settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ገንዘብ አያያዛችን ምን ይላል?

መልስ፤


መጽሐፍ ቅዱስ ገንዘብን ስለማስተዳደር ብዙ የሚለው ነገር አለው፡፡ ገንዘብን ስለ መበደር መጽሐፍ ቅዱስ በተቃራኒው ይመከራል፡፡ ምሳ 6:1-5; 20:16; 22:7, 26-27 እንመልከት፡፡ (‹‹ባለጠጋ ድሆችን ይገዛል፥ ተበዳሪም የአበዳሪ ባሪያ ነው። እጃቸውን አጋና እንደሚማቱ፥ ለባለ ዕዳዎች እንደሚዋሱ አትሁን የመትከፍለው ባይኖርህ ምንጣፍህን ከበታችህ ስለ መን ይወስዳል?)

በመደጋገም ለባለጠግነት እንዳናከማች እስጠንቅቆአል፤ መንፈሳዊን ሃብት በእርሱ ፈንታ እንድናከማች ነግሮናል፡፡ ምሳ 28፡20 ‹‹ የታመነ ሰው እጅግ ይባረካል ባለጠጋ ለመሆን የሚቸኵል ግን ሳይቀጣ አይቀርም።›› ምሳሌ 10:15; 11:4; 18:11; 23:5. ተመልከቱ፡፡

ሌላው ምሳ 6፡6-11 ታካችነት እና አባካኝነት ለሚያስከትለው ጥፋት ጥበብን ያቀርብልናል፡፡ ጉንዳኖች እንዴት ምግባቸውን ለራሳቸው እነደሚያከመቹ ይነግረናል፡፡ ክፍሉ መስራት እና መጠቀም እያለብን መተኛትን በመቃወም ያስጠነቅቃል፤ መጨረሻው በትክክል ድህነት እና ችጋር ነው፡፡ በሌላው ጥግ ደግሞ ያለው በገንዘብ ፍቅር የነሆለለ ሰው ነው፡፡ እንደ መክ 5፡10 እንዳለው ሰው ምንም አይነት የሚያረካው ሃብት ሊሰበስብ አይችልም ሁልጊዜም ጨምሮ ጨምሮ መሰብሰብ አለበት፡፡ 1ጢሞ 6፡6-11 ባለጠግነት መፈለግ ስላለው ወጥመድ ያስጠነቅቃል፡፡

ለራሳችን ባለጥግነት ለማከማቸት ከመፈለግ ይልቅ መጽሐፍ ቅዱሳዊው መመሪያ መቀበል ሳይሆን መስጠት ነው፡፡ ‹‹በጥቂት የሚዘራ በጥቂት ደግሞ ያጭዳል፥ በበረከትም የሚዘራ በበረከት ደግሞ ያጭዳል።እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም።›› (2 ቆሮ 9:6-7). እግዚአብሔር ለሰጠን ነገር መልካም ባለአደራዎች እንድንሆን ተነግሮናል፡፡ በሉቃ 16፡1-13 ኢየሱሰስ ታማኝነት ስለጎደለው ባለአደራነት ምሳሌ በመናገር ሰነፍ ባለአደራዎችን ያስጠነቅቃል፡፡ የታሪኩ ስርዓት ትምህርት ቁ.11 ‹‹እንግዲያስ በዓመፃ ገንዘብ ካልታመናችሁ፥ እውነተኛውን ገንዘብ ማን አደራ ይሰጣችኋል?›› ነው፡፡ ለቤተሰቦቻችን የሚያስፈልጋቸውን ለማዘጋጀት ኃላፊነት እንዳለብን ያስጠነቅቃል 1ጢሞ 5፡8 ‹‹ነገር ግን ለእርሱ ስለ ሆኑት ይልቁንም ስለ ቤተ ሰዎቹ የማያስብ ማንም ቢሆን፥ ሃይማኖትን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው።››

በማጠቃለያ መጸሐፍ ቅዱስ ገንዘብን ስለማስተዳደር ምን ይላል? መልሱ ጥበብ በሚል አንድ ቃል ሊጠቃለል ይችላል፡፡ በገንዘበችን ጥበበኞች መሆን አለብን፡፡ ገንዘብ ማስቀመጥ አለብን ግን ማከማቸት አይደለም፡፡ ገንዘብን መጠቀም አለብን በአግባቡ እና በመቆጣጠር መሆን አለብት፡፡ ለእግዚአብሔር በደስታ እና በመስዋዕትነት ለእግዚአብሔር መልሰን መስጠት አለብን፡፡ በገንዘባችን ሌሎችን መርዳት አለብን ነገር ግን መንፈስን በመመርመር እና በእግዚአብሔር ምሪት መሆን አለበት፡፡ ሃብታም መሆን ስህተት አይደለም ገንዘብ መውደድ ስህተት ነው፡፡ ድሃ መሆን ስህተት አይደለም በማያስፈልጉ ነገሮች ገንዘብ ማባከን ስህተት ነው፡፡ ገንዘብን በሚመለከት የመጽሐፍ ቅዱስ መልዕክት ጥበበኛ መሆን የሚል ነው፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ገንዘብ አያያዛችን ምን ይላል? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries