settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያን በጦር ሠራዊት አባል ሆኖ ስለመስራት ምን ይላል?

መልስ፤


መጽሐፍ የጦር ሠራዊት አባል ሆኖ ስለማገልገል የሚነገረው ብዙ ነገር አለ፡፡ አብዛኛዎቹ ስለ ጦር ስራዊት የሚናገራቸው ተመሳሳይ ናቸው፤ አብዛኛዎቹ ከዚህ ጥያቄ ጋር የሚስማሙ ናቸው፡፡ መጸሐፍ ቅዱስ ቃል በቃል በጦር ሠራዊት መገልገልን ወይም አለማገልገልን አያስቀምጥም፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ክርስቲያን ወታደር መሆን በመጽሐፍ ቅዱስ በከፍተኛ ሁኔታ የተከበረ እንደ ሆነ በአለም አቀፍ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አመለካከት የሚታመንበት እንደሆነ እርግጠኛ መሆን ይችላሉ፡፡

ሌላው የመጀመሪያው የጦር ሠራዊት አገልግሎት ምሳሌ የሚገኘው በብሉይ ኪዳን ነው (ዘፍ 14) የአብርሃም የአጎት ልጅ ሎጥ በኤላም ንጉሥ በኮሎዶጎምርተማርኮ ነበር፤ የኤላም ንጉሥ እና የእርሱ አጋሮች፤ አብርሃም ሎጥን ለማገዝ 318 የሰለጠኑ የቤቱን ሰዎች ይዞ በመሄድ ኢልማዩትን አሸነፈ፡፡ እዚህ ጋር የምናየው የታጠቁ ኃይሎች አስፈላጊ በሆነ ተልዕኮ ተጠምደው ንጹሃንን ሲታደጉ ሲጠብቁ እናያለን፡፡

በታሪክ የእስራኤል ህዝብ ሠራዊት ለማቆም ዘግይተው ነበር፡፡ እስራኤላዊያን የጦር ሠራዊትን በሚመለከት ያላቸው ጥንካሬ ለመሳደግ የዘገዩ እንዲሆኑ ያደረጋቸው ምናልባት እግዚአብሔር መለኮታዊ ተዋጊ እንደሆነ እና ህዝቡን እንደሚጠብቅ ያላቸው መረዳት ነው፡፡ የእስራኢላውያን የተደራጀ ቋሚ የጦር ሠራዊት የመጣው ጠንካራ የተደራጀ የፖለቲካ ስርዓት በሳኦል በዳዊት እና በሰለሞን ከተዘረጋ በኋላ ነበር፡፡ ሳኦል ነበር የመጀመሪያውን የጦር ሠራዎት ያቋቋመው፡፡ (1 ሳሙ 13:2; 24:2; 26:2).

ሳኦል የጀመረውን ዳዊት ቀጠለበት፤ የጦር ሠራዊቱን አበዛ፤ በዙዎች ለእርሱ የታመኑትን ከሌሎች ግዛት አምጥቶ ቀጠረ (2ኛ ሳሙ 15፡19-22) አመራሩንም የጦሩ አለቃ ለሆነው ለኢዮአብ አዞረው፡፡ በዳዊት አመራር ስር በጦር ፖለቲካዋ ጠንካራ እየሆነች መጣች፤ አምኖንን የመሰሉ የተዋሃዱ ወዳጆች ነበሩት(2 ሳሙ 11:1; 1 ዜና 20:1-3):: ዳዊት 12 ቡድን ያለው የሚዞር ስርዓት 24000 ሰዎች በዓመቱ ውስጥ አንዱን ወር የሚያገለግሉት አደራጀ፡፡ (1ዜና 27)፡፡ የሰለሞን ንግስና የሰላም ነበር እረሱም ጦሩን አስፋፋው ሰረገሎችንና ፈረሰኞችን ጨመረበት፡፡ (1 ነገ 10:26)፡፡ ይህ የተደራጀው ሠራዊት (ግን ከሰለሞን ሞት በኋላ ከመንግስቱ ጋራ ተከፈለ) እስከ 586 ከክርስቶስ ልደት በፊት እስራኤል በአንድ የፖለቲካ ማዕቀፍ መቆም እስካቃተቸው ጊዜ ድረስ፡፡

በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ በሮማዊው በመቶ አለቃ አክብሮት ተደነቀ፡፡ የመቶ አለቃው ስለ ሥልጣን ያለውን ግልጽ መረዳት እንዲሁም በኢየሱስ ላይ ስላለው እምንነት ነገረው (ማቲ 8:5-13). ኢየሱስ ክርስቶስ ስራውን አልተቃወመውም፡፡ ብዙ ወታደሮች በአዲስ ኪዳን የተመሰገኑ ክርስቲያኖች እግዚአብሔርን የሚፈሩ መልካም ባህሪ ያላቸው ሆነው ተጠቅሰዋል፡፡ (ማቲ 8:5; 27:54; ማር 15:39-45; ሉቃ 7:2; 23:47; ሥራ 10:1; 21:32; 28:16).

ቦታውና ርዕሱ ሊቀየር ይችላል ግን የእኛም የታጠቀው ኃይል ልክ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደምናያቸው የተከበሩ መሆን አለባቸው፡፡ የወታደሮች ስልጣን የተከበረ ነበር፡፡ ለምሳሌ ጳውሎስ አፍሮዲጦስን ይጠቅሳል፤ ክርስቲያን ጌታን የሚከተል ወታደር “fellow soldier” (ፊሊ 2:25). መስሐፍ ቅዱስም ወታደራዊ መግለጫዎችን በጌታ የበረታን መሆንን ለመግለጽ መንፈሳዊ የጦር ዕቃዎችን የወታደርን ጦር ዕቃዎች በመጥቀስ ያራስ ቁር የደረት ጥሩር ሰይፍን ጨምር ልበሱ ይላል፡፡ (ኤፌ 6:10-20)

አዎን መጽሐፍ ቅዱስ በውትድርና ስለማገልገል በቀጥታ ወይንም በተዘዋዋሪ ይናገራል፡፡ ክርስቲያን የሆኑ ወንድና ሴቶች አገራቸውን በመልካም ባሕሪ በክብር ለራሳቸው ጥሩ አመለካከት ኖሮአቸውና እና በክብር የሚያገለግሉ እርግጠኛ መሆን የምንችለው ለህዝባቸው የሚሰጡት አገልግሎት እግዚአብሔር የሚያየው እና የተከበረ ነው፡፡ በክብር በውትድርና ወስጥ የሚያገለግሉ አክብሮት እና ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያን በጦር ሠራዊት አባል ሆኖ ስለመስራት ምን ይላል? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries