settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ፕሪተሪዝም /preterism/ ስለመጨረሻው ዘመን ያለው አመለካከት ምንድን ነው?

መልስ፤


እንደ ፕሪተርዝም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ ትንበቶች ሁል እውነተኛ ታሪኮች ናቸው፡፡ ፕሪተርስት የዮሐንስን ራዕይ መጽሐፍ አስመልክቶ ያላቸው ትርጓሜ የመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ግጭቶች ምሳሌያዊ መግለጫ እንጂ በመጨረሻው ዘመን ምን እንደሚሆን መግለጫ የሚሰጥ አይደለም የሚል ነው፡፡ ፕሪታሪዝም የሚለው ቃል ከላቲን ፕራተር praeter ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ ያለፈ ጊዜ “past.” ነው፡፡ እንግዲህ ፕሪታሪዝም የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች የመጨረሻውን ዘመን ጨምሮ ከዚህ በፊት ተፈጽመዋል የሚል አመለካከት ነው፡፡ ፕሪታሪዝም በቀጥታ የሚቀወመው የወደፊቱን የመጨረሻው ጊዜ ትንቢቶች አሁንም ገና የወደፊት ፍጻሜ እንዳላቸው አድርጎ የሚያየውን የመጪውን ጊዜ አመለካከት ነው፡፡

ፕሪታሪዝም በሁለት ይከፈላል፡- መሉ ፕሪታሪዝም እና ከፊል ፕሪታሪዝም ይህ ጽሁፍ ሙሉ ለሙሉ ፕሪታሪዝም (ወይንም አንዳንዶች ከፍተኛው ፕሪተሪዝም ብለው የሚጠሩት) ለመነጋገር ይገድበዋል፡፡ ፕሪታሪዝም የራዕይ መጽሐፍን የሚጪውን ጊዜ የመናገር ትንቢታዊ ብቃት ይክዳል፡፡ ፕሪታሪዝም እንቅስቃሴ የሚያስተምረው ሁሉም የአዲስ ኪዳን የመጪው ጊዜ ትንቢቶች ሮማውያን ኢየሩሳሌምን በወጉና ባቃጠሉ በ70 ዓ.ም ተፈጽሞአል በማለት ነው፡፡ ፕሪታሪዝም ከኢየሱስ ዳግም መመለስ ከመጨረሻው ዘመን ጋር የተያያዙ እያንዳንዱ ክስተት የፍዳው ዘመን የሙታን ትንሳኤ እና የመጨረሻ ፍርድ እንደተፈጸሙ ያስተምራል፡፡ (የመጨረሸውን ፍርድ በሚመለከት አሁንም በመፈጽም ላይ ነው) የኢየሱስ ወደ ምድር መምጣት መንፈሳዊ እንጂ አካላዊ አይደለም፡፡

ፕሪታሪዝም ህጉ በ70 ዓ.ም እንደተፈጸመ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር የነበረው ኪዳን እንዳበቃ ያስተምራል፡፡ በራዕይ 21፡1 ‹‹አዲስ ሰማይና ምድር›› ለፕሪታሪዝም በአዲሱ ኪዳን ውስጥ ያለችው አለም ማብራሪያ ነው፡፡ ክርስቲያኖች ‹‹አዲስ ፍጥረት›› እንደሆኑ (2 ቆሮ 5:17) በአዲሱ ኪዳን ውስጥ ያለችው አለም ‹‹አዲስ ምድር›› ነች፡፡ ይህ ምልከታ ፕሪታሪዝምን /preterism/ በቀላሉ አንዱ ሌላውን የመተካት አስተሳሰብን ‹‹replacement›› ወደመቀበል ይመራቸዋል፡፡

ፕሪታሪዝም /preterism/ በአብዛኛው ኢየሱስ ስለበለሷ የተናገረበትን ክፍል ብዙ ጊዜ ክርክራቸውን ለመደገፍ ይጠቅሳሉ፡፡ ‹‹እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም።››(ማቲ 24:34). ፕሪታሪስቶች ይህ ኢየሱስ በማቲዎስ 24 የተናገረው ሁሉ እርሱ በተናገረበት በአንድ ትውልድ ውስጥ መፈጸም አለበት፤ በ70 ዓ.ም የሆነው የእየሩሳሌም ጥፋትም ‹‹የፍርድ ቀን›› ነው እንደማለት ይወስዱታል፡፡

ከፕሪታሪዝም ጋር ያለው ችግር ብዙ ነው፡፡ አንድ እውነት አለ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ያለው ኪዳን ዘላለማዊ ነው፡፡ (ኤር 31:33–36), እስራኤል የምትታደስበት ዘመን ይመጣል (ኢሳ 11:12). ሐዋሪያው ጳውሎስ ሃሰትን የሚያስተምሩትን ሄሜኔዎስና ፊሊጦስ አስጠነቀቀ ‹‹እነዚህም። ትንሣኤ ከአሁን በፊት ሆኖአል እያሉ፥ ስለ እውነት ስተው፥ የአንዳንዶችን እምነት ይገለብጣሉ።›› (2 ጢሞ 2:17–18). ኢየሱስ ይህ ትውልድ ብሎ የጠቀሳቸው መወሰድ ያለበት በማቲዎስ 24 ላይ ያለው ሊፈጸም ሲጀምር ያለውን ለማየት በህይወት ያሉትን ለማለት እንደሆነ ነው፡፡

የመጨረሻው ዘመን ወስብስብነት ያለው የትምህርት አይነት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የራዕይ ምስሎችን ብዙ ትንቢቶችን ለማስተላለፍ መጠቀሙ ስለመጨረሻው ዘመን የተለያዩ ትርጉሞች እንዲኖሩ አድርጎአል፡፡ እነዚህን ነገሮች በሚመለከት በክርስትና ለአንዳንድ የሃሳብ ልዩነቶች ክፍት ቦታ አለ፡፡ ይሁን እንጂ ሙሉው ፕሪታሪዝም የጠበቀ የተቃውሞ ፍሰት ከኢየረሳሌም ውድቀት ጋር ነገሮችን በማገኛኘት የክርስቶስን ዳግም መምጣት አካላዊ መገለጥ በመካድ እና የፍዳው ዘመን አስከፊነት ዝቅ ያደርጋል፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ፕሪተሪዝም /preterism/ ስለመጨረሻው ዘመን ያለው አመለካከት ምንድን ነው?
© Copyright Got Questions Ministries