settings icon
share icon
ጥያቄ፤

እግዚአብሔርን መጠየቅ ስህተት ነውን?

መልስ፤


ጥያቄው እግዚአብሔርን መጠየቅ አለብን ወይስ የለብንም? በምን አይነት መንገድ እና በምን ምክንያት እርሱን እንጠይቃለን? አምላክን መጠየቅ በራሱ ስህተት አይደለም፡፡ ነቢዩ ዕንባቆም የጌታን እቅድ እና አሠራር በተመለከተ እግዚአብሔርን በተመለከተ ጥያቄዎች ነበሩት፤ ዕንባቆምን ለጥያቄዎቹ ከመገሠጽ ይልቅ በትዕግስት ምላሽ ሰጥቷል፡፡ ነቢዩም መጽሐፉን በመዝሙር በምስጋና አጠናቀቀ፡፡ በመዝሙር መጽሐፍ ውስጥ ብዙ ጥያቄዎች ለእግዚአብሔር ይቀርባሉ (መዝሙር 10, 44, 74, 77)፡፡ እነዚህ የእግዚግዚአብሔር ጣልቃ ገብነት እና ድነት የፈለጉ የተሰደዱ የተጨነቁ ሰዎች ጩኸቶች ናቸው፡፡ ምንም እንኳን እግዚአብሔር ጥያቄያችንን እኛ በሚፈልገው መንገድ ባይመልስልንም በእውነተኛ ልብ ከልብ ብንጠየቀው እንደሚቀበለን ከእነዚህ አንቀጾች እናነባለን፡፡

ከልብ የማይነሱ ጥያቄዎች ወይም ግብዝነት የሌላቸው ጥያቄዎች የተለያዩ ጥያቄዎች ናቸው፡፡ "ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና።" (ዕብራውያን 11 6) ንጉሥ ሳኦል እግዚአብሔርን ሳይታዘዝ ከቀረ በኋላ ጥያቄዎቹ ምላሽ አላገኙም (1 ሳሙኤል 28፡ 6)፡፡

እግዚአብሔር የእርሱን መልካምነት ጥያቄ ውስጥ እንድናስገባ የሚያደርጉ ነገሮች እንዲሆን እንደሚፈቅድ ግራመጋባ የእግዚአብሔርን መልካምነት በቀጥታ ከመጠየቃችን የተለየ ነው፡፡ ጥርጥር የእግዚአብሔርን ሉዓላዊነት ከመጠየቅ ባሪውን ከመቃወም የተለየ ነው፡፡ በአጭሩ, መራራ, የማይታመን, ወይም ዓመፀኛ ልብ እንጂ ሀቀኛ ጥያቄ ኃጢአት አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ጥያቄዎችን አይፈራም፤ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር የጠበቀ ህብረት እንዲኖረን ይጋብዘናል፡፡ እግዚአብሔርን ስንጠይቅ በተዋረደ መንፈስ እና ክፍት በሆነ አይምሮ መሆን አለበት፡፡ እግዚአብሔርን ልንጠይቅ እንችላለን፤ ነገር ግን እኛ የእርሱን መልሰ ከልባችን ካልፈለግን መልስን መጠበቅ የለብንም፡፡ እግዚአብሔር ልባችንን ያውቃል፤ እርሱ ብርሃኑን እንዲሰጠን ከልባችን እንፈልገው ይሆናል ይህንንም እርሱ ያውቃል፡፡ የእውነት ልቦቻችን እግዚአብሔርን መጠየቅ መፈለግ ትክክልና ስህተት ነው የሚለው የሚወሰነው ነው፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

እግዚአብሔርን መጠየቅ ስህተት ነውን? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries