settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ ከጋብቻ በፊት ስለሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት/ ቅድመ-ጋብቻ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ምን ይላል?

መልስ፤


በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከጋብቻ በፊት የሚደረግን የግብረ-ሥጋ ግንኙነት በትክክል ለማመልከት ያገለገለ የዕብራይስጥ ወይም የግሪክ ቃል የለም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በማይካድ መልኩ አመንዝራነትን እና ግብረ-ገብነትን ያጣ ጾታዊ ግንኙነትን ይኮንናል፤ ነገር ግን ከጋብቻ በፊት የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት በሥነ-ጾታው ግብረ-ገብነትን እንዳጣ ይቆጠራል? በ1ኛ ቆሮንቶስ 7፤2 መሠረት “አዎ” ግልጽ መልስ ነው፤ “ነገር ግን ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራስዋ ባል ይኑራት።” በዚህ ጥቅስ ውስጥ ጋብቻ ከዝሙት “መዳኛ” እንደሆነ ጳውሎስ ያን ያትታል፡፡ 1ኛ ቆሮንቶስ 7፤2 በዋናነት ሰዎች እራሳቸውን መቆጣጠር ባለመቻላቸው እና በጣም ብዙዎች ከጋብቻ ውጪ ዝሙትን በማድረጋቸው ምክንያት ሰዎች ማግባት አለባቸው እያለ ነው፡፡ ከዚያም ፍላጎቶቻቸውን በተገቢው መንገድ ማሟላት ይችላሉ፡፡

1ኛ ቆሮንቶስ 7፤2 ከጋብቻ በፊት የሚደረግን የግብረ ሥጋ ግንኙነትን በጾታዊ ግብረ-ገብነት ማጣት ገለጻ ውስጥ በግልጽ ካካተተ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ግብረ-ገብነት ያጣ ጾታዊ ግንኙነት ኃጥአት እንደሆነ የሚኮንኑ ጥቅሶችም ሁሉ ከጋብቻ በፊት የሚደረገውን የግብረ ሥጋ ግንኙነትንም እንደ ኃጥአት ይኮንናሉ፡፡ ከጋብቻ በፊት የሚደረግ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ግብረ-ገብነት ባጣ የጾታዊ ግንኙነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ገለጻ ውስጥ ተካቷል፡፡ ከጋብቻ በፊት የሆነ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ኃጥአት እንደሆነ የሚያውጁ ብዙ መጽሐፍቶች አሉ (የሐዋሪያት ሥራ 15፡20፣ 1ኛ ቆሮንቶስ 5፡1፣6፡13፣18፣10፡8፣ 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡21፣ ወደ ገላቲያ ሰዎች 5፡19፣ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፡3፣ ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3፡5፣ 1ኛ ተሰሎንቄ 4፡3፣ የይሁዳ መልዕክት 7)፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ከጋብቻ በፊት ፍፁም መታቀብን ያውጃል፡፡ በባልና በሚስቱ መሐከል የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት እግዚአብሔር የሚያፀድቀው ብቸኛው ጾታዊ ግንኙነቶች ነው (ወደ ዕብራውያን ሰዎች 13፤4)፡፡

ብዙውን ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነትን ሌላኛውን ጎን፤ መራቢያነቱን፤ ከግምት ውስጥ ሳናስገባ “አዝናኝነቱ” ብቻ ላይ እናተኩራለን፡፡ በጋብቻ ውስጥ የሆነ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት አስደሳች ነው እናም እግዚአብሔርም በዚያ መልኩ አድርጎታል፡፡ እግዚአብሔር ወንዶችና ሴቶች ጾታዊ ተግባሮችን በጋብቻ ክልል ውስጥ ሆነው እንዲደሰቱበት ይፈልጋል፡፡ የሰሎሞን መዝሙሮች እና ሌሎች ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦች (ለምሳሌ መጽሐፈ ምሳሌ 5፤19) የግብረ-ሥጋን አስደሳችነት በግልጽ ይገልጻሉ፡፡ ሆኖም ግን እግዚአብሔር ለግብረ ሥጋ ግንኙነት ያለው ሀሳብ ልጆችን ማፍራትንም እንደሚጨምር ጥንዶች ያን ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ ስለዚህ ጥንዶች ከጋብቻ በፊት በግብረ ሥጋ ግንኙነት ውስጥ መግባት በድጋሚ ስህተት ነው፤ ለእነርሱ ያልተፈቀደውን ደስታ በመደስት ላይ ናቸው እናም እግዚአብሔር ለሁሉም ልጅ ካዘጋጀው ከቤተሰባዊ አደረጃጀት ውጪ የሰውን ህይወት የመፍጠሩን ዕድል በመውሰድ ላይ ናቸው፡፡

ተግባራዊነት ትክክለኛውን ከስህተቱ የሚለይ ባይሆንም ከጋብቻ በፊት የግብረ ሥጋ ግንኙነት በማድረግ ላይ ያለው የመጽሐፍ ቅዱስ መልዕክት ተግባራዊ ተደርገው ቢሆን ኖሮ በግብረ ሥጋ ግንኙነት ምክንያት የሚተላለፉ በጣም ጥቂት በሽታዎች ይሆናሉ፣ በጣም ጥቂት ውርጃዎች፣ በጣም ጥቂት ያላገቡ እናቶች እና ያልተፈለጉ እርግዝናዎች ይሆናሉ፤እና በሕይወታቸው ያለ ወላጆቻቸው የሚያድጉ በጣም ጥቂት ልጆች ይሆናሉ፡፡ ከጋብቻ በፊት ወደሚደረግ የግብረ ስጋ ግንኙነት ስንመጣ መታቀብ የእግዚአብሔር ብቸኛው ህግ ነው፡፡ መታቀብ ህይወትን ያድናል፣ ህፃናትን ይጠብቃል፣ ለፆታዊ ግንኙነቶች ተገቢውን ዋጋ ይሰጣል እና እጅግ በጣም በዋናነት እግዚአብሔርን ያከብራል፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ ከጋብቻ በፊት ስለሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት/ ቅድመ-ጋብቻ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ምን ይላል?
© Copyright Got Questions Ministries