settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ስልታዊ ሥነ-መለኮት ምንድነው?

መልስ፤


“ስልታዊ” የሚያመለክተው አንድን በሥርዓታዊ አሠራር ውስጥ ያለ ነገርን ነው። ስለዚህ፣ ሥልታዊ ሥነ-መለኮት፣ ወደ ተለያዩ ሥርዓቶች የሥነ-መለኮት ምድብ ሲሆን፣ የተለያዩ አካባቢዎቹን ይተነትናል። ለምሳሌ፣ በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት ስለ መላእክት መረጃ ይሰጣሉ። ማናቸውም አንድ መጽሐፍ ስለ መላእክት ሁሉንም መረጃ አይሰጥም። ስልታዊ ሥነ-መለኮት ስለ መላእክት ሁሉንም መረጃ ከሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት ላይ ይወስድና ሥነ-መላእክት ወደሚባል ሥርዓት ያደራጃል። ስልታዊ ሥነ-መለኮት ማለት ይህ ነው— የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርቶች ወደ ምድባዊ ሥርዓቶች ማደራጀት።

ፍጹም ሥነ-መለኮት ወይም ፓቴሮሎጂ የእግዚአብሔር አብ ጥናት ነው። ክርስቶሎጂ የእግዚአብሔር ወልድ ጥናት ነው፣ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ። ፌኑማቶሎጂ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጥናት ነው። ባይብሎሎጂ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ነው። ሶቲሪኦሎጂ የደኅንነት ጥናት ነው። ኢከለሲኦሎጂ የቤተ-ክርስቲያን ጥናት ነው። ኢስካቶሎጂ የፍጻሜ ዘመን ጥናት ነው። ኤንጅሎሎጂ የመላእክት ጥናት ነው። የክርስቲያን አጋንንት የአጋንንት ጥናት ነው፣ ከክርስቲያን አተያይ አኳያ። ክርስቲያን አንትሮፖሎጂ የሰብዓዊነት ጥናት ነው፣ ከክርስቲያን አተያይ አኳያ። ሀማርቲዎሎጂ የኃጢአት ጥናት ነው። ስልታዊ ሥነ-መለኮት ጠቃሚ መሣርያ ነው፣ መጽሐፍ ቅዱስን በተደራጀ መልኩ ለመገንዘብና ለማስተማር የሚረዳን።

ከስልታዊ ሥነ-መለኮት በተጨማሪ፣ ሥነ-መለኮት የሚከፋፈልባቸው ሌሎች መንገዶች አሉ። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥነ-መለኮት የተወሰነ የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ (ወይም መጻሕፍት) ማጥናትና ለሚያተኩርበት የተለያየ የሥነ-መለኮት ገጽታ አጽንዖት መስጠት ነው። ለምሳሌ፣ የዮሐንስ ወንጌል እጅግ ክርስቶሎጂካዊ ነው፣ በክርስቶስ መለኮትነት ላይ እጅግ ከማተኮሩ የተነሣ (ዮሐንስ 1:1, 14; 8:58; 10:30; 20:28)። ታሪካዊ ሥነ-መለኮት የዶክትሪኖችና እነርሱም በክርስቲያን ቤተ-ክርስቲያን በዘመናት እንዴት እየጎለበሱ እንደመጡ የሚያጠና ነው። ቀኖናዊ ሥነ-መለኮት የተወሰኑ የክርስቲያን ቡድኖች፣ ስልታዊ ዶክትሪን ያላቸውን ዶክትሪን ማጥናት ነው— ለምሳሌ፣ ካልቪኒስታዊ ሥነ-መለኮት እና ነጻ የሆነ ሥነ-መለኮት። ዘመነኛ ሥነ-መለኮት እየዳበረ የመጣ ወይም በቅርብ ጊዜ ትኩረት ያገኘ ዶክትሪን ጥናት ነው። ምንም ዓይነት የሥነ-መለኮት ዘዴ ቢጠናም፣ ጠቃሚው ነገር የሥነ-መለኮት መጠናት ነው።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ስልታዊ ሥነ-መለኮት ምንድነው?
© Copyright Got Questions Ministries