settings icon
share icon
ጥያቄ፤

በልሳን መጸለይ ምን ማለት ነው? በልሳን መጸለይ የጸሎት ቋንቋ ነውን፣ በአማኝና በእግዚአብሔር መካከል? በልሳን መጸለይ ራስን ለማነጽ ነውን?

መልስ፤


እባክዎን በልሳን የመናገር ስጦታ የሚለውን ጽሑፋችንን ያንብቡ። አራት ቀዳሚ የቅዱስ ቃሉ ምንባቦች አሉ፣ በልሳን ስለመጸለይ በማስረጃነት የሚጠቀሱ፡ ሮሜ 8፡26፤ 1 ቆሮንቶስ 14፡4-17፤ ኤፌሶን 6፡18፤ እና ይሁዳ ቁጥር 20። ኤፌሶን 6፡18፤ እና ይሁዳ ቁጥር 20 የሚጠቅሱት “በመንፈስ መጸለይ” ነው። ሆኖም፣ እንደ ጸሎት ቋንቋ የሆኑት ልሳናት “በመንፈስ መጸለይ” ለሚለው ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም አይደለም።

ሮሜ 8፡26 የሚያስተምረን፣ “እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል።” ሁለት ቁልፍ ነጥቦች ሮሜ 8፡26 ልሳናት የጸሎት ቋንቋ መሆኑን ለመጥቀሱ እጅግ አጠራጣሪ ያደርጉታል። የመጀመሪያው፣ ሮሜ 8፡26 የሚያስቀምጠው “የሚቃትተው” መንፈስ መሆኑን ነው፣ አማኞች ሳይሆኑ። ሁለተኛው፣ ሮሜ 8፡26 የሚያስቀምጠው የመንፈስ “መቃተት” “የማይገለጽ” መሆኑን ነው። በልሳን የመናገር ዋነኛው ነጥብ በንግግር/በድምጽ መግለጽ ነው።

ያም 1 ቆሮንቶስ 14፡4-17ላይ ይተወናል፣ በተለይም ቁጥር 14፡ “በልሳን ብጸልይ መንፈሴ ይጸልያል አእምሮዬ ግን ያለ ፍሬ ነው።” አንደኛ ቆሮንቶስ 14፡14 ስለ “ልሳን መጸለይ"ለይቶ ይጠቅሳል። ይህ ምን ማለት ነው? በመጀመሪያ፣ ዐውደ-ጽሑፉን ማጥናት እጅግ ጠቃሚ ነው። አንደኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ 14 በቀዳሚነት ማወዳደሪያ/ማነጻጸሪያ ነው፣ በልሳን የመናገር ስጦታን እና የትንቢት ስጦታን። ቁጥር 2-5 ግልጽ እንደሚያደርገው፣ ጳውሎስ ትንቢትን የሚያየው ከልሳን እንደሚበልጥ ስጦታ ነው። በተመሳሳይ ጊዜ፣ ጳውሎስ የልሳናትን ዋጋ/እሴት አጽንዖት ይሰጣል፣ እናም በይፋ እንደሚናገረው ከማንም ይልቅ በልሳን በመናገሩ ደስተኛነቱን ይገልጻል (ቁጥር 18)።

ሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2 የልሳን ስጦታን የመጀመሪያ ክስተት ይገልጻል። በበዓለ ሃምሳ ቀን ሐዋርያት በልሳናት ተናግረዋል። ሐዋ. ምዕራፍ 2 ግልጽ እንዳደረገው ሐዋርያት የተናገሩት በሰዎች ቋንቋ ነበር (ሐዋ. 2፡6-8)። “ልሳናት” የሚለው ቃል የተተረጎመው፣ በሁለቱም በሐዋ. ምዕራፍ 2 እና 1 ቆሮንቶስ ምዕራፍ 14 glossa (ግሎሳ) በሚል ሲሆን፣ ፍችውም “ቋንቋዎች” የሚል ነው። ከዚህ የቃል መልክ ነው፣ የዘመናዊውን እንግሊዝኛችን ቃል “ግሎሰሪ”ን ያገኘነው። በልሳን የመናገር ችሎታ ማለት፣ተናጋሪው በማያውቀው ቋንቋ መናገር ማለት ነው፣ ወንጌልን ያንን ቋንቋ ለሚናገር ሰው ለማስተላለፍ እንዲቻል።ብዝኃ-ባህል ያለው አካባቢ በሆነው ቆሮንቶስ፣ የልሳን ስጦታ በተለይ እጅግ ጠቃሚና ዓይነተኛ ይመስላል። የቆሮንቶስ አማኞች ወንጌልንና የእግዚአብሔርን ቃል በተሻለ ለማስተላለፍ ችለዋል፣ በልሳን ስጦታ ምክንያት። ሆኖም፣ ጳውሎስ እጅግ ግልጽ አድርጎታል፣ ማለትም በልሳን አጠቃቀም ላይ እንኳ ቢሆን፣ ሊፈታ ወይም “ሊተረጎም” እንደሚገባ ነው (1 ቆሮንቶስ 14፡13፣ 27)። የቆሮንቶስ አማኝ በልሳን ይናገር ነበር፣ የእግዚአብሔርን እውነት በማወጅ፣ ያንን ቋንቋ ለሚናገረው ለአንዱ፣ ከዚያም በኋላ ያ አማኝ፣ ወይም ሌለኛው አማኝ በቤተ-ክርስቲያን የተነገረውን ይተረጉማል፣ ሞላው ማኅበረ-ምዕመን ምን እንደተባለ ይረዳ ዘንድ።

እንግዲህ በልሳን መጸለይ ምን ማለት ነው፣ በልሳን ከመናገርስ በምን መልኩ ይለያል? አንደኛ ቆሮንቶስ 14፡13-17 በልሳን መጸለይ ደግሞ መተርጎም እንደሚኖርበትያመለክታል። በውጤቱም፣ በልሳን መጸለይ የሚመስለው ለእግዚአብሔር ጸሎት ማቅረብ ነው። ይህ ጸሎት ያንን ቋንቋ ለሚናገረው ሰው ይካሄዳል፣ ግን ደግሞ ሊተረጎም ይገባል፣ ሙሉው አካል ይታነጽ ዘንድ።

ይህ ትርጓሜ፣ በልሳን መጸለይን እንደ የጸሎት ቋንቋ አድርገው የመውሰድ አመለካከት ካላቸው ጋር አይስማማም። ይህን አማራጭ መረዳት በሚከተለው መልኩ ሊጠቃለል ትችላል፡ በልሳን መጸለይ ማለት ግላዊ የጸሎት ቋንቋ ነው፣ በአማኝ እና በእግዚአብሔር መካከል (1 ቆሮንቶስ 13፡1) ማለትም አማኙ ራሱን ለማነጽ የሚጠቀምበት (1 ቆሮንቶስ 14፡4)። ይህ ትርጓሜ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም፣ በሚከተሉት ምክንያቶች፡ 1) በልሳን መጸለይ እንዴት አድርጎ ግላዊ የጸሎት ቋንቋ ሊሆን ይችላል፣ የሚተረጎም ከሆነ (1 ቆሮንቶስ 14፡13-17)? 2) በልሳን መጸለይ እንዴት ለራስ ማነጫ ይሆናል፣ ቅዱስ ቃሉ መንፈሳዊ ስጦታዎች ለቤተ-ክርስቲያን ማነጫ ናቸው እያለ፣ ለግል ሳይሆን (1 ቆሮንቶስ 12፡7)? 3) በልሳን መጸለይ እንዴት የግል ጸሎት ቋንቋ ሊሆን ይችላል፣ የልሳን ስጦታ “ለማያምኑ ምልክት” ከሆነ (1 ቆሮንቶስ 14፡22)? 4) መጽሐፍ ቅዱስ ግልጽ አድርጎታል፣ እያንዳንዱ የልሳን ስጦታ እንደማይኖረው (1 ቆሮንቶስ 12፡11፣ 28-30)። ልሳናት እንዴት ራስን የማነጽ ስጦታ ይሆናሉ፣ እንዲያ ካልሆነ እያንዳንዱ አማኝ ሊኖረው ይችላልን? ሁላችንም መታነጽ አያስፈልገንምን?

አንዳንዶች በልሳን መጸለይን “የምሥጢራዊ ቋንቋ መክፈቻ/ኮድ” እንደሆነ ይረዳሉ፣ ይኸውም ሰይጣንና አጋንንቱ ጸሎታችንን ከመረዳት የሚከለከሉበት፣ በእኛ ላይ ፈንታ እንዳያገኙብን። ይህ ትርጓሜ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም፣ በሚከተሉት ምክንያቶች፡ 1) መጽሐፍ ቅዱስ ስልታዊ በሆነ መልኩ እንደሚገልጸው ልሳናት የሰው ቋንቋ መሆኑን ነው፣ እናም ሰይጣንና አጋንንቱ የሰው ልጆችን ቋንቋ በተገቢው መረዳትይችላሉ። 2) መጽሐፍ ቅዱስ ቁጥር የሌላቸው አማኞች በገዛ ራሳቸው ቋንቋ መጸለያቸውን አስፍሯል፣ ጮክ ብለው፣ ሰይጣን ጸሎትን ይተረጉመዋል የሚል ስጋት ሳያድርባቸው። ምንም እንኳ ሰይጣን እና/ወይም አጋንንቱ የምንጸልየውን ጸሎት ቢሰሙና ቢረዱትም፣ እነርሱ እንደ ፍቃዱ ለሆነ ጸሎታችን እግዚአብሔር ምላሽ እንዳይሰጠን ለማከላከል ፈጽሞ ኃይል የላቸውም። እግዚአብሔር ጸሎታችንን እንደሚሰማን እናውቃለን፣ እናም ያ ሐቅ ሰይጣን እና አጋንንቱ ጸሎታችንን መስማታቸውንና መረዳታቸውን ዋጋ-ቢስ አድርጎታል።

እንግዲህ ምን እንላለን፣ በርካታ ክርስቲያኖች እነርሱም በልሳን መጸለይን ስለሚለማመዱ፣ እንዲሁም እጅግ በግላዊ የሚያንጽ መሆኑን ስለሚቆጥሩት? በመጀመሪያ፣ እምነታችንንና ድርጊታችንን መመሥረት ያለብን በቅዱስ ቃሉ ላይ መሆን አለበት፣ በልምድ ላይ ሳይሆን። ልምምዶቻችንን በቅዱስ ቃሉ ብርሃን መመልከት አለብን፣ ቅዱስ ቃሉን በልምምዶቻችን መተርጎም ሳይሆን። ሁለተኛ፣ አብዛኞቹ የሐሰት አምልኮቶች እና የዓለም ሃይማኖቶች ደግሞ በልሳን የመናገር/በልሳን የመጸለይ ክስተቶች እንዳጋጠሟቸው ገልጸዋል። በግልጽ እንደሚታወቀው መንፈስ ቅዱስ ለእነዚህ የማያምኑ ግለሰቦች ስጦታ አይሰጥም። ስለዚህ፣ አጋንንት በልሳን የመናገርን ስጦታ የኮረዡ ይመስላል። ይህም ልምምዶቻችንን በቅዱስ ቃሉ በጥንቃቄ እንድናስተያይ ምክንያት ይሆነናል። ሦስተኛ፣ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በልሳን መናገር/መጸለይ እንዴት አድርጎ የምንማረው ባሕርይ ሊሆን እንደሚችል ነው። ሌሎች በልሳን ሲናገሩ በመስማት እና በማስተዋል፣ አንድ ግለሰብ ደንቡን/አገባቡን ሊማር ይችላል፣ በውስጠ-ሕሊናው እንኳ ሆኖ። ይህ እጅግ ሊሆን የሚችል ገለጻ ነው፣ ለሰፋና ለአብዛኛው ገጠመኞች፣ በክርስቲያኖች መካከል በልሳን ስለመናገር/መጸለይ። አራተኛ፣ “ራስን የማነጽ” ስሜት ተፈጥሯዊ ነው። የሰው አካል አድሬናሊን እና ኢንዶርፊንስን (ሆርሞኖች) ያመርታል፣ አዲስ ነገር፣ አስደሳች፣ ስሜታዊ እና/ወይም ምክንያታዊ ከሆነ ሐሳብ ጋር የሚያለያይ ልምምድ ሲያጋጥመው።

በልሳን መጸለይ ክርስቲያኖች በመከባበር እና በመፈቃቀር ላለመስማማት የሚስማሙበት ያለምንም ጥያቄ የሚያዝ ጉዳይ መሆን ይኖርበታል። ድኅነታችንን (መዳን) የሚወስነው በልሳን መጸለይ አይደለም። በልሳን መጸለይ የበሰለ ክርስቲያንን ካልበሰለ ክርስቲያን የሚለይ አይደለም። እንደዚህ ዓይነት ነገር ማለትም በልሳን መጸለይ እንደ ግላዊ የጸሎት ቋንቋ ቢኖርም ባይኖርም ለክርስቲያን እምነት መሠረታዊ አይደለም። ስለዚህ፣ በልሳን የመጸለይን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጓሜ ስናምን፣ ከግል የጸሎት ቋንቋ፣ ራስን ለማነጽ ከሚለው ሐሳብ እንደሚያርቀን ሁሉ፣ አብዛኞቹ በዚህ ልምምድ ውስጥ ያሉትን በክርስቶስ ወንድሞቻችንንና እኅቶቻችንን እውቅና እንሰጣቸዋለን፣ እናም የእኛ ፍቅር እና ክብር ይገባቸዋል።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

በልሳን መጸለይ ምን ማለት ነው? በልሳን መጸለይ የጸሎት ቋንቋ ነውን፣ በአማኝና በእግዚአብሔር መካከል? በልሳን መጸለይ ራስን ለማነጽ ነውን?
© Copyright Got Questions Ministries