settings icon
share icon
ጥያቄ፤

በምሞትበት ወቅት ወደ መንግስተ ሰማይ እንደምገባ እንዴት እርግጠኛ ልሆን እችላለሁ?

መልስ፤


የዘላለም ሕይወት እንዳለህና በምትሞትበትም ወቅት ወደ መንግስተ ሰማያት እንደምትገባ በእርግጠኝነት ታውቃለህ? እግዚሐብሔር እርግጠኛ እንድትሆን ይፈልጋል። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡ “የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚሐብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህንን ጽፌላችኋለሁ።”(1ኛ ዮሐንሰ 5፡13) ለአብነት ያህል አሁን በእግዚሐብሔር ፊት ቆመሃል እንበልና “ለምንድነው ወደ መንግስተ ሰማይ እንድትገባ የምፈቅድልህ?” ብሎ ቢጠይቅህ ምን ብለህ ትመልስለታለህ? ምላሹን ለመስጠት ግር ሊልህ ይችላል። ልታውቀው የሚገባ ነገር ቢኖር እግዚሐብሔር እኛን እንደሚወደንና ቀሪው ዘመናችንን የት እንደምናሳልፍ እንድናውቅ መንገድ አዘጋጅቶልናል። መጽሐፍ ቅዱስ ጉዳዩን በዚህ መልክ ያብራራዋል። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚሐብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ አለሙን እንዲሁ ወዶአልና” (ዮሐንስ 3፡ 16)።

በመጀመሪያ ወደ መንግስተ ሰማይ እንዳንገባ የሚከለክለን ችግር ምን እንደሆነ ሊገባን ያስፈልጋል። ችግሩ ይህንን ይመስላል፦ ኃጢያታዊ ተፈጥሮአችን ከእግዚሐብሔር ጋር ግንኙነት እንዳናደርግ ያግደናል። እኛ በተፈጥሮአችንና በምርጫችን ኃጢያተኞች ነን። “ልዩነት የለምና፣ ሁሉ ኃጢያትን ሰርተዋልና የእግዚሐብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል” (ሮሜ 3፡ 23)። እኛ ራሳችንን ማዳን አንችልም። “ጸጋው በእምነት አድኗችኋልና ይህም የእግዚሐብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከስራ አይደለም።” (ኤፌሶን 2፡ 8-9)። እኛ ሞትና ገሐነም እሳት ይገባናል። “የኃጢያት ደመወዝ ሞት ነውና” (ሮሜ 6፡ 23)።

እግዚሐብሔር ቅዱስና ቅን ፈራጅ ስለሆነ ኃጢያትን መቅጣት አለበት። ይሁን እንጂ እኛን ይወደናል፣ ለኃጢያታችንም ይቅርታ አዘጋጅቶልናል። ኢየሱስ ሲናገር እንዲህ አለ “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ። ከእኔ በቀር ወደአብ የሚመጣ የለም”። (ዮሐንስ 14፡ 6)። ኢየሱስ ለኛ ብሎ በመስቀል ላይ ሞተ። “ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚሐብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለአመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢያት ምክንያት ሞቶአልና።” (1ኛ ጴጥሮስ 3፡ 18)። ኢየሱስ ከሙታን ተነስቷል። “ስለእኛም ነው እንጂ ስለበደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለማጽደቅም የተነሳውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሳው ለምናምን ለእኛ ይቆጠርልን ዘንድ አለው።” (ሮሜ 4፡ 25)።

ስለሆነም ወደ መጀመሪያው ጥያቄ እንመለስ፦ “በምሞትበት ወቅት ወደ መንግስተ ሰማይ እንደምገባ እንዴት እርግጠኛ ልሆን እችላለሁ?” መልሱ ይህ ነው፡ “በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተም ትድናለህ(የሐዋርያት ሥራ 16፡ 31)። “ለተቀበሉት ሁሉ ግን፣ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚሐብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ስልጣንን ሰጣቸው።” ( ዮሐንስ 1፡ 12)። አንተ የዘላለም ህይወትን እንደ ነጻ ስጦታ ልትቀበል ትችላለህ። “የእግዚሐብሔር የፀጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።” (ሮሜ 6፡ 23)። በአሁኑ ሰዓት ሙሉና ትርጉም ያለው ሕይወት መኖር ትችላለህ። ኢየሱስ እንዲህ ብሏል “እኔ ህይወት እንዲሆንላቸው፣ እንዲበዛላቸውም መጣሁ።” (ዮሐንስ 10፡ 10)። በመንግስተ ሰማያት ከኢየሱስ ጋር ለዘላለም መኖር ትችላለህ። እሱ ቃል እንደገባው “ ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፣ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ” (ዮሐንስ 14፡ 3)።

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደግል አዳኝህ በመቀበል ከእግዚሐብሔር የቀረበውን ይቅርታ ለመቀበል የምትፈልግ ከሆነ አሁን የቀረበልህን ፀሎት መፀለይ ትችላለህ። ይህንን ፀሎት ማቅረብ ወይም ሌላ ፀሎት ማነብነብ አያድንህም። ለኃጢያትህ ስርየት የሚያስገኝልህ በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ስታምን ነው። ይህንን ፀሎት የምታቀርበው ለእግዚሐብሔር ያለህን እምነት ለመግለጽና ኃጢያትህን ይቅር ስላለህ ምስጋና የምታቀርብበት መንገድ ነው። “እግዚሐብሔር ሆይ በአንተ ፊት ኃጢያት ፈጽሜአለሁ። ሰለሆነም ቅጣት ይገባኛል። ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኔ የሚገባውን ቅጣት ስለከፈለልኝ በርሱ በማመኔ ይቅርታ ተደርጎልኛል። በምህረትህ እታመናለሁ። ስለአስደናቂው ፀጋህና ይቅርታህ አመሰግንሐለሁ! አሜን!

እዚህ ባነበብከው ምክንያት ለክርስቶስ ውሳኔ ላይ ደርሰሃል? እንዲያ ከሆነ፣ “ዛሬ ክርሰቶስን ተቀብያለሁ” የሚለውን ቁልፍ ተጫን

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

በምሞትበት ወቅት ወደ መንግስተ ሰማይ እንደምገባ እንዴት እርግጠኛ ልሆን እችላለሁ?
© Copyright Got Questions Ministries