settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ፍርድ ቤት ሄዶ ስለመካሰስ ምን ይላል?

መልስ፤


ሐዋሪያው ጳውሎስ የቆሮንቶስ አማኞችን አንዳቸው ሌላቸውን እንዳይካሰሱ ያሳስባቸዋል፡፡ (1ቆሮ 6፡1-18)፡፡ ለክርስቲያኖች እርስ በእርስ ይቅር አለመባባልና በልዩነታቸው ለመስማማት አለመቻል መንፈሳዊ ውድቀትን ያመለክታል፡፡ አንድ ሰው ክርስቲያኖች ብዙ ችግሮች እናዳለባቸው እና መፍታትም እንደማይችሉ እያየ ለምን ክርስቲያን መሆን ይፈልጋል? ሆኖም ግን ወደ ፍርድ ቤት መሄድ ትክክለኛው እርምጃ የሚሆንበት ጊዜ ምሳሌዎች አሉ፡፡ መጸሐፍ ቅዱሳዊ የሆነው እንደ ገና የመስማማት የመታረቅን መንገድ ከተከተልን እና ወንጀለኛው አካል በስህተቱ ከቀጠለ አንዳንድ ጊዜ ወደ ፍርድ መሄድ ትክክል ሊሆን ይችላል (ማቲ 18:15-17) ፡፡ ይህም መደረግ ያለበት በብዙ ጸሎት እና ጥበብ መሆን አለበት እንዲሁም መንፈሳዊ መሪዎች ጋር መመካከር ያስፈልጋል (ያዕ 1፡5)

ሌላው የ1ኛ ቆሮ 6፡1-6 በቤተክርስቲያን ውስጥ ስላለ አለመግባባት ጳውሎስ የሚጠቅሰው የፍርድ ቤት ስርዓት ፍርድን በሚናገርበት ጊዜ ለዚህ ህይወት አመቺ የሚሆነውን ነው፡፡ ጳውሎስ እያለ ያለው ፍርድ ቤት ያለው ከቤተክርስቲያ ውጪ ያሉ ጉዳዩችን ለመዳኘት እንደሆ ነው የሚለው፡፡ የቤተክርስቲያ ችግሮች ወደ ፍርድ ቤት መሄድ የለባቸውም፤ በቤተክርስቲያ ውስጥ መዳኘተ አለባቸው፡፡

ሥራ ምዕራፍ 21-22 ሲናገር ጳውሎስ በስህተት ባልሰራው ወንጀል ተከሶ ታስሮ ነበር፡፡ ሮማውያን አስረውት ነበር፤ ‹‹አዛዡ ጳውሎስን ወደ ውስጥ አስገባው እና ጥፋቱን እንዲናገደር ጠየቀው፡፡ ለምን ህዝቡ ተቆጥቶ እንደሚጮህ ለማወቅ ፈለገ፡፡ ጳውሎስን ሊያስሩት ሲፈልጉ ጳውሎስ ለወታደሩ ሮሜውያኑን ማሰር ተፈቅዶአለን ብሎ ጠየቀው፡፡››

ጳውሎስ የሮማውያንን ህግ መብቱን ለማስከበር ተጠቀመበት፡፡ የፍርድ ቤት ስርዓትን በትክክለኛ የልብ ሃሳብ ሞቲቭ እስከተደረገ ድረስ መጠቀሙ ምንም ስህተት የለውም፡፡

ጳውሎስ በተጨማሪ እንዲህ አለ ‹‹እንግዲህ ፈጽሞ የእርስ በርስ ሙግት እንዳለባችሁ በእናንተ ጉድለት ነው። ብትበደሉ አይሻልምን? ብትታለሉስ አይሻልምን?›› (1ቆሮ 6፡7) ጳውሎስ በዚህ ስፍራ ትኩረት የሰጠው የአማኞችን ምስክርነት ነው፡፡ ለእኛ አንድን ሰው ወደ ፍርድ ቤት በመውሰድ ይልቅ ከክርስቶስ ከምናርቀው ይልቅ ጥቅሞቻችን ቢቀሩብን ወይንም ብንበደል ይሻላል፡፡ የትኛው የበለጠ አስፈላጊ ነው? የህግ ትግል ወይንስ የአንድ ሰው የዘላለማዊ ነፍስ ትግል?

በማጠቃለያ ክርስቲያኖች በቤተክርስቲያን ጉዳይ ተያይዘን ወደ ፍርድ ቤት መሄድ አለብን? በፍጹም አይደለም! ክርስቲያኖች በህዝባዊ ጉዳዩች ወደ ፍርድ ቤት መሄድ አለባቸው? በሌላ መንገድ ማስወገድ እየተቻለ? አይ የለባቸውም፡፡ ክርስቲያኖች የማያምኑ ሰዎች ወደ ፍርድ ቤት በህዝባዊ ጉዳዩች መውሰድ አለባቸው? እንደገና በሌላ መንገድ ማስወገድ እየተቻለ? አይ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን በአንዳንድ ጉዳዩች ላይ ለምሳሌ መብትን ለማስከበር (ጳውሎስ እዳደረገው) ምናልባት ህጋዊ መፍትሄ መፈለግ ትክክል ሊሆን ይችላል፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ፍርድ ቤት ሄዶ ስለመካሰስ ምን ይላል? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries