settings icon
share icon
ጥያቄ፤

እንዴት ልድን እችላለሁ?

መልስ፤


ቀላል ነው ሆኖም መሰረታዊ ነገር ነው ሊጠየቅ የሚችል ዋና ጥያቄ ነው፡፡ ‹‹እንዴት ልድን እችላሉሁ?›› ይህ የሚያትተው የዚህ ምድር ኑሮ ሲያበቃ ወዴት ልሄድ እችላለሁ የሚለውን ነው፡፡ ከዘላለማዊ መኖሪያችን በላይ አስፈላጊ የሆነ ጉዳይ ሊኖር አይችልም፡፡ ደስ የሚለው መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ሰው እንዴት መዳን እንደሚችል በግልጽ ይናገራል፡፡ የእስሪ ቤቱ አለቃ ጳውሎስን እና ሲላስ ለመዳን ምን ማድረግ ይገባኛል ብሎ ሲጠይቅ ጳውሎስና ሲላስ የመለሱለት ‹‹ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ አሉት።›› (ሥራ 16፡30-31)

እንዴት መዳን እችላለሁ? መዳን ለመን ያስፈልገኛል?
ሁላችንም በኃጢያት ወደቀናል (ሮሜ 3፡23) በኃጢያት ተወልደናል (መዝ 51፡5) ሁላችንም ኃጢያትን መርጠናል (መክ 7፡20፡ 1ዮሐ 1፡8)፡፡ ኃጢያት ከድኅነት ውጪ ያደርጋል፡፡ ኃጢያት ከእግዚአብሔር ይለያል፡፡ ኃጢያት የዘለአለም የጥፋት መንገድ ነው፡፡

እንዴት ልድን እችላለሁ? ከምንድን ነው የምድነው?
በኃጢያታችን ምክንያት ሁላችንም ሞት ይገባናል (ሮሜ 6፡23)፡፡ የሚታየው የኃጢያት ውጤት አካላዊ ሞት በሆንም ነገር ግን በኃጢያት ምክንያት የሚመጣ ብቸኛው አይነት ሞት ግን አይደለም፡፡ ሁለም ኃጢያት ዘላለማዊውን አምላክ በመቃወም የሚሰራ ነው (መዝ 51፡4)፡፡ በዚህም የተነሳ ትክክለኛው የኃጢያታችን ዋጋም ዘላለማዊ ነው፡፡ መዳንም የሚያስፈልገን ከዘላለማዊ ጥፋት ነው (ማቲ 25፡46;ራዕ 20፡15)፡፡

እንዴት ልድን እችላለሁ? እግዚአብሔር እንዴት ነው ድኅነትን ያዘጋጀው?
ትክክለኛው የኃጢያት ቅጣት ዘላለማዊ ከሆነ እግዚአብሔር ብቻ ነው ቅጣቱን ሊከፍለው የሚችለው ምክንያቱም እርሱ ብቻ ዘላለማዊ ነው፡፡ እግዚአብሔረ ግን በመለኮታዊ ማንነቱ ሊሞት አይችልም፡፡ ስለዚህም በኢየሱስ ክርስቶስ ኢየሱስ ስጋ አምላክ ሰው ሆነ፡፡ መለኮት ስጋን ለበሰ በእኛም መካከል አደረ እናም አስተማረን፡፡ ሰዎች እርሱን እና መልእክቱን ተቃወሙት ገደሉት፡፡ እረሱ በፈቃደኝነት ራሱን አሳልፎ ሰጠን ላመሰቀል ራሱን አሳልፎ ሰጠ (ዮሐ 10፡15)፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውም ስለነበር መሞት ይችል ነበር መለኮትም ስለነበር የእርሱ ሞት ዘላለማዊ ፈይዳ አለው፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ መሞት ሙሉ የሆነ የኃጢያታችን ክፍያ ነበር (1ዮሐ 2፡2)፡፡ እኛ ልንቀበለውን የሚገባንን እርሱ ወሰደልን፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን መነሳት የሚገልጽልን የእርሱ ሞት በትክክል በቂ የሆነ የኃጢያታችን ከፍያ እንደሆነ ነው፡፡

እንዴት ልድን እችላለሁ? ምን ማድረግ ይገባኛል?
‹‹ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ አሉት።›› (ሥራ 16፡31)፡፡ እግዚአብሔር ስራውን ሁሉ ፈጽሞታል፡፡ ማድረግ የሚኖርብህ እግዚአብሔር ያዘጋጀውን ድኅነት በእምነት መቀበል ነው (ኤፌ 2፡8-9)፡፡ መሉ በሙሉ ስል ኃጢያትህ አዳ ክፍያ ኢየሱስ ክርስቶስን ማመን፡፡ በእርሱ ማመን እናም አትጠፋም (ዮሐ 3፡16)፡፡ እግዚአብሔር ድኅነትን በስጦታ እየሰጠህ ነው፡፡ ማድረግ የሚጠበቅብህ መቀበል ብቻ ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የድኅነት መንገድ ነው (ዮሐ 14፡6)፡፡

English


ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ
እንዴት ልድን እችላለሁ?
© Copyright Got Questions Ministries