settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ኢየሱስ የእግዚአብሔር በግ ነው ማለት ምን ማለት ነው?

መልስ፤


ኢየሱስ የእግዚአብሔር በግ ተበብሎ በዮሐ 1፡29 እና ዮሐ 1፡36 ሲጠራ ትክክለኛውና የመጨረሻው የኃጢያት መስዋእት መሆኑን ለማመልከት ነው፡፡ ክርስቶስ ማን አንደነበር እና ምን እንደሰራ ለመረዳት ከብሉይ ኪዳን ስለመተላለፋችን እንደሚሰዋ የሚናገሩትን ትንቢታዊ መልእክት ያላቸውን ክፍሎች በመመልከት መጀመር አለብን (ኢሳ 53፡10)፡፡ በእርግጥ ሁሉም መስዋዕት ለኢየሱስ መምጣት ደረጃን በማዘጋጀት በብሉይ ኪዳን የተጀመሩት በእግዚአብሔር ነው፤ እርሱም ትክክለኛ መስዋዕት እግዚአብሔር ለህዝቡ ኃጢያት ያዘጋቸው ንሰሐ ያዘጋጀው፡፡ (ሮሜ 8፡3፤ ዕብ 10)፡፡

የበግ መስዋዕት በአይሁዳዊያን ሃይማኖታዊ ህይወት በስዋእት ስርአት ውስጥ ትልቅ ስፍራ አለው፡፡ ዮሐንስ ኢየሱስን እንደ ‹‹የሰውን ለጆች ኃጢያት የሚያስወግድ ይእግዚአብሔር በግ›› በሎ ሲመስል የሚሰሙት አይሁዶች ወዲያውኑ የሚያስቡት አስፈላጊ የነበሩትን እንዚያን መስዋዕት ነው፡፡ የማለፍ በአል እየቀረበ በሚመጣበት ወቅት የመጀሪያው ሃሳብ የማለፍ በአል በግ ነው፡፡ የማለፍ በዓል የአይሁድ ህዝብ ዋንኛ በአሎች መካከል አንዱ ነው ሲሆን እግዚአብሔር እስራኤል እንዴት ከግብጽ ባረነት እንዳወጣቸው የሚያስቡበት ነው፡፡ በእርግጥ የማለፍ በዓል በግ መታረድ የደሙ በቤቱ ላይ መቀባት የኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል ላይ የመስዋዕት ጥሩ መግለጫ ነው (ዘጽ 12፡11-13)፡፡ እርሱ የሞተላቸውና በደሙ የተሸፈኑ ከሞት (መንፈሳዊ) መልአክ አዳናቸው፡፡

ሌላኛው ዋና መስዋዕት በጉን አስመልክቶ በየቀኑ በኢየሩሳሌም መቅደስ የሚቀርበው ነበር፡፡ በየጠዋቱ እና በየማታው በመቅደሱ ውስጥ በግ ለህዝቡ ኃጢያት ይሰዋ ነበር (ዘጽ 29፡ 38-42)፡፡ እንዚህ የየቀን መስዋዕቶች እንደሌሎቹ ሁሉ ወደ እውነተኛው የኢየሱስ የመስቀል መስዋዕት ህዝቡን ያመለክቱ ነበር፡፡ በእርግጥ ኢየሱስ በመስቀል ላይ የሞተበት ሰአት በመቅደስ የማታው መስዋእት ከሚሰዋበት ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ አይዶች በዚያን ጊዜ በኤርሚያስና በኢሳያስ በነበያቱ በተነገረው ትንቢት አውቀውት ሊሆን ይችላል፤ እርሱ ‹‹እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ እንደ የዋህ በግ›› እንደዚህ እንደሚሆን (ኤር 11፡19፡ ኢሳ 53፡7) እና መከራን እንደሚቀበል እና መስዋዕት እንደሚሆን ለእስራኤልም መቤዣትን እንደሚያደርግ፡፡ በትክክል ያ ሰው ከኢየሰስ ክርስቶስ ውጪ ማንም ሊሆን አይችልም‹‹የእግዚአብሔር በግ››

የመስዋዕቱ ስርዓት ዛሬ ለእኛ እንግዳ ቢመስልም ግን የክፍያ እና የካሳ ሃሳብ ግን በቀላሉ ልንረዳው የምንችለው ነው፡፡ እናውቃለን የኃጢያት ዋጋው ሞት ነው (ሮሜ 6፡23) ኃጢያታችን ከእግዚአብሔር ለይቶናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሁላችንም ኃጢያተኞች እንደሆንን እንደሚያስተምር እናውቃለን ማናችንም ብንሆን በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን አይደለንም (ሮሜ 3፡23)፡፡ በእኛ ኃጢያት ምክንያት ከእግዚአብሔር ተለየን እና በፊቱም ኃጢያተኞች ሆንን፡፡ ያለን በቸኛው ተስፋ እርሱ ከራሱ ጋር ሊያስታርቀን መንገድ ሲያዘጋጅልን ነው እርሱም ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ለእኛ በመስቀል ላይ እንዲሞት ያደረገው ለዚህ ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ለኃጢያት ምትክ ለመሆን ሞተ የኃጢያትንም እዳ ለመክፈል በእርሱ ለሚያምኑት ሁሉ፡፡

በእርሱ የመስቀል ሞት በኩል ነው ለኃጢያት የእግዚአብሔር ፍጹም መስዋዕት እና ከሶስት ቀን በኋላ የእርሱ ትንሳኤ እኛ አሁን ዘላለማዊ ህይወት በእርሱ ብናምን እንድናገኝ አድርጎናል፡፡ እውነታው እግዚአብሔር ራሱ ለኃጢያታችን መስዋዕትን አዘጋጀልን ለኃጠያታችን የተደረገ መስዋዕት የክብር የወንጌል መልካም ወሬ በ1ጴጥ 1፡18-21 በግልጽ የተቀመጠ ነው፡ ‹‹ ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።ዓለም ሳይፈጠር እንኳ አስቀድሞ ታወቀ፥ ነገር ግን እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ፥ ከሙታን ባስነሣው ክብርንም በሰጠው በእግዚአብሔር በእርሱ ስለምታምኑ ስለ እናንተ በዘመኑ መጨረሻ ተገለጠ።››

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ኢየሱስ የእግዚአብሔር በግ ነው ማለት ምን ማለት ነው? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries