settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ጥንዶቹ ከጋብቻ በፊት አንድ ላይ መኖራቸው ስሕተት ነውን?

መልስ፤


የዚህ ጥያቄ መልስ የሚወሰነው “አብሮ መኖር” የሚለውን እንዴት እንደምንረዳው ነው። እሱ ማለት የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ማድረግ ከሆነ፣ በርግጥ ስሕተት ነው። ከጋብቻ በፊት የሚደረግ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት በቅዱስ ቃሉ በተደጋጋሚ ተኮንኗል፣ ከሌሎቹ የዝሙት ተግባራት ጋር (ሐዋ. 15፡20፤ 1:29; 1 ቆሮንቶስ 5:1; 6:13, 18; 7:2; 10:8; 2 ቆሮንቶስ 12:21; ገላትያ 5:19; ኤፌሶን 5:3; ቆላስይስ 3:5; 1 ተሰሎንቄ 4:3; ይሁዳ 7)። መጽሐፍ ቅዱስ አጠቃላይ መታቀብን ያበረታታል፣ ከጋብቻ ውጭ (እና በፊት)። ከጋብቻ በፊት የሚደረግ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት እንደ ዝሙትና ሌሎቹ አመንዝራነት ስሕተት ነው፣ ሁሉም ካልተጋቡት ሰው ጋር የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነትን ስለሚያካትቱ።

“አብሮ መኖር” ማለት በአንድ ቤት መኖር ከሆነ፣ ያ እንግዲህ የተለየ ጉዳይ ነው። ባጠቃላይ፣ ወንድ እና ሴት በአንድ ቤት ቢኖሩ ምንም ችግር የለውም— ምንም ዓይነት ኢሞራላዊነት እስካልተከናወነ ድረስ። ሆኖም፣ እዛጋ የሚነሣው ችግር አሁንም የኢሞራላዊነት ገጽታ መኖር ነው (1 ተሰሎንቄ 5፡22፤ ኤፌሶን 5፡3)፣ እናም እሱ ለኢሞራላዊነት ብርቱ ፈተና ሊሆን ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ ከዝሙት እንድንሸሽ ይነግረናል፣ ራሳችንን ቋሚ ለሆነ የዝሙት ፈተና እንዳናጋልጥ (1 ቆሮንቶስ 6፡18)። ከዚያም የገጽታ ችግር ይኖራል። አንድ ላይ የሚኖሩ ጥንዶች አብረው እንደሚተኙ ይገመታል— የነገሮች ተፈጥሮ እንደዚያ ነው። ምንም እንኳ በአንድ ቤት መኖር በራሱ ኃጢአት ባይሆንም፣ የኃጢአት ገጽታ ግን እዚያ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ የክፉውን ገጽታ እንድናስወግድ ይነግረናል (1 ተሰሎንቄ 5፡22፤ ኤፌሶን 5፡3)፣ ከዝሙት እንድንሸሽ፣ እና በማንም ላይ መሰናከያ እንዳይኖር ወይም እንዳይቀየም። በውጤቱም፣ እግዚአብሔርን ማክበር አይደለም፣ ወንድና ሴት ከጋብቻ ውጭ አብረው መኖራቸው።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ጥንዶቹ ከጋብቻ በፊት አንድ ላይ መኖራቸው ስሕተት ነውን?
© Copyright Got Questions Ministries