settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ ባርነትን ይኮንናል?

መልስ፤


ባርነትን ያለፈ ጊዜ ነገር አድርጎ የመውሰድ እሳቤ አለ፡፡ ዛሬም 27 ሚሊዮን ሰዎች በአለም ላይ ለባርነት አልፈው ተሰጥተው ተብሎ ይገመታል፡፡ በግዳጅ የጉልበት ስራ የፆታ ግንኙነት ንግድ ዘርን ተከትሎ በመጣ ውርስ…በመሳሰሉት፡፡ ከኃጢያት ባርነት የተዋጁ የክርስቶስ ተከታዮች ባዛሬው ጊዜ የሚደረገውን የሰዎች ባርነት ለማስቆም የመጀሪያዎቹ ቅድሚያን የሚወስዱ መሆን አለባቸው፡፡ ጥያቄ የሚነሳው እንግዲያው መጽሐፍ ቅዱስ ለምን ባርነትን በመቃወም ለምን አይናገርም? ለምን መጽሐፍ ቅዱስ በእውነት የሰዎች ን ባርነትን የሚደግፍ ይመስላል?

መጽሐፍ ቅዱስ በትክክል በግልጽ ባርነትን አይኮንንም፡፡ ባሪያዎች እንዴት መያዝ እንዳለባቸው መመሪያ ይሰጣል (ዘዳ 15:12-15; ኤፌ 6:9; ቆላ 4:1) ግን ባርነት አብሮ አይከለክልም፡፡ ብዙዎች መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉንም አይነት ባርነት እንደሚቃወም ይቆጥራሉ፡፡ ብዙዎች ሳይረዱት የሚቀሩት ነገር ባርነት በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የነበረው ባርነት በአለም ላይ በለፉት ዘመናት ከሆነው ባርነት ጋር የተለየ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የነበረው ባርነት በአንድ ዘር ላይ ላይቶ የሚደረግ አለበረም፡፡ ሰዎች ባላቸው ዜግነት እና የቆዳ ቀለም አልነበረም ባሪያዎች የሚሆኑት፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ባርነት በኢኮኖሚ ላይ የተመሰረተ ነበር፤ በማህበረስብ ውስጥ የነበረ የደረጃ ልዩነት ነው፡፡ ሰዎች በእዳ ውስጥ ሲገቡ እና ለቤተሰቦቻቸውን የሚያስፈልጋቸውን ማቅረብ ሲያቅታቸው ራሳቸውን ለባርነት ይሸጡ ነበር፡፡ በአዲስ ኪዳን ጊዜ አንዳንድ ጊዜ ሐኪሞች ጠበቆች እና የፖለቲካ ሰዎችም ጭምር ለሌላው ሰው ባሪያዎች ይሆኑ ነበር፡፡ አንዳንድ ሰዎች ባሪያ መሆንን ሁሉም የሚያስፈልጋቸውን ነገር ከጌታቸው ለማግኘት ሲሉ ይመርጣሉ፡፡

ባለፉት ጥቂት አመታት የነበረው ባርነት በተለየ ሁኔታ በቆዳ ቀለም ላይ የተመሰረተ ነበር፡፡ በአሜሪካን ብዙ ጥቁር ሰዎች በዜግነታቸው እንደ ባሪያ ይቆጠሩ ነበር ብዙ ባሪያ ያላቸው ሰዎች ጥቁር ሰዎች አነስተኛ ክብር የማይገባቸው አድርገው ይቀበላሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ዘርን መሰረት ያደረገ ባርነትን ይቃወማል፤ ሁሉም ሰዎች ሰዎች በእግዚአብሔር የፈጠሩ በአምሳሉ የፈጠራቸው ናቸው (ዘፍ 1፡27)፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በሉይ ኪዳን ኢኮኖሚን መሰረት ያደረገ ባርነት ይፈቅዳል በመቆጣጠር፡፡ ዋናው ቁልፍ እውነት ነው መጽሐፍ ቅዱስ የሚፈቅደው ባርነት አሁን በዘመናችን ባለፉት ጥቂት ዘመናት ከነበረው ጋር ምንም አይነት ተማሳሳይነት የሌለው ነው፡፡

በተጨማሪም በሉይም አዲስ ኪዳንም በአፍሪካ በ19ኛው ዘመን የተደረገውን አይነት ሰዎችን መሸጥ ይቃወማል፡፡ አፍሪካ ባሪያዎችን በሚሸጡ ባሪያ በሚያድኑ ተከባ ነበር ወደ አዲስ ስፍራ አምጥተዋቸው የእርሻን ስራ እንዲሰሩ ያደርጉዋቸው ነበር፡፡ ይህ አይነቱ ነገር እግዚአብሔር ያስቆጣዋል፡፡ በመሰረቱ እንዲህ ያለ ወንጀል በሙሴ ህግ ያለው ቅጣት ሞት ነው (ዘጽ 21፡6)፡- ‹‹ ሰውን ሰርቆ ቢሸጥ፥ ወይም በእጁ ቢገኝ፥ እርሱ ፈጽሞ ይገደል።›› በተመሳሳይ በአዲስ ኪዳን የባሪያ ነጋዴዎች ‹‹ኃጢያተኞች ክፉዎች›› ተደርገው ይቆጠሩ እና አባታቸውን እናታቸውን የገደሉ ነፍሰ ገዳዩች ዘማዊ ውሸታም እና የሐሰት ምስክሮች ጋር በአንድ ላይ ይቆጠሩ ነበር (1ጢሞ 1፡8-10)፡፡

ሌላኛው አሳማኝ ነጥብ የመጽሐፍ ቅዱስ ዋናው አላማው የደህንነትን መንገድ ለሰዎች ማሳየት ነው እንጂ ማህበረሰብን ማሻሻል አይደለም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በአብዛኛው የሚያቀርበው ከውስጥ ወደ ውጭ ነው፡፡ አንድ ሰው ፍቅርን ምህረትን እና የእግዚአብሔር ጸጋን ደህንነትን ከተቀበለ ከተለማመደ እግዚአብሔር ነፍሱን ያድሳል አስተሳሰቡ እና ተግባሩ ይለወጣል፡፡ የእግዚአብሔርን የደህንነት ስራ እና ነጻነት ከኃጢያት በመውጣት እግዚአብሔር ነፍሱን ያደሰለት ለሌላው ሰው ራሱን ባሪያ አድርጎ ማቅረብ ትክክል እንዳልሆነ ያውቃል፡፡ ጳውሎስ እንዳለው ባሪያ መሆን የሚችለውን ያያል‹‹በክርስቶስ የሆነ ወንድም›› (ፊሊ 1፡16)፡፡ የእግዚአብሔርን ጸጋ በትክክል የተካፈለ የተለማማደ ሰው ለሌሎች ደግ መልካም ይሆናል፡፡ ያም ደግሞ የሚጽሐፍ ቅዱስ ባርነትን የማቆሚያ ማዘዣ ነው፡፡

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ ባርነትን ይኮንናል? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries