settings icon
share icon
ጥያቄ፤

በተደራጀ ሃይማኖት ለምን አምናለሁ?

መልስ፤


የ“ሃይማኖት” መዝገበ-ቃላታዊ ፍች የሚመሳሰለው “በእግዚአብሔር ወይም በጣዖት ማመን ነው፣ ለማምለክ፣ ዘወትር የሚገለጸውም በጠባይና በአምልኮ ሥርዓት ነው፤ ማንኛውም ዓይነት የተለየ የአምነት፣ የአምልኮ ሥርዓት ወዘተ… ዘወትርም የሥነ-ምግባር ሕግጋትን ያካትታል።” በዚህ ማብራሪያ መሠረት መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ተደራጀ ሃይማኖት ይናገራል፣ ነገር ግን በብዙ ምክንያቶች “የተደራጀ ሃይማኖት” ዓላማና አንድምታ እግዚአብሔር ደስ የሚሰኝበት አይደለም።

በዘፍጥረት ምዕራፍ 11፣ ምናልባትም የተደራጀ ሃይማኖት የመጀመሪያው አጋጣሚ፣ የኖኅ ዝርዮች ራሳቸውን አደራጅተው የባብኤል ግንብን ገነቡ፣ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ከማክበር ይልቅ፣ ሞላው ዓለምን ለመሙላት። እነሱም ያመኑት ኅብረታቸው እጅግ ጠቃሚ መሆኑን ነው፣ ከእግዚአብሔር ጋር ካላቸው ግንኙነት ይልቅ። እግዚአብሔር ጣልቃ ገብቶ ቋንቋቸውን አደበላለቀ፣ እናም የተደራጀ ሃይማኖታቸውን አፈረሰ።

በዘጸአት ምዕራፍ 6 እና በቀጣዩ፣ እግዚአብሔር ሃይማኖትን “አደራጀ” ለእስራኤል ሕዝቦች። አስርቱ ትዕዛዛት፣ መቅደሱን የሚመለከቱ ሕግጋት፣ እና የመሥዋዕት ሥርዓቱ ሁሉ የተቋቋሙት በአግዚአብሔር ሲሆን፣ እስራኤላውያን የሚከተሏቸው ናቸው። በአዲስ ኪዳን ላይ የተደረገ ተጨማሪ ጥናት ግልጽ እንደሚያደርገው፣ የሃይማኖቱ ቁም-ነገር አዳኝ መሲህ ማስፈለጉን ለማመልከት ነው (ገላትያ 3፤ ሮሜ 7)። ሆኖም፣ ብዙዎች ይሄንን በስሕተት ተረድተውታል፣ እናም ሕግጋቱንና የአምልኮ ሥርዓቱን ያመልካሉ፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ።

በእስራኤል ታሪክ ሁሉ፣ አብዛኞቹ በእስራኤላውያን የተካሄዱት ግጭቶች፣ በተደራጁ ሃይማኖቶች ሳቢያ የተካሄዱ ግጭቶች ናቸው። ከሚያካትቱት ምሳሌዎችም የበአል አምልኮ (መሳፍንት 6፤ 1 ነገሥት 18)፣ ዳጎን (1 ሳሙኤል 5)፣ እና ሞሎክ (2 ነገሥት 23፡10)። እግዚአብሔር የእነዚህን ሃይማኖት ተከታዮች አሸነፈ፣ ሉዓላዊነቱንና ሁሉን አድራጊነቱን እያሳየ።

በወንጌላት ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን በክርስቶስ ጊዜ የነበረውን የተደራጀ ሃይማኖት ወክለው ያመላክታሉ። ኢየሱስ ባለማቋረጥ ተቃውሟቸው ነበር፣ ስለ ስሕተት ትምህርታቸውና ስለ ግብዝ የሕይወት ስልታቸው። በመልእክቶች የተደራጁ ወገኖች ነበሩ፣ እነርሱም ወንጌልን ከተወሰኑ አስፈላጊ ሥራዎችና የአምልኮ ሥርዓት ዝርዝር ጋር የቀላቀሉ። እነሱ ደግሞ በአማኞች ላይ ግፊት ያደርጉ ነበር፣ እንዲለወጡና እነዚህን “የክርስትና ተደማሪ” ሃይማኖቶችን እንዲቀበሉ። ገላትያና ቆላስያስ ስለ እንዲህ ዓይነት ሃይማኖቶች ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። በራዕይ መጽሐፍ የተደራጀ ሃይማኖት በዓለም ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል፣ የክርስቶስ ተቃዋሚ አንድ የዓለም ሃይማኖት እንደሚያደራጅ ሁሉ።

በብዙ ጉዳዮች፣ የተደራጀ ሃይማኖት የመጨረሻ ፍጻሜው ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ ጥፋት ነው። ሆኖም፣ መጽሐፍ ቅዱስ የእሱ ዕቅድ ስለሆኑት የተደራጁ አማኞች አይናገርም። እግዚአብሔር እነዚህን የተደራጁ አማኝ ወገኖች “አብያተ-ክርስቲያናት” በማለት ይጠራቸዋል። ከሐዋርያት ሥራ መጽሐፍና ከመልእክቶች የተገኘው ገለጻ የሚያመለክተው ቤተ-ክርስቲያን ተደራጅታ ትደጋገፋለች። አደረጃጀቱ ወደ መከላከል፣ ውጤታማነት፣ እና ወደ መድረስ ያመራል (ሐዋርያት ሥራ 2:41-47)። ቤተ-ክርስቲያንን በተመለከተ፣ “የተደራጀ ግንኙነት” ተብሎ ቢጠራ ይሻላል።

ሃይማኖት ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት ለማድረግ የሰው ሙከራ ነው። የክርስቲያን እምነት ከእግዚአብሔር ጋር የሚደረግ ግንኙነት ነው፣ እሱ ለሁላችን ባደረገው በኢየሱስ ክርስቶስ መሥዋዕትነት በኩል። ወደ እግዚአብሔር ለመድረስ ዕቅድ የለም (እሱ ወደ እኛ ስለ ደረሰ— ሮሜ 5፡8)። ትምክህት የለም (ሁሉም በጸጋ ይቀበላሉ— ኤፌሶን 2፡8-9)። ለሥልጣን ግጭት አያስፈልግም (ክርስቶስ ራስ ነው— ቆላስይስ 1፡18)። ምንም ቀዳሚ-ፍርድ የለም (ሁላችንም በክርስቶስ አንድ ነን— ገላትያ 3፡28)። የተደራጁ መሆን ችግር የለውም። በሕግጋትና በሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ላይ ማተኮር ነው ችግሩ።

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

በተደራጀ ሃይማኖት ለምን አምናለሁ?
© Copyright Got Questions Ministries