settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ የህይወትን አላማ ስለማግኘት ምን ይላል?

መልስ፤


በመጽሐፍ ቅዱስ የህይወታችን አላማ ምን መሆን እንዳለበት ግልጽ ነው፡፡ ሰዎች በብሉይም ሆነ በአዲስ የህይወታቸውን አላማ ለማግኘት ጥረዋል ፈልገዋል፡፡ ሰለሞን በምድር ላይ ከኖሩ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ጥበበኛ ነበር፤ በዚህ አላም ላይ የህይወትን ከንቱነት ተረድቶ ነበር፡፡ የዚህን ሃሳብ መደምደሚያ በመክብብ መጽሐፍ ላይ ገልጾአል፡፡ መክ 12፡13-14 ‹‹የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ እግዚአብሔር ሥራን ሁሉ የተሰወረውንም ነገር ሁሉ፥ መልካምም ቢሆን ክፉም ቢሆን፥ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና።›› ሰለሞን እንዲህ አለ ህይወት በሃሳባችን እና በኑሮአችን እግዚአብሔርን ማክበር ተዕዛዙን መጠበቅ ነው፤ አንድ ቀንም በእግዚአብሔር ፊት እንቆማለን፡፡ የህይወታችን አላማ ድርሻ እግዚአብሔርን መፍራት እና እርሱን መታዘዝ ነው፡፡

ሌላኛው የህይወታችን አላማ ድርሻ ህይወትን በትክክለኛው መንገድ ሲሄድ ማየት ነው፡፡ ትኩረታቸው በዚህ አለም ላይ እንደሆኑት ሳይሆን ንጉስ ዳዊት እርካታን በሚመጣው ህይወት ተመልክቶአል፡፡ እንዲህ አለ ‹‹እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ።›› (መዝ 17፡15)፡፡ ለዳዊት ሙሉ እርካታ በሚቀጥለው ህይወት ሲነሳ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ሲያየው እርሱን ሲመስለው የሚመጣ ነው፡፡ (1 ዮሐ 3:2).

በመዝሙር 73 አሳፍ እንዴት እንደተፈተና ይናገራል በክፉዎች ቀና ምንም ግድ የሌላቸው የሚመስሉ እድላቸውንም በሌሎች ትከሻ ላይ ያደረጉ እርሱ ግን መጨረሻቸውን ተመለከተ፡፡ እነርሱ ለማግኘት የሮጡትን በማነጻጸር በቁ.25 እንዲህ ይላል ‹‹በሰማይ ያለኝ ምንድርነው; በምድር ውስጥ ከአንተ ዘንድ ምንእሰሻለሁ;›› ለአሳፍ ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ህብረት በምድር ላይ ካለ ነገር ሁለ ይበልጣል፡፡ ከዚያ ህብረት ውጪ ህይወት ምንም አላማ የላትም፡፡

ሐዋሪያው ጳውሎስ ከሙታን ከተነሳው ከኢየሱስ ጋር ከመጋፈጡ ከመለወጡ በፊት በሃይማኖተኝነት ያሳካቸው ነገሮች ኢየሱስ ከማወቅ ጋር ሲነጻጸሩ እንደ ጉድፍ ናቸው ብሎአል፡፡ በፊሊ 3፡9-10 ኢየሱስን ከማወቅ በላይ የምፈልገው ነገር የለም አለ፤ ‹‹በእርሱ መመስረት›› በእርሱ መገኘት፤ የእርሱን ጽድቅ ማገኘት እና በእርሱ ላይ ባለ እምነት መኖር፤ መከራ እና ሞትም እንኳ ቢሆን፡፡ የጳውሎስ አላማ ክርስቶስን ማወቅ ነበር፤ እርሱን በማመን የሚገኘውን ጽድቅ ማግኘት፤ ያ ምንም እንኳ ወደ መከራ የሚያመጣውም በሆን ከእርሱ ጋር ህብረት ማድረግ (2 ጢሞ 3:12):: በአጠቃላይ ከሙታን ከተነሱት መሃከል የሚሆንበትን ጊዜ ተመልክቶአል፡፡

እግዚአብሔር ሰውን በመጀመሪያ ሲፈጥረው አላማው የነበረው 1) እግዚአብሔርን እንዲያከብር እና ከስርሱ ጋር ባለው ህብረት እንዲደሰት 2) ከሌሎች ጋር መልካም ግንኙነት እንዲኖረው 3) እንዲሰራ 4) ምድርን እንዲገዛ ነበር፡፡ ሰው ግን በኃጢያት በመውደቁ ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ህብረት ተቋረጠ፤ ከሌሎችም ጋር የነበረው ግንኙነት ተበላሸ፤ ስራውም ሁልጊዜ ፍርሃት ተስፋመቁረጥ እንደገና መልሶ በተፈጥሮ ላይ የሚሰለጥንበትን ለመጠገን መታገል ሆነ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ህብረቱን በማደስ በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ብቻ የህይወት አላማ እንደገና ማግኘት ይችላል፡፡

የሰው አላማ እግዚአብሔርን ለዘላለም ማክበርና ማስደሰት ነው፡፡ እግዚአብሔርን በፍራትና በመታዘዝ፤ አይናችን በሰማይ ባለው ቤታችን ላይ በመትከል፤ እርሱን ተጠግተን በማወቅ እናከብረዋለን፡፡ እግዚአብሔርን በህይወታችን የእርሱን አላማ በመከተላችን እናከብረዋለን፤ ይህም ዘለቄታዊ ደስታን ለእኛ ያዘጋጀውን የተትረፈረፈ ህይወት እንድንለማመድ ያስችለናል፡፡

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ የህይወትን አላማ ስለማግኘት ምን ይላል? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries