settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ክርስቲያኖች የሚኖሩባትን ምድር ህግ መታዘዝ ነበረባቸው?

መልስ፤


መልስ ሮሜ 13፡1-7 ሲናገር ‹‹ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ።ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው።ስለዚህ ባለ ሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማል፤ የሚቃወሙትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ይቀበላሉ።ስለዚህ ስለ ቍጣው ብቻ አይደለም ነገር ግን ስለ ሕሊና ደግሞ መገዛት ግድ ነው።ስለዚህ ደግሞ ትገብራላችሁና፤ በዚህ ነገር የሚተጉ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸውና።ለሁሉ የሚገባውን አስረክቡ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን፥ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን፥ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፥ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ።››

ይህ ክፍል በግልጽ እንደሚናገረው እግዚአብሔር በእኛ ላይ ያስቀመጠውን መንግስት መታዘዝ አለብን፡፡ እግዚአብሔር መንግስታት ህግን እንዲመሰርቱ ስርዓትን እንዲያነግሱ ክፉውን እንዲቀጡ ፍትህን እንዲያደርጉ አቁሞአቸዋል(ዘፍ 9:6; 1 ቆሮ 14:33; ሮሜ 12:8). በሁሉም መንግስትን ልንታዘዝ ታክስ በመክፈል ህግ እና ስረአትን በማክበር አክበሮት ልናሳይ ይገባናል፡፡ ይህን ባናደርግ የማናከብረው እግዚአብሔርን ነው ምክንያቱም መንግስታትን በእኛ ላይ ያስቀመጠው እርሱ ነው፡፡ ጳውሎስ ለሮማዊያን ሲጽፍላቸው በኔር ዘመን በሮማውያን እጅ ነበር ይህ ሰው በሮማ ከነበሩ ገዢዎች ሁሉ የከፋ ነበር፡፡ ጳውሎስ በዚህ ውስጥ ለሮማ መንግስት ያለውን መገዛት ያሳያል፡፡ እኛስ ከዚህ ውጪ ምን ልናደርግ እንችላለን?

የሚከትለው ጥያቄ ‹‹በመድር ላይ የሚኖረውን ህግ መታዘዝ የማይኖርብን ጊዜ ይኖራል;›› የዚህ ጥያቄ መልስ ምናልባት የሚገኘው በሥራ 5፡27-29 ‹‹አምጥተውም በሸንጎ አቆሙአቸው።ሊቀ ካህናቱም። በዚህ ስም እንዳታስተምሩ አጥብቀን አላዘዝናችሁምን?እነሆም፥ ኢየሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞልታችኋል፤ የዚያንም ሰው ደም በእኛ ታመጡብን ዘንድ ታስባላችሁ ብሎ ጠየቃቸው።

ጴጥሮስና ሐዋርያትም መልሰው አሉ። ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል።›› ከዚህ የምናየው የመድር ህግ የእግዚአብሔርን ህግ እስካልተቃወመ ድረስ የመድሪቱን ህግ ለመታዘዝ እንገደዳለን፡፡ የምድሪቱ ህግ የእግዚአብሔርን ህግ በተቃወመ ጊዜ ግን የምድሪቱን ህገ በመቃወም የእግዚአብሔርን ህግ እንፈጽማለን፡፡ ሆኖም በዚያን ጊዜም የምድሬቱን መንግስት ህግ የሚያዝብንን እንቀበላለን፡፡ ይህ ተግልጾልናል ጴጥሮስና ዮሐንስ ታስረው በተገረፉ ጊዜ እግዚአብሔርን በመታዘዛቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ እንጂ አልተቃወሙም(ሥራ 5:40-42).

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ክርስቲያኖች የሚኖሩባትን ምድር ህግ መታዘዝ ነበረባቸው? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries