settings icon
share icon
ጥያቄ፤

በብልሃት የተሰራ ንድፍ ፅንሰ ሃሳብ ምንድን ነው?

መልስ፤


‹‹ በብልሃት የተሰራ ንድፍ ፅንሰ ሃሳብ የሚለው ወስብስቡን ነገር ለመግለጽ የብልሃት መክንያቶቸ አስፈላጊ ናቸው፤ በመረጃ የበለጸገው የስነ ህይወት አካል መረጃ እና ከርሱ ጋር ተከትለው የሚመጡት በተለመዶ ተለይተው የሚታወቁነና ሊደረስባቸው የሚችሉ ናቸው፡፡

የማይቀነሰው ውስብስባዊነት (Irreducible complexity) ሲተረጎም ‹‹…ለአንድ ዋና ተግባር የተለያዩ ተመሳሳይነት ያላቸው አንዱ ከአንዱ ጋር የተያያዙ ከፍሎች ውስጥ ያ አንዱ ነጠላ ስርዓት ቢጎድል ስርዓቱ እንዲቆም ይሆናል፡፡››በግልጽ ለማስቀመጥ ህይወት ጠቃሚ እንዲሆን አንዱ በአንዱ ላይ ተያይዞ ተጠላልፎ የሚገኙበት ነው፡፡ የዘፈቀደ ለውጥ ለአዲስ ክፍል እድገት መረጃ ሊሆን ይችላል፤ ግን በአንድ ላይ ለተገናኙ በዙ ከፍሎች እድገት በተለይም በአንድ ስርዓት ለሚሰሩ ሊሆን አይችልም፡፡ ለምሳሌ የሰው አይን ስርዓት እንደሚታወቀው በጣም ጠቃሚው ነው፡፡ ከአይን ብሌን ውጪ የኦፕቲክ ነርቭ እና ቪዥአል ኮርቴክስ የሚታይ በዘፈቀደ መለወጥ ያልተሟላ አይን ሁሉም ከፍሎቹ ከሌሉ በአንድ ጊዜ በአንድ ላይ ሆነው በትክክል ካልሰሩ ወጤቱን በመቃወም የዛን አካል ጥቅም አያስገኝም፤ ወይንም ደግሞ ከተፈጥር ስርዓት ወጪ ይሆናል፡፡

የማይቀነሰው ውስብስባዊነት (Irreducible complexity) ሃሳብ ህይወት ያለው አካል ወስጥ ውስብስብ ነድፍ ካለ ወደ አንድ ወደ መገኛቸው የሚወስደን የሚመራን ነገር አለ፡፡ የተወሰነው ውስብስባዊነት (specified complexity) ረቂቁን ንድፍ በዘፈቀደ ስርዓት ውስጥ ልናሳድገው አንችልም ብሎ የክርክር ሃሳብ ያስቀምጥልናል፡፡ ለምሳሌ 100 ጦጣዎች የተሞላ ክፍል እና 100 ኮምፒዩተር ምናልባት ጥቂት ቃላቶችን ወይንም ዓረፍተ ነገር ሊያስገኙልን ይችላሉ ነገር ግን የሼኪስፔርን ግጥም ግን አይስገኙልንም፡፡ እናም ምን ያህል ስነ ፍጥረቱ ህይወት ከሼክስፒር ስራ ይልቅ ረቂቁ ነው?

የሰው ዘር ጥናት መርህ እንደሚያስቀምጥልን አለምና ስነ ህዋ ዩኒቨርስ ህይወት በመድር ላይ እንዲሆን ‹‹‹ተስተካክለዋል››፡፡ በአየር ውስጥ ያለ ንጥረ ነገር መጠን ቢቀየር ብዙ ፍጥረታት ወዲያውኑ ይሞታሉ፡፡ መሬት ከፀሐይ ትንሽ የቀረበች ቢሆን ወይንም የራቀች ቢሆን በዙ ፍጥረታት መኖር ያቆማሉ፡፡ የህይወት በምድር ላይ መኖርና ማደግ ብዙ ተለዋዋጭ ነገሮች በትክክል ያልተስተካከሉ ከሆነ ተለዋዋጭ የሆኑ ነገሮች በዘፈቀደ ባልተደራጀ ሁኔታ የሚሄዱ ከሆነ የማይቻል ነው፡፡

በብልሃት የተሰራ ንድፍ (The Intelligent Design) የማሰብ ችሎታ ምንጭ ለይተው ማሳየት የማይችሉ ከሆነ (ለእግዚአብሔርም ሆነ ለልዩ ፍጥረት ወይንም ሌላ ነገር) በብልሃት የተሰራ ንድፍ ጽንሰ ሃሳብ ያላቸው እግዚአበሔር የለም የሚሉ ናቸው፡፡ በስነ ህይወት ካለው አለም ጋር የሚስማማውን ንድፍ መኖር አይተው ለእግዚአብሔር መኖር እንደ መረጃነት ይወስዳሉ፡፡ ሆኖም ጥቂት የብልሃት ንድፍን የማይክዱ ከሃዲ አምላክ የለሾች አሉ ነገር ግን ለእግዚአብሔረ ፈጣሪነት እውቅና አይሰጡም፡፡ መረጃዎችን ምድር የተመሰረተችው ከምድር ወጪ ከሆነ ስፍራ በመጣ አለቃ ጌታ ነው ብለው ለመተረጎም ይጠቀሙባቸዋል፡፡ እውነት ነው የዛን የልዩ ፍጥረት መገኛም አይጠቅሱም መልስም የላቸውም፡፡

በብልሃት የተሰራ ንድፍ ጽንሰ ሃሳብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የመፍጠር ስራ ሃሳብ አይደለም፡፡ በሁለቱ መካከል አስፈላጊ የሆነ ልዩነት አለ፡፡ በጽሐፍ ቅዱሳዊ የመፍጠር ስራ የሚጀመረው መጽፍ ቅዱስ ስለ መፍጠር ስራ የሚለው ትክክልና እውነት ነው የሚል ድምዳሜ በመስጠት ነው፤ በመድር ያለው ህይወት ብልህ በሆነ አካል የተነደፈ ነው እርሱም እግዚብሔር፡፡ ከዛም በዚህ መደምደሚያ ላይ ለመድረስ ከገሃዱ አለም መረጃን ይፈልጋሉ፡፡ በብልሃት የተሰራ ንድፍ ጽንሰ ሃሳብ የሚያራምዱ ከገሃዱ አለም በመነሳት ምድር ብልህ በሆነ አካል ተነድፋለች ይላሉ(ማንም የትኛውም ሊሆን ይችላል) ፡፡

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

በብልሃት የተሰራ ንድፍ ፅንሰ ሃሳብ ምንድን ነው?
© Copyright Got Questions Ministries