settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ቅድመ መወሰን ምንድነው? ዕጣ ፈንታ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነውን?

መልስ፤


ሮሜ 8፡29-30 ይነግረናል፣ “ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤ አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው።” ኤፌሶን 1፡5 እና 11 ያውጃል፣ “በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን… እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ፥ አስቀድመን የተወሰንን በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ተቀበልን።” ብዙ ሰዎች ጠንከር ያለ ጥላቻ በዕጣ ፈንታ ዶክትሪን ላይ አላቸው። ሆኖም፣ ቅድመ መወሰን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዶክትሪን ነው። ቁልፉ ቅድመ መወሰን ከመጽሐፍ ቅዱስ አኳያ ምን እንደሆን መረዳት ላይ ነው።

ከላይ “ቅድመ መወሰን” የሚሉት ቃላት በቅዱስ ቃሉ የተተረጎሙት የግሪክ ቃል proorizo ነው፣ እሱም የሚይዘው ትርጉም “ቀደም ብሎ መወሰን”፣ “ሥልጣናዊ ትእዛዝ፣” “ቀደም ባለው ጊዜ መወሰን” ማለት ነው። ስለዚህ፣ ቅድመ መወሰን ወይም ዕጣ ፈንታ እግዚአብሔር ከጊዜ በኋላ የሚሆኑትን አንዳንድ ነገሮች ሲወስን ነው። እግዚአብሔር ቀደም ብሎ ምን ወሰነ? እንደ ሮሜ 8፡29-30፣ እግዚአብሔር አንዳንድ ሰዎች የልጁን መልክ እንዲመስሉ ቀድሞ ወስኗል፣ የተጠሩ፣ የጸደቁ፣ እና የከበሩ እንዲሆኑ። በመሠረቱም፣ እግዚአብሔር የተወሰኑ ሰዎች እንዲድኑ ቀድሞ ወስኗል። በርካታ የቅዱስ ቃሉ ክፍሎች በክርስቶስ የሚያምኑ እንደተመረጡ ይጠቅሳሉ (ማቴዎስ 24:22, 31; ማርቆስ 13:20, 27; ሮሜ 8:33, 9:11, 11:5-7, 28; ኤፌሶን 1:11; ቆላስያስ 3:12; 1 ተሰሎንቄ 1:4; 1 ጢሞቴዎስ 5:21; 2 ጢሞቴዎስ 2:10; ቲቶ 1:1; 1 ጴጥሮስ 1:1-2, 2:9; 2 ጴጥሮስ 1:10)። ዕጣ ፈንታ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዶክትሪን ነው፣ እግዚአብሔር በሉዓላዊነቱ አንዳንድ ሰዎች እንዲድኑ መምረጡ።

በቅድመ መወሰን ዶክትሪን ላይ እጅግ የተለመደው ተቃውሞ ፍትሐዊ አለመሆኑ ነው። እግዚአብሔር አንዳንድ ሰዎችን ለምን ይመርጣል ሌሎቹን ትቶ? መታወስ ያለበት ጠቃሚ ነገር ማንም መዳን እንደማይገባው ነው። ሁላችን ኃጢአት ሠርተናል (ሮሜ 3፡23)፣ እናም ሁላችንም ዘላለማዊ ቅጣት ይገባናል (ሮሜ 6፡23)። በውጤቱም እግዚአብሔር ፈጽሞ ልክ ነው፣ ሁላችንም ዘላለማዊነትን በሲኦል እንድናሳልፍ ቢያደርግ። ሆኖም፣ እግዚአብሔር አንዳንዶቻችንን ሊያድን መረጠ። ባልተመረጡት ላይ ኢ-ፍትሐዊ እንደሆነ ተደርጎ መወሰድ የለበትም፣ ምክንያቱም የሚገባቸውን ስለ ተቀበሉ። የእግዚአብሔር ምርጫ አንዳንዶች እንዲከብሩ መደረጉ፣ ለሌሎች ኢ-ፍትሐዊ አይደለም። ማንም ከእግዚአብሔር ምንም ነገር አይገባውም፤ ስለዚህ፣ ማንም መቃወም አይችልም፣ ከእግዚአብሔር አንዳች ነገር ባይቀበል። አንድ ማስረጃ የሚሆነው፣ አንድ ሰው ለአምስት ሰዎች ገንዘብ ሲሰጥ ነው፣ ከሃያ ሰዎች መካከል። አስራ አምስቱ ሰዎች ገንዘቡን ያልተቀበሉት ቅር ይሰኛሉን? ሊሆን ይችላል። ቅር ለመሰኘት መብት አላቸውን? የለም፣ አይችሉም። ለምን? ምክንያቱም ሰውየው የማንም ሰው ዕዳ ስለሌለበት? እሱ እንዲያው ለአንዳንዶች ቸር ሊሆን ወሰነ።

እግዚአብሔር ማን እንደሚድን ከመረጠ፣ ያ የእኛን ነጻ ፍቃድ ዝቅ አያደርገውምን፣ ክርስቶስን እንድንመርጥና እንድናምን? መጽሐፍ ቅዱስ ምርጫ አለን ይላል— በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምኑ ሁሉ ይድናሉና (ዮሐንስ 3፡16፤ ሮሜ 10፡9-10)። መጽሐፍ ቅዱስ ፈጽሞ አይገልጽም፣ እግዚአብሔር በእርሱ የሚያምነውን እንደማይቀበል ወይም እሱን በሚፈልገው ላይ ፊቱን እንደሚያዞር (ዘዳግም 4፡29)። አንዳንዴ፣ በእግዚአብሔር ምሥጢር፣ ዕጣ ፈንታ እጅ ለእጅ ይሠራል ወደ እግዚአብሔር እንዲቀርብ በተደረገው ሰው ላይ (ዮሐንስ 6፡44) እና ለመዳን ማመን (ሮሜ 1፡16)። እግዚአብሔር ማን እንደሚድን ቀድሞ ይወስናል፣ እናም ለመዳን ክርስቶስን የግድ መምረጥ ይኖርብናል። ሁለቱም ሐቆች እኩል እውነት ናቸው። ሮሜ 11፡33 ያውጃል፣ “የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም!”

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ቅድመ መወሰን ምንድነው? ዕጣ ፈንታ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነውን?
© Copyright Got Questions Ministries