settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ ስለብልጽግና ወንጌል ምን ይላል?

መልስ፤


በብልጽግና ወንጌል እንደሁም የእምነት ቃል “Word of Faith,” ተብሎ በሚታወቀው አማኞች መጽሐፍ ቅዱሳዊ የክርስትና እውነት ጋር የተቃረነ እግዚአብሔር ክርስቲያኖችን የሚጠቀምባቸው ሆኖ ሳለ እግዚአብሔርን መጠቀሚያ እንዲያደርጉ ተነግሮአቸዋል፡፡ የእምነት ቃል ወይንም የብልጽግና ስነመለኮት መንፈስ ቅዱስ አማኞችን የፈቀዱትን ሁሉ ለማስፈጽም የሚጠቅም አድርጎ ያስቀምጣል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረን መንፈስ ቅዱስ አካል ያለው እንደሆነና አማኞች የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዲፈጽሙ የሚያስችላቸው እንደሆነ ነው፡፡ የብልጽግና ወንጌል በመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ሰርጎ የገባውን አጥፊ ስስታም አካለት ጋር በጣም ይመሳሰላል፡፡ ጳውሎስና ሌሎች ሐዋሪያት እንደዚህ አይነት ነፋቄ ከሚያስተምሩ ከሃሰት አስተማሪዎች ጋር አልተባበሩም ወይም አልተስማሙም፡፡ አደገኛ የስህተት አስተማሪዎች ብለው ለይተው አወጧቸው እና ክርስቲያኖችም እንዲሸሹአቸው እጥብቀው አስገነዘቡአቸው፡፡

ጳውሎስ ስለእንደነዚህ አይነት ሰዎች ጢሞቲዎስን አስጠንቅቆታል 1 ጢሞ 6:5, 9-11. ይህም ማለት በተበላሸ አይምሮ እግዚአብሔርን መምሰል የፍላጎቶቻቸውና የምኞታቸውን የሚያገኝበት አድርጎ ለሚወስዱ ባለጠጎች የባለጥግነት ምኞት በወጥመድ ይጥላቸዋል ቁ.9፡፡ ኃብትን ማሳደድ ለክርስቲያኖች አደገኛ መንገድ ነው፤ እግዚአብሔርም ከሚያስጠንቅቅበት ነገር አንዱ ነው፡፡ ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ፥ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ።ቁ.10 ባለጠግነት ምሳሌነት ላለው ህይወት ምክንያታዊ ግብ ቢሆን ኢየሱስ ይከተለው ነው፡፡ ነገር ግን እርሱ እንደዚያ አላደረገም፤ የመረጠው በእርሱ ሃሰብ ምንም ስፍራ እንዳይኖረው ነው(ማቲ8:20) ደቀመዛሙርቱም እንደዚሁ እንዲያደርጉ አስተማራቸው፡፡ ከደቀመዛሙርቱ ለሃብት ቦታ የነበረው ብቸኛው ሰው ይሁዳ ብቻ እንደነበር ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡

ጳውሎስ መመኝት ጣኦትን ማምለክ ነው ብሎአል፡፡(ኤፌ 5:5) ለኤፌሶን ሰዎች ማንም የመመኘትን የኃጢያተኝነትን ሃሳብ እንዳያቀርብ መመሪያን ሰጥቶአቸዋል፡፡ (ኤፌ 5:6-7). ብልጽግና እግዚአብሔር በራሱ እንዳይሰራ ይከለክለዋል ማለትም እግዚአብሔር የሁለም ነገር ጌታ ባለቤት አይሆንም ምክንያቱም እኛ እንዲሰራ እስካልፈቀድንለት ድረስ ሊሰራ አይችልም፡፡ እንደ እምነት ቃል አስተምህሮ ለእግዚአብሔር መሸነፍ በእግዚአብሔር መታመን አይደለም፤ እምነት የብልጽግና አስተማሪዎች አለመን የሚቆጣጠር መንፈሳዊ ህጎችን የማምታታት ስልት ቀመር ነው፡፡ ‹‹የእምነት ቃል›› ስም የሚያመለክተው ይህ እንቅስቃሴ የሚያስተምረው እምነት እኛ የምንለው ከምንታመነውና ወይንም ምንም አይነት አውነት ብንይዝ በልባችንም እርግጠኛ ከሆንበት ከዛ ይበልጣል፡፡

በእምነት እንቅስቃሴ የተለመደው የተወደደ ቃል መልካምን ማወጅ ነው “positive confession.”፡፡ይህ የሚያመለክተው ቃሎቹ በራሳቸው የመፍጠር ኃይል እንዳለቸው ነው፡፡ አንተ የምትናገረው የእምነት እንቅስቃሴ አስተማሪዎች እንደሚሉት ለአንተ የሚሆነውን ሁሉ ይወስናል፡፡ የአንተ አዋጅ ከእግዚአብሔር ለመቀበል ከፈለግክ ሁልጊዜ ያለመናውጥ መልካም መናገር አለብህ፡፡ እግዚአብሔርም ለመመለስ ይገደዳል (እግዚአብሔርን ሰው ሊያስገድደው እንደሚችል ይመስል!) እንግዲህ የእግዚአብሔር እኛን የመባረክ ችሎታ በእኛ እምነት ላይ የተንጠለጠለ ነው፡፡ ያዕ 4፡13-16 ከዚህ ትምህርት ጋር በቀጥታ ይጋጫል፡፡‹‹ አሁንም ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን እናተርፍማለን የምትሉ እናንተ፥ ተመልከቱ፥ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና።ሕይወታችሁ ምንድር ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና።›› እንኳን ወደፊት ነገሮች ወደ መኖር እንዲመጡ ለመናገር ቀርቶ ነገ የሚያመጣውን እንኳን አናውቅም፤ መኖራችንንም እንኳ አናውቅም፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኃብት አስፈላጊነት ትኩረት ከመስጠት ይልቅ በተቃራኒው እንዳንከተለው ያስጠነቅቀናል፡፡ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ክርስቲያኖች ይልቁንም አማኞች ከገንዘብ ፍቅር ነጻ መሆን አለባቸው (1 ጢሞ 3:3) (ዕብ 13:5). ገንዘብን መውደድ ወደ ክፋት ሁሉ ይመራል፡፡l (1 ጢሞ 6:10). ኢየሱስ አስጠንቋል፡- ‹‹የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ፥ ከመጐምጀትም ሁሉ ተጠበቁ አላቸው።›› (ሉቃ 12:15). ከዚህ ፈጽሞ በተለየ የእምነት ቃል ገንዘብን ስለማግኝት እና በኑሮ መክበር /possessions in this life/ ኢየሱስ ሲናገር፤- ‹‹ ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤›› (ማቲ 6:19). ሊታረቅ የማይችል ግጭት በብልጽግና ወንጌል ትምህርት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ትምህርት መካከል በተጨማሪ በይበልጥ በኢየሱስ በኢየሱስ ክርስቶስ ንግግር ተገልጾአል ማቲ 6:24, “ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም”

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለብልጽግና ወንጌል ምን ይላል?
© Copyright Got Questions Ministries