settings icon
share icon
ጥያቄ፤

በኢየሱስ ስም መጸለይ ምን ማለት ነው?

መልስ፤


በኢየሱስ ስም ስለ መጸለይ ዮሐንስ 14፡13-14 ላይ ተስተምሯል፣ “አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ። ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።” አንዳንዶች ይህንን ቁጥር አላግባብ ይጠቀሙበታል፣ “በኢየሱስ ስም” ከጸሎታቸው መጨረሻ ማለት፣ እግዚአብሔር የተጠየቀውን ሁሉ እንደሚቀበል በማሰብ። ይህ እንዲያውም “በኢየሱስ ስም” የሚለውን ቃል እንደ አስማት ቀመር መውሰድ ነው። ይህ ፈጽሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም።

በኢየሱስ ስም መጸለይ ማለት፣ በእርሱ ሥልጣን መጸለይና እግዚአብሔር አብን መለመን ነው፣ ለጸሎታችን ምላሽ እንዲሰጥ፣ ምክንያቱም በልጁ በኢየሱስ ስም ስለ መጣን። በኢየሱስ ስም መጸለይ ማለት እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ መጸለይ ማለት ነው፣ “በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል። የምንለምነውንም ሁሉ እንዲሰማልን ብናውቅ ከእርሱ የለመነውን ልመና እንደ ተቀበልን እናውቃለን።” (1 ዮሐንስ 5፡14-15)። በኢየሱስ ስም መጸለይ ማለት፣ ኢየሱስን ስለሚያስከብሩና ከፍ ከፍ ስለሚያደርጉ ነገሮች መጸለይ ማለት ነው።

በጸሎት መጨረሻ ላይ “በኢየሱስ ስም” ማለት የአስማት ቀመር አይደለም። የምንለምነው ወይም በጸሎት የምንለው ለእግዚአብሔር ክብር ካልሆነና እንደ ፍቃዱ ካልሆነ፣ “በኢየሱስ ስም” ማለት ዋጋ የለውም። በኢየሱስ ስም እና ለእርሱ ክብር በቅንነት መጸለይ ላይ ጠቃሚ የሚሆነው፣ የሆኑ ቃላትን በጸሎት መጨረሻ ማያያዝ አይደለም። ቁም ነገሩ በጸሎት ላይ ያሉት ቃላት አይደሉም፣ ነገር ግን ከጸሎቱ ጀርባ ያለው ዓላማ እንጂ ነው። ከእግዚአብሔር ፍቃድ ጋር ስለሚስማሙ ነገሮች መጸለይ፣ በኢየሱስ ስም የመጸለይ ዋነኛ ነገር ነው።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

በኢየሱስ ስም መጸለይ ምን ማለት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries