settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፖርኖግራፊ ምን ይላል? ፖርኖግራፊ መመልከት ኃጢአት ነውን?

መልስ፤


ባብዛኛው፣ በኢንተርኔት እጅግ የሚፈለገው ነገር ከፖርኖግራፊ ጋር ይያያዛል። ፖርኖግራፊ አሁን በዓለም እየበጠበጠ ነው። ምናልባትም ከምንም ነገር በላይ፣ ሰይጣን ወሲብን እየጠመዘዘውና እያበላሸው ነው። እሱ መልካሙንና ተገቢ የሆነውን ወስዶ (በባልና ሚስት መካከል የሚደረግ የፍቅር ግንኙነት) በምትኩ በሴሰኝነት፣ በአስጸያፊ ምስል፣ በዝሙት፣ በአስገድዶ መድፈር፣ እና በግብረ-ሰዶማዊነት ቀየረው። ፖርኖግራፊ የመጀመሪያው ደረጃ ሊሆን ይችላል፣ የቁልቁለታማ ዳጡ እየጨመረ ያለው ኃጢአተኝነትና የሞራል ውድቀት (ሮሜ 6፡19)። የፖርኖግራፊ ሱሳዊ ባሕርይ በጥናት ተረጋግጧል። አደንዛዥ ዕጽ ተጠቃሚ ትልቁንና ኃይለኛውን የአደንዛዥ ዕጽ መጠን እንደሚጠቀም፣ “ከፍ” ያለውን ርካታ ለማግኘት፣ ፖርኖግራፊም ግለሰቡን ይጎትተዋል፣ የጥልቅ ጥልቅ ወደ ሆነ ጽኑ ወሲባዊ ሱስ እና መልካም ወደ አልሆነ ፍላጎት።

ሥስቱ ዋነኛ የኃጢአት ምድቦች የሥጋ አምሮት፣ የዓይን አምሮት፣ እና የሕይወት ኩራት ናቸው (1 ዮሐንስ 2፡16)። ፖርኖግራፊ በትክክል የሥጋ ፍላጎት እንዲያድርብን ምክንያት ይሆናል፣ እሱም በማይካድ ሁኔታ የዓይን አምሮት ነው። ፖርኖግራፊ በትክክል ሊያበቃን አይችልም፣ ማሰብ ስላሉብን ነገሮች፣ እንደ ፊሊጵስዩስ 4፡8። ፖርኖግራፊ ሱስ ነው (1 ቆሮንቶስ 6፡12፤ 2 ጴጥሮስ 2፡19)፣ እንዲሁም አጥፊ ነው (ምሳሌ 6:25-28፤ ሕዝቅኤል 20:30፤ ኤፌሶን 4:19)። በሐሳባችን በሌሎች ሰዎች ኋላ መሴሰን፣ ይኽውም የፖርኖግራፊ ይዘት የሆነ፣ እግዚአብሔርን ያስቀይመዋል (ማቴዎስ 5፡28)። ልማዳዊ የፖርኖግራፊ መሰጠት የሰውየውን ሕይወት ሲይዘው፣ ሰውየው እንዳልዳነ አመላካች ነው (1 ቆሮንቶስ 6፡9)።

በፖርኖግራፊ ለተያዙት እግዚአብሔር ድልን ሊሰጥ ይችላል፣ ፍቃዱም ነው። በፖርኖግራፊ ተይዘሃልን፣ ከእሱም ነጻነትን ትሻለህን? ለድሉ አንዳንድ ርምጃዎች እነሆ፡ 1) ኃጢአትህን ለእግዚአብሔር ተናዘዝ (1 ዮሐንስ 1፡9)፣ 2) እግዚአብሔር እንዲያነጻህ፣ እንዲያድስህ፣ እንዲሁም አእምሮህን እንዲለውጥ ጠይቀው (ሮሜ 12፡2)። 3) እግዚአብሔርን ለምነው፣ አእምሮህን በፊሊጵስዩስ 4፡8 እንዲሞላ። 4) አካልህን በቅድስና መያዝን ተማር (1 ተሰሎንቄ 4፡3-4)። 5) የወሲብን ትክክለኛ ፍቺ ተረዳ፣ እናም ከትዳር አጋርህ ጋር ብቻ ያንን መሻት ፈጽም (1ቆሮንቶስ 7፡1-5)። 6) ይሄንን ተረዳ በመንፈስ ከተራመድክ የሥጋን መሻት አትፈጽምም (ገላትያ 5፡16)። 7) ተግባራዊ ርምጃ ውሰድ፣ ለጎጂ ምስሎች የመጋለጥህን ዕድል ለመቀነስ። የፖርኖግራፊ ገደቦችን በኮምፒውተርህ ላይ አድርግ፣ የቴሌቪዥንና የቪዲዮ አጠቃቀምህን ገድብ፣ እንዲሁም ሌላ ክርስቲያን ፈልግ የሚጸልይልህና ንቁ እንድትሆን የሚረዳህ።

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፖርኖግራፊ ምን ይላል? ፖርኖግራፊ መመልከት ኃጢአት ነውን?
© Copyright Got Questions Ministries