settings icon
share icon
ጥያቄ፤

እግዚአብሔር መንፈሳዊ ስጦታዎችን እንዴት ያድላል? እግዚአብሔር የለመንኩትን መንፈሳዊ ስጦታ ይሰጠኛልን?

መልስ፤


ሮሜ 12፡3-8 እና 1 ቆሮንቶስ ምዕራፍ 12 ግልጽ አድርገውታል፣ ማለትም እያንዳንዱ ክርስቲያን መንፈሳዊ ስጦታዎች እንደተሰጠው፣ በጌታ ምርጫ መሠረት። መንፈሳዊ ስጦታዎች የሚሰጡት የክርስቶስን አካል ለማነጽ ነው (1 ቆሮንቶስ 12:7 14:12)። እነዚህ ስጦታዎች የሚሰጡበት ጊዜ ተለይቶ አልተጠቀሰም። አብዛኞች የሚያስቡት፣ መንፈሳዊ ስጦታዎች የሚሰጡት በመንፈሳዊ ልደት ጊዜ ነው (በመዳን ጊዜ)። ሆኖም፣ አንዳንድ ቁጥሮችም ይገኛሉ፣ እግዚአብሔር መንፈሳዊ ስጦታዎችን ኋላ ላይ እንደሚሰጥ የሚያመለክቱ። ሁለቱም 1 ጢሞቴዎስ 4፡14 እና 2 ጢሞቴዎስ 1፡6 ስለ ስጦታ የሚያመለክቱት፣ ጢሞቴዎስ የተቀበለው ለአገልግሎት በተለየ ጊዜ ነው፣ “በትንቢት።”ይህም ባመዛኙ የሚያመለክተው በጢሞቴዎስ ለአገልግሎት መለየት ጊዜ ከሽማግሌዎቹ አንዱ ስለ መንፈሳዊ ስጦታ መናገሩ፣ ጢሞቴዎስ ቀጣይ አገልግሎቱን ማከናወን እንዲችል ነው።

ደግሞም በ1 ቆሮንቶስ 12:28-31 እና በ1 ቆሮንቶስ 14:12-13 እንደተነገረን እግዚአብሔር ነው (እኛ ሳንሆን) ስጦታዎቹን የሚመርጠው። እነዚህ ምንባቦች ደግሞ እያንዳንዱ ሁሉ የተለየ ስጦታ እንደማይኖረው ያመለክታሉ። ጳውሎስ ለቆሮንቶስ አማኞች ይነግራቸዋል፣ መንፈሳዊ ስጦታዎችን የሚሹ ወይም የሚፈልጉ ከሆነ፣ እጅግ የሚያንጹትን በብርቱ መፈለግ ይኖርባቸዋል፣ እንደ ትንቢት መናገር ያለ (የእግዚአብሔርን ቃል በግልጽ መናገር፣ ሌሎችን ለማነጽ)። እንግዲህ፣ ጳውሎስ ለምን “ትልልቁን” ስጦታዎች በብርቱ ፈልጉ እያለ ይነግራቸዋል፣ እነርሱ ቀደም ብለው ሊሰጣቸው የሚገባቸው ሁሉ ተሰጥቷቸው ሳለ፣ እናም እነዚህን ታላላቅ ስጦታዎች የማግኘት ተጨማሪ ዕድል የለም ማለት ነውን? ይህም አንዱን ወደ ማመን ይመራዋል፣ ሰሎሞን ከእግዚአብሔር ጥበብን እንደለመነ፣ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መልካም መሪ እንዲሆን፣ እንዲሁም እግዚአብሔር የሚያስፈልጉንን እነዚህን ስጦታዎች ሊሰጠን ይችላል፣ ለእርሱ ቤተ-ክርስቲያን የተሻለ ጠቀሜታ እንዲሆን።

ይሄም ከተባለ በኋላ፣ አሁንም ቢሆን እነዚህ ስጦታዎች የሚሰጡት በእግዚአብሔር ምርጫ መሆኑ የማይቀር ነው፣ በእኛ በራሳችን ሳይሆን። እያንዳንዱ ቆሮንቶሳዊ የተለየ ስጦታ አጥብቆ የሚፈልግ ከሆነ፣ ማለትም እንደ ትንቢት መናገር ያለ፣ እግዚአብሔር እያንዳንዱ በጥብቅ በመፈለጉ ብቻ አይሰጠውም። እንደዚያ ቢያደርግ፣ እንግዲያውስ በሌሎቹ ተግባሮች ላይ ማን ሊያገለግል ይችላል፣ በክርስቶስ አካል?

አንድ ነገር አለ፣ በተገቢው መልኩ ግልጽ የሆነ — የእግዚአብሔር ትዕዛዝ እግዚአብሔር የሚያስችለው ነው። እግዚአብሔር አንድ ነገር እንድናደርግ ካዘዘን (ማለትም፣ ምስክርነት፣ የማይወደዱትን መውደድ፣ አሕዛብን ደቀ-መዝሙር ማድረግ፣ ወዘተ ያሉት)፣ እሱም ይሄንን እንድናደርግ ያስችለናል። አንዳንዶች በወንጌላዊነት እንደ ሌሎቹ ስጦታ ላይኖራቸው ይችላል፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ክርስቲያኖችን ሁሉ አዟል፣ እንዲመሰክሩና ደቀ-መዝሙር እንዲያደርጉ (ማቴዎስ 28:18-20፤ ሐዋ. 1:8)። እኛ ሁላችን ወንጌልን ለመስበክ ተጠርተናል፣ የወንጌላዊነት መንፈሳዊ ስጦታ ባይኖረን እንኳ። ቁርጠኛ የሆነ ክርስቲያን ቃሉን ለመማር መሻት ያለው እና የማስተማር ችሎታውን ለማጎልበት የሚጥር የተሻለ መምህር ሊሆን ይችላል፣ የማስተማር ጸጋ ኖሮት ስጦታውን ችላ ከሚለው ይልቅ።

መንፈሳዊ ስጦታዎቹ ለእኛ የሚሰጡን ክርስቶስን ስንቀበል ነውን፣ ወይስ እነርሱ እየጎለበቱ/እየዳበሩ የሚሄዱት ከእግዚአብሔር ጋር በምናደርገው ጕዞ ነውን? መልሱ ሁለቱም ነው። በአብዛኛው፣ መንፈሳዊ ስጦታዎች የሚሰጡት በደኅንነት ጊዜ ነው፣ ነገር ግን ደግሞ በመንፈሳዊ ዕድገት መዳበር ይኖርባቸዋል። በልባችሁ የሚኖረው መሻት ወደ መንፈሳዊ ስጦታችሁ እያመራ ይጎለብታልን? እናንተ የተወሰኑ መንፈሳዊ ስጦታዎችን መፈለግ ትችላላችሁን? አንደኛ ቆሮንቶስ 12፡31 ይህ እንደሚቻል የሚጠቁም ይመስላል። “ከሁሉ የተሻለውን የጸጋ ስጦታ በብርቱ ፈልጉ።” እናንተ መንፈሳዊ ስጦታን ከእግዚአብሔር መለመን ትችላላችሁ፣ እናም ከእርሱ ኋላ በጋለ ፍላጎት ልትሆኑ ትችላላችሁ፣ ያን አካባቢ ለማጎልበት። በተመሳሳይ ጊዜ፣ የእግዚአብሔር ፍቃድ ካልሆነ የተለየ መንፈሳዊ ስጦታ ልትቀበሉ አትችሉም፣ ምንም ያህል በብርቱ ብትፈልጉትም። እግዚአብሔር ወሰን የሌለው ብልህ ነው፣ እናም እርሱ የትኛው ስጦታ በተሻለ መልኩ ውጤታማ እንደሚያደርጋችሁ ያውቃል፣ ለመንግሥቱ።

ምንም ያህል በአንዱ ወይም በሌላው ጸጋ ስጦታ ቢኖረንም፣ ሁላችንም የተጠራነው በርከት ያሉ አካባቢዎችን እንድናጎለብት ነው ፣ በመንፈሳዊ ስጦታዎች ዝርዝር ውስጥ የተጠቀሱትን፡ እንግዶችን በመቀበል፣ ምሕረትን እንድናሳይ፣ እርስ በርሳችን እንድናገለግል፣ ወንጌላዊነትን እንድናካሂድ፣ ወዘተ። እኛ ለእርሱ ክብር ሌሎችን ለማነጽ ካለው ተግባር ፍቅር የተነሣ እግዚአብሔርን ለማገልገል እንደምንሻ፣ እሱም ለስሙ ክብር ያመጣል፣ ቤተ-ክርስቲያኑን ያሳድጋል፣ ይሸልመናልም(1 ቆሮንቶስ 3:5-8፣ 12:31–14:1)። እግዚአብሔር ቃል ገብቶልናል፣ ደስ ስናሰኘው፣ የልባችንን መሻት ይሰጠናል (መዝ. 37፡4-5)። ይህም በ’ርግጥ እሱን ለማገልገል እኛን ማዘጋጀትን ያካትታል፣ ለእኛ ዓላማና ርካታን በመስጠት መልኩ።

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

እግዚአብሔር መንፈሳዊ ስጦታዎችን እንዴት ያድላል? እግዚአብሔር የለመንኩትን መንፈሳዊ ስጦታ ይሰጠኛልን?
© Copyright Got Questions Ministries