settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የእግዚአብሔር ወንዶች ልጆች እና የሰዎች ሴቶች ልጆች በዘፍጥረት 6፡1-4 እነማን ነበሩ?

መልስ፤


ዘፍጥረት 6፡1-4 የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን ወንዶች ልጆችና የሰዎችን ሴቶች ልጆች ነው። በርካታ አስተያየቶች ተሰንዝረዋል የእግዚአብሔር ወንዶች ልጆች ማን እንደነበሩ እና ለምን ከሰዎች ሴቶች ልጆች ስለወለዷቸው ልጆች ግዙፍነት ዝርያ (ያንን ነው ኒፊሊም የሚለው ቃል የሚያመለክተው)።

ሦስቱ ቀዳሚ አተያዮች፣ የእግዚአብሔርን ወንዶች ልጆች በተመለከተ 1) የወደቁ መላእክት ነበሩ፣ 2) ኃይለኞች የሰዎች ገዥዎች ነበሩ፣ ወይም 3) የሴት መልካም ዝርያዎች ከቃየን ክፉ ዝርያዎች ጋር ጋብቻ የፈጸሙ ነበሩ፣ የሚሉ ናቸው። ለመጀመሪያው ንድፈ-ሐሳብ ክብደት መስጠት የሚሆነው፣ በብሉይ ኪዳን “የእግዚአብሔር ወንዶች ልጆች” የሚለው ሐረግ ዘወትር የሚጠቅሰው ለመላእክት ነው (ኢዮብ 1:6፤ 2:1፤ 38:7)። የዚህ ዋነኛ ችግር የሚሆነው ማቴዎስ 22፡30 ላይ ነው፣ እሱም መላእክት እንደማያገቡ የሚያመለክተው። መጽሐፍ ቅዱስ ምንም ምክንያት አይሰጠንም መላእክት ጾታ እንዳላቸው ወይም መውለድ እንደሚችሉ። ሌሎቹ ሁለቱ አተያዮች ይህ ችግር የለባቸውም።

የ2) እና 3) አተያዮች ድክመት፣ ተራ ወንዶች ሰዎች ተራ ሴቶች ሰዎችን ማግባታቸው ልጆቻቸው “ግዙፋን” ወይም “የድሮ ኃይለኞች፣ ስማቸው የተጠራ” መሆናቸው ርግጠኝነት አይኖረውም። በተጨማሪም፣ እግዚአብሔር ለምን የጥፋት ውኃ በምድር ላይ እንዲመጣ ወሰነ (ዘፍጥረት 6፡5-7) እግዚአብሔር ኃይለኞቹ ወንዶች ሰዎች ወይም የሴት ዝርያዎች ተራ ሴቶች ሰዎችን ወይም የቃየንን ዝርያዎች እንዳያገቡ ፈጽሞ ሳይከለክል? እየመጣ ያለው የዘፍጥረት 6፡5-7 ፍርድ በዘፍጥረት 6፡1-4 ከተካሄደው ጋር የተያያዘ ነው። የወደቁ መላእክት ከሰው ሴቶች ጋር አደረጉ የተባለው የሴሰኝነት፣ የእምቢተኝነት ጋብቻ ይህንን አስፈሪ ፍርድ ትክክለኝነት ለማሳየት ይመስላል።

ቀደም ሲል እንደተገለጸው፣ የመጀመሪያው አመለካከት ችግር ማቴዎስ 22፡30 እንደሚገልጸው፣ “በትንሣኤ ቀን ሰዎች አያገቡም አይጋቡምም፤ እንደ ሰማይ መልአክ ይሆናሉ እንጂ።” ሆኖም፣ ጽሑፉ “መላእክት ማግባት አይችሉም” አይልም። እንዲያው መላእክት እንደማያገቡ ነው የሚጠቁመው። ሁለተኛ፣ ማቴዎስ 22፡30 የሚያመለክተው ስለ “ሰማይ መላእክት” ነው። ስለ ወደቁ መላእክት አያመለክትም፣ እነሱም ስለ እግዚአብሔር የተፈጥሮ ሥርዓት ግድ ስለሌላቸው፣ እናም የእግዚአብሔርን ዕቅድ በማበላሸት በንቃት የሚሹ ናቸው። ሐቁ፣ የእግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክት አያገቡም፣ ወይም በጾታዊ ግንኙነት አይጠመዱም ማለት ለሰይጣንና ለእሱ አጋንንት አንድ ነው ማለት አይደለም።

አተያይ 1) የተሻለ የሚመስል አቋም ነው። አዎን፣ አስገራሚ “ተቃርኖ” ነው፣ መላእክት ጾታ የላቸውም ማለትና አያይዞ “የእግዚአብሔር ልጆች” ማለት፣ የወደቁ መላእክት ከሴት ሰዎች ይወልዳሉ ማለት። ሆኖም፣ መላእክት መንፈሳዊ ሕላዌ እስከሆኑ ድረስ (ዕብራውያን 1፡14)፣ በሰው ሊገለጡ ይችላሉ፣ በሥጋ አካል (ማርቆስ 16፡5)። የሰዶምና የገሞራ ሰዎች ከሁለቱ መላእክት ጋር ግብረ-ሥጋ ለመፈጸም አስበው ነበር፣ ከሎጥ ጋር ከነበሩት (ዘፍጥረት19፡1-5)። መላእክት የሰው መልክ ይዘው ሊከሰቱ እንደሚችሉ አሳማኝ ነው፣ ይልቁንም የሰው የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ፈጽመው መውለድ እንደሚችሉ። የወደቁ መላእክት ለምን ይሄንን ደጋግመው አያደርጉትም? ይህ የሚመስለው እግዚአብሔር ይህንን የከፋ ኃጢአት የፈጸሙትን መላእክት ስላሰራቸው ነው፣ ስለሆነም ሌሎቹ የወደቁ መላእክት ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጽሙ (ይሁዳ 6 ላይ እንደተገለጸው)። የድሮዎቹ የዕብራይስጥ ተርጓሚዎች እና የተጓዳኝና ሌሎች ሃይማኖታዊ ጽሑፎች ሙሉ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፣ የወደቁ መላእክት “የእግዚአብሔር ልጆች” ናቸው ለሚለው አስተያየት፣ እሱም ዘፍጥረት 6፡1-4 ላይ የተጠቀሰው። ይህ በምንም ምክንያት ክርክሩን ከፍጻሜ አያደርስም። ሆኖም፣ ዘፍጥረት 6፡1-4 ላይ ያለው የሚያካትተው አስተሳሰብ፣ የወደቁ መላእክት ከሴት ሰዎች ጋር መወዳጀታቸው ጠንከር ያለ ዐውደ-ጽሑፋዊ፣ ሰዋሰዋዊ፣ እና ታሪካዊ መሠረት እንዳለው ነው።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የእግዚአብሔር ወንዶች ልጆች እና የሰዎች ሴቶች ልጆች በዘፍጥረት 6፡1-4 እነማን ነበሩ?
© Copyright Got Questions Ministries