settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የዘላለም ደኅንነት ኃጢአት ለመፈጸም “ፍቃድ” ነውን?

መልስ፤


የዘላለማዊ ደኅንነት አስተምህሮት ተደጋጋሚ ተቃውሞ የሚሆነው፣ ሰዎች እንደፈቀዱት ቢኖሩ ይድናሉ የሚል መረዳት በመኖሩ ነው። ይህ “ውጭውን” ሲታይ እውነት ነው፣ በተጨባጭ ግን እውነት አይደለም። በኢየሱስ ክርስቶስ በእውነት የተዋጀ ሰው፣ ቀጣይነት ባለው የፍቃድ ኃጢአት ባሕርይ ሊኖር አይችልም። ልዩ ምልክት ማድረግ አለብን፣ ክርስቲያን እንዴት መኖር እንዳለበትና፣ ደኅንነትን ለመቀበል አንድ ሰው ምን ማድረግ እንዳለበት መሐል ያለውን።

መጽሐፍ ቅዱስ ግልጽ ነው፣ እሱም፣ ደኅንነት በጸጋ ብቻ፣ በእምነት በኩል ብቻ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው (ዮሐንስ 3፡16፤ ኤፌሶን 2፡8-9፤ ዮሐንስ 14፡6)። አንድ ሰው በእውነት በኢየሱስ ክርስቶስ ባመነበት ቅጽበት፣ እሱ ወይም እሷ ድነዋል፤ እናም በዛ ደኅንነት ተጠብቀዋል። ደኅንነት በእምነት ይገኛል፣ ነገር ግን ከዚያ በኋላ በሥራ ይጸናል። ሐዋርያው ጳውሎስ ይሄንን ጉዳይ በተመለከተ በገላትያ 3፡3 እንዲህ በማለት ይጠይቃል፣ “እንዲህን የማታስተውሉ ናችሁ? በመንፈስ ጀምራችሁ አሁን በሥጋ ትፈጽማላችሁን?” በእምነት ከዳንን፣ ደኅንነታችን የሚጠበቀውም ሆነ የሚረጋገጠው በአምነት ነው። የራሳችንን ደኅንነት ልናገኝ አንችልም። ስለሆነም፣ በራሳችን የደኅንነታችንን ማረጋገጫ ልናገኝም አንችልም። ደኅንነታችንን የሚያረጋግጥ እግዚአብሔር ነው (ይሁዳ 24)። በራሱ ጭብጥ አጽንቶ የያዘን የእግዚአብሔር እጅ ነው (ዮሐንስ 10፡28-29)። የእግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ ምንም ነገር ከእሱ እንዳይለየን ያደረገው (ሮሜ 8፡38-39)።

ማንኛውም ዓይነት የዘላለም ደኅንነት ክህደት፣ በመሠረተ ሐሳቡ፣ የራሳችንን ደኅንነት በራሳችን መልካም ሥራና ጥረት ማግኘት አለብን ከሚል እምነት የነጨ ነው። ይህም ባጠቃላይ ደኅንነት በጸጋ የሚለውን የሚጻረር ነው። የዳንነው በክርስቶስ ሥራ ምክንያት ነው፣ በራሳችን አይደለም (ሮሜ 4፡3-8)። የእግዚአብሔርን ቃል የግድ መታዘዝ አለብን፣ ወይም መልካም ሕይወትን መኖር አለብን፣ የራሳችንን ደኅንነት ለማግኘት የሚል ክርክር ማቅረብ፣ የኢየሱስ ሞት የኃጢአታችንን ዋጋ ለመክፈል አይበቃም ማለት ነው። የኢየሱስ ሞት የኃጢአታችንን ዋጋ ለመክፈል ፈጽሞ በቂ ነው— ያለፈውን፣ የአሁኑን፣ እና የወደፊቱን፣ ይህም ቅድመ-ደኅንነት እና ከደኅንነት በኋላ ያለውን ያጠቃልላል(ሮሜ 5፡8፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 15፡3፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡21)።

ይሄንን ማለት ክርስቲያን እንደፈለገው ቢኖርም አሁንም ድኗል ማለት ነውን? ይህ በመሠረቱ መላምታዊ ጥያቄ ነው፣ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ግልጽ እንዳደረገው እውነተኛ ክርስቲያን “እሱን እንዳፈቀደው” መኖር ስለማይችል ነው። ክርስቲያኖች አዲስ ፍጥረት ናቸው (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡17)። ክርስቲያኖች የመንፈስ ፍሬ ያፈራሉ (ገላትያ 5፡22-23)፣ የሥጋ ድርጊት ያልሆኑትን (ገላትያ 5፡19-21)። አንደኛ ዮሐንስ 3፡6-9 በግልጽ እንደሚያስቀምጠው እውነተኛ ክርስቲያን ቀጣይነት ባለው ኃጢአት አኖርም። ጸጋ ኃጢአትን ያበዛል የሚለውን ክስ በተመለከተ ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ገልጿል፣ “እንግዲህ ምን እንላለን? ጸጋ እንዲበዛ በኃጢአት ጸንተን እንኑርን? አይደለም። ለኃጢአት የሞትን እኛ ወደ ፊት እንዴት አድርገን በእርሱ እንኖራለን?” (ሮሜ 6፡1-2)።

የዘላለም ደኅንነት ኃጢአትን ለመፈጸም ፍቃድ አይደለም። ይልቁን፣ የእግዚአብሔር ፍቅር እሱም በክርስቶስ ለሚያምኑት የሆነውን ማስረገጫና የደኅንነት እውቀት ነው። የእግዚአብሔርን ታላቅ የሆነ የደኅንነት ስጦታ ማወቅና መረዳት መቻል ለኃጢአት ፍቃድ መስጠት ከሚለው በተጻራሪው ነው። ማንም ቢሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ የከፈለውን ዋጋ አውቆ እንዴት አድርጎ፣ በኃጢአት ሕይወት ሊቀጥል ይችላል (ሮሜ 6፡15-23)? ማንም ቢሆን የእግዚአብሔርን ያልተጠበቀና የተረጋገጠ ፍቅር እሱም ለሚያምኑት የሆነውን፣ ከተረዳ በኋላ፣ ያንን ፍቅር መልሶ በእግዚአብሔር ፊት ይወረውራል? እንዲህ ዓይነቱ ሰው የሚያሳየው የዘላለም ደኅንነት የኃጢአት ፍቃድ እንደሰጠው አይደለም፣ ነገር ግን ይልቁን እሱ ወይም እሷ በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን ደኅንነት በትክክል እንዳልያዙት ነው። “በእርሱ የሚኖር ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፤ ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ አላየውም አላወቀውምም” (1ኛ ዮሐንስ 3፡6)።

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የዘላለም ደኅንነት ኃጢአት ለመፈጸም “ፍቃድ” ነውን?
© Copyright Got Questions Ministries