቹም ከክርስቶስ መቀበር እና እሑድ ጠዋት ሆነው የተፈጠሩትም ከዓርብ ምሽት እስከ እሑድ ጠዋት ይደርሳሉ። የኀሙስ ተከራካሪዎች አስተሳሰባቸው የሚያመለክተው ዋነኛው ችግር በዓርብና በእሑድ መሐል የሚገኘው ብቸኛ ሙሉ ቀን ቅዳሜ መሆኑን ነው፣ የአይሁድ ሰንበት። አንድ ተጨማሪ ቀን ወይም ሁለት ነው፣ ይህን ችግር ሊያቃልል የሚችለው። የኀሙስ ተከራካሪዎች ይሄን ምክንያት ሊያቀርቡ ይችላሉ፡ ጓደኛህን እስከ ሰኞ ምሽት አላየኸውም እንበል። በቀጣዩ ጊዜ የተመለከትከው ኀሙስ ጠዋት ነው፣ እናም አንተ የምትለው፣ “እነዚህን ሦስት ቀናት አላየውህም” ብለህ ነው፣ ምንም እንኳ ባቆጣጠር 60 ሰዓታት (2.5 ቀናት) ብቻ ቢሆንም። ኢየሱስ ኀሙስ ከተሰቀለ፣ ይህ ምሳሌ እንዴት ሦስት ቀናት እንደሆነው ያሳያል።

የረቡዕ አስተያየት መሠረት የሚያደርገው በዛ ሳምንት ሁለት ሰንበታት መኖራቸውን ነው። ከመጀመሪያው በኋላ (በስቅለቱ ምሽት ከሆነው [ማርቆስ 15፡42፤ ሉቃስ 23፡52-54])፣ ሴቶቹ ሽቶውን ገዙ— እነሱ ግብይት የሚያደርጉት ከሰንበት በኋላ መሆኑን ተገንዘብ (ማርቆስ 16፡1)። የረቡዕ አስተሳሰብ የሚነሣው ይህ “ሰንበት” ፋሲካ እንደሆነ ነው (ሌዋውያን 16፡29-31፣ 23፡24-32፣ 39፣ ታላቅ የክብረ በዓል ቀናት የግድ የሳምንቱ ሰባተኛ ቀን ያልሆኑ ሰንበት ተብለው ተጠቅሰውልናል)። ሁለተኛው የዛ ሳምንት ሰንበት መደበኛው ሳምንታዊ ሰንበት ነው። በሉቃስ 23፡56 ያለውን ተመልከት፣ ሽቶውን የገዙት ሴቶች፣ ከመጀመሪያው ሰንበት በኋላ ተመልሰው ሽቶውን አሰናዱት፣ ከዚያም “በሰንበት ዐረፉ” (ሉቃስ 23፡56)። ክርክሩ መሠረት የሚያደርገው እነሱ ከሰንበት በኋላ ሽቶውን መግዛት እንደማይችሉ ነው፣ እናም ሽቶውን ከሰንበት በፊት ያዘጋጃሉ— አለበለዚያ ሁለት ሰንበታት እስካልሆኑ ድረስ። በሁለት ሰንበት እይታ፣ ክርስቶስ ኀሙስ ከተሰቀለ፣ እናም ታላቁ ቅዱስ ሰንበት (ፋሲካ) ኀሙስ ይጀምራል ማለት ነው ፀሐይ ስትጠልቅ አንሥቶ ዓርብ ፀሐይ ስትጠልቅ ያበቃል— በሳምንታዊው ሰንበት ወይም ቅዳሜ መጀመሪያ ላይ። ከመጀመሪያው ሰንበት የሽቶ ግዥው ቢፈጸም (ፋሲካ) በቅዳሜ ገዝተውታል ማለት ይሆናል፣ በዚህም ሰንበትን ይሽራሉ።

ስለሆነም፣ እንደ ረቡዕ አተያይ ከሆነ፣ ብቸኛው መጽሐፍ ቅዱስን የማይጣረሰው፣ የሴቶቹንና የሽቶውን በተመለከተ በጥሬው በማቴዎስ 12፡40 ላይ የሰፈረው፣ ክርስቶስ ረቡዕ ተሰቅሏል ማለት ነው። ታላቁ ቅዱስ ሰንበት ቀን (ፋሲካ) ኀሙስ ሆኗል ማለት ነው፣ ሴቶቹ ሽቶውን ገዝተው (ከዚያ በኋላ) በዓርብ እንዲሁም ተመልሰው ሽቶውን ያሰናዳሉ በዚያው ቀን፣ እነሱም ቅዳሜ ያርፋሉ በሳምንቱ ሰንበት፣ ከዚያም ሽቶውን ይዘው እሑድ በማለዳ ወደ መቃብር መጥተዋል። ኢየሱስ የተቀበረው ረቡዕ ፀሐይ ስትጠልቅ አካባቢ ነው፣ እሱም እንደ አይሁድ የቀን አቆጣጠር ኀሙስ የሚጀምርበት ነው። የአይሁድን የቀን አቆጣጠር በመያዝ፣ ኀሙስ ምሽት ይኖራችኋል (አንደኛ ምሽት)፣ ኀሙስ ቀን (አንደኛ ቀን)፣ ዓርብ ምሽት (ሁለተኛ ምሽት)፣ ዓርብ ቀን (ሁለተኛ ቀን)፣ ቅዳሜ ምሽት (ሦስተኛ ምሽት)፣ ቅዳሜ ቀን (ሦስተኛ ቀን)። መቼ እንደ ተነሣ በትክክል አናውቀውም፣ ነገር ግን እሑድ ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት እንደሆነ እናውቃለን (ዮሐንስ 20፡1፣ መግደላዊት ማርያም “ገና ጨለማ ሳለ” መጣች)፣ ስለዚህ ሊነሣ የሚችለው ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ቅዳሜ ሌሊት ነው፣ እሱም ለአይሁድ የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን።

በረቡዕ እይታ ላይ ሊኖር የሚችለው ችግር ከኢየሱስ ጋር በኢማኦስ መንገድ ከኢየሱስ ጋር የተጓዙት ደቀ መዛሙርት በተመሳሳይ መልኩ “በዛኑ ቀን” በእሱ ትንሣኤ መሆኑ ነው (ሉቃስ 24፡13)። ደቀ መዛሙርት፣ ኢየሱስን ስላላወቁት፣ ስለ ኢየሱስ ስቅለት ነገሩት (24፡21) እንዲህ በማለት “ይህም ነገር ከሆነ እነዚህ ሦስተኛ ቀናት ናቸው” (24፡22)። ከረቡዕ እስከ እሑድ አራት ቀናት ነው። ሊሆን የሚችለው ቆጠራውን የጀመሩት ከረቡዕ ምሽት ከኢየሱስ ቀብር፣ ከአይሁድ ኀሙስ ጀምሮ ነው፣ ለኀሙስ እስከ እሑድ ሲቆጠር ሦስት ቀን ይሆናል።

ከነገሮች የክብደት ደረጃ አኳያ፣ ኢየሱስ ከሳምንቱ በየትኛው ቀን እንደተሰቀለ ማወቁ አስፈላጊ ላይሆን ይችላል። በጣም አስፈላጊ ቢሆን ኖሮ፣ የእግዚአብሔር ቃል የቀንና የጊዜውን ሂደት በግልጽ ባስቀመጠው ነበር። ጠቃሚ የሚሆነው የእሱ በሥጋ መሞት ነው ፣ እንዲሁም በአካል ከሙታን መነሣቱ። በተመሳሳይ መልኩ ጠቃሚ የሚሆነው የሞተበት ምክንያት ነው— ሁሉም ኃጢአተኞች ይገባቸው የነበረውን ቅጣት መውሰድ ነው። ዮሐንስ 3፡16 እና 3፡36 ሁለቱም የሚገልጹት በእሱ ላይ እምነትን ማኖር ውጤቱ የዘላለም ሕይወት ነው! ይህ እንግዲህ እሱ ረቡዕም፣ ኀሙስም፣ ወይም ዓርብ ቢሰቀል ያው ነው።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ኢየሱስ የተሰቀለው ዓርብ ነውን? ከሆነስ፣ በመቃብር ውስጥ ሦስት ቀናትን እንዴት ያሳልፋል፣ እሑድ እስከ ተነሣ ድረስ?
© Copyright Got Questions Ministries