settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የታላቁ ነጭ ዙፋን ፍርድ ምንድነው?

መልስ፤


የታላቁ ነጭ ዙፋን ፍርድ ራዕይ 20፡11-15 ላይ ተገልጿል፣ እሱም የፍጻሜው ፍርድ ሥርዓት ነው፣ የጠፉት ወደ እሳት ባሕር የሚጣሉበት። ከራዕይ 20፡7-15 እንደምንረዳው፣ ይህ ፍርድ የሚከናወነው ከሚሊኒየሙ በኋላ ነው፣ እንዲሁም ሰይጣን፣ አውሬው፣ እና ሐሰተኛው ነቢይ ወደ እሳት ባሕር ከተጣሉ በኋላ (ራዕይ 20፡7-10)። የተከፈቱት መጻሕፍት (ራዕይ 20፡12) የእያንዳንዱን ሰው ሥራ ይዘዋል፣ መልካም ቢሆን ወይም ክፉ፣ እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ከማወቁ የተነሣ፣ የተባለውን፣ የተደረገውን፣ ወይም የታሰበ እንኳ ቢሆን፣ እሱም ይሸልማል ወይም ይቀጣል፣ እያንዳንዱን በዚያው መሠረት (መዝሙር 28:4፤ 62:12፤ ሮሜ 2:6፤ ራዕይ 2:23፤ 18:6፤ 22:12)።

ደግሞም በዚህ ጊዜ፣ ሌላ መጽሐፍ ተከፈተ፣ “የሕይወት መጽሐፍ” የሚባል (ራዕይ 20፡12)። ይህ መጽሐፍ ነው የሚወስነው፣ ግለሰቡ ከእግዚአብሔር ጋር የዘላለም ሕይወትን የሚወርስበት አልያም ዘላለማዊ ቅጣት በእሳት ባሕር የሚቀበልበት። ምንም እንኳ ክርስቲያኖች ለድርጊታቸው ተጠያቂ ቢሆኑም፣ በክርስቶስ ይቅር ተብለዋል፣ እናም ስማቸው ተጽፏል “በሕይወት መጽሐፍ ላይ፣ ከዓለም ፍጥረት አንሥቶ” (ራዕይ 17፡8)። ከቅዱስ ቃሉም እንደምንረዳው በዚህ ፍርድ ላይ ነው፣ ሙታን “እንደ ሥራቸው መጠን የሚፈረድባቸው” (ራዕይ 20፡12) እናም “የማንም ሰው ስም” እሱም “በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፈ” “ወደ እሳት ባሕር ይጣላል” (ራዕይ 20፡15)።

በሰዎች ሁሉ ላይ የመጨረሻ ፍርድ ይሰጣል የሚለው ሐቅ፣ አማኞችም ሆነ የማያምኑ፣ በግልጽ ተረጋግጧል፣ በቅዱስ ቃሉ በበርካታ ምንባቦች። እያንዳንዱ ሰው አንድ ቀን በክርስቶስ ፊት ይቆማል፣ ስለ ሥራውም ወይም ሥራዋም የፈረድባቸዋል። የታላቁ ነጭ ዙፋን ፍርድ በየመጨረሻ ፍርድ መሆኑ እጅግ ግልጽ ቢሆንም፣ ክርስቲያኖች ስምምነት የላቸውም፣ ከሌሎቹ ፍርዶች፣ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ከተጠቀሱት ጋር እንዴት እንደሚዛመድ፣ በተለይም ማን በታላቁ ነጭ ዙፋን ፍርድ ፊት እንደሚፈረድበት።

አንዳንድ ክርስቲያኖች የሚያምኑት፣ ቅዱስ ቃሉ የሚገልጠው ሦስት የተለያዩ ፍርዶች እንደሚመጡ ነው። የመጀመሪያው የበጎች እና የፍየሎች ፍርድ ነው ወይም የአሕዛብ ፍርድ (ማቴዎስ 25፡31-36)። ይህም የሚሆነው ከመከራው ጊዜ በኋላ ሲሆን፣ ከሚሊኒየሙ ቀደም ይላል፤ የእሱም ዓላማ ማን ወደ ሚሊኒየሙ መንግሥት እንደሚገባ መወሰን ነው። ሁለተኛው የአማኞች ሥራ ፍርድ ነው፣ ዘወትርም የሚጠቀሰው እንደ “ክርስቶስ የፍርድ ወንበር [bema]” ነው (2 ቆሮንቶስ 5፡10)። በዚህ ፍርድ ክርስቲያኖች ለሥራቸው ወይም ለእግዚአብሔር ላደረጉት አገልግሎት የሽልማት ማዕርጎችን ይቀበላሉ። ሦስተኛው የታላቁ ነጭ ዙፋን ፍርድ ነው፣ በሚሊኒየሙ መጨረሻ (ራዕይ 20፡11-15)። ይህ የማያምኑት ፍርድ ነው፣ እነርሱም እንደ ሥራቸው መጠን የሚፈረድባቸውና በእሳት ባሕር የዘላለም ቅጣት የሚወሰንባቸው።

ሌሎች ክርስቲያኖች የሚያምኑት እነዚህ ሦስቱም ፍርዶች የሚናገሩት ስለ ተመሳሳይ የመጨረሻ ፍርድ ነው፣ ስለ ተለያዩ ሦስት ፍርዶች ሳይሆን። በሌላ አገላለጽ፣ የታላቁ ነጭ ዙፋን ፍርድ፣ በራዕይ 20፡11-15 ላይ አማኞች እና የማያምኑት በተመሳሳይ መልኩ የሚፈረድባቸው ነው። ስሞቻቸው በሕይወት መጽሐፍ የተገኙት እነርሱ በሥራቸው ይፈረድባቸዋል፣ ስለሚቀበሉት ወይም ስለሚያጡት ሽልማት ለመወሰን። ስሞቻቸው በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፉት እነርሱ በሥራቸው ይፈረድባቸዋል፣ በእሳት ባሕር ስለሚቀበሉት የቅጣት ደረጃ መጠን ለመወሰን። ይሄንን አመለካከት የያዙት የሚያምኑት፣ ማቴዎስ 25፡31-46 ሌለኛው መግለጫ ነው፣ በታላቁ ነጭ ዙፋን ፊት ምን እንደሚከናወን። እነርሱ የሚጠቁሙት ሐቅ፣ የዚህ ፍርድ ውጤት ራዕይ 20፡11-15 ላይ ካለው ከታላቁ የነጭ ዙፋን ፍርድ ቀጥሎ ከሚታየው ጋር ተመሳሳይ ነው። በጎች (አማኞች) ወደ ዘላለም ሕይወት ይገባሉ፣ ፍየሎች (የማያምኑ) ደግሞ ወደ “ዘላለማዊ ቅጣት” ይጣላሉ (ማቴዎስ 25፡46)።

ስለ ታላቁ ነጭ ዙፋን ፍርድ ማንም የፈለገውን ዓይነት አመለካከት ቢይዝም፣ ጠቃሚ የሚሆነው ስለሚመጣው(ጡት) ፍርዶች ሐቅ በተመለከተ ፈጽሞ ዕይታን ማጣት አይገባም። በቅድሚያ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ፈራጅ ይሆናል፣ የማያምኑት ሁሉ በክርስቶስ ይፈረድባቸዋል፣ እናም በሠሩት ሥራ መሠረት ይቀጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ እጅግ ግልጽ ነው፣ የማያምኑት በራሳቸው ላይ ቁጣን እንደሚያከማቹ (ሮሜ 2፡5) እግዚአብሔርም “ለእያንዳንዱ ሰው እንዳደረገው መጠን ይሰጠዋል” (ሮሜ 2፡6)። አማኞችም ደግሞ በክርስቶስ ይፈረድባቸዋል፣ ነገር ግን የክርስቶስ ጽድቅ ወደ እኛ በመተላለፉ ምክንያት እና ስማችን በሕይወት መጽሐፍ በመጻፉ፣ እንሸለማለን እንጂ አንቀጣም፣ እንደ ሥራችን ሁኔታ። ሮሜ 14፡10-12 እንደሚለው፣ ሁላችንም በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለን፣ እናም እያንዳንዳችን ለእግዚአብሔር ምላሽ እንሰጣለን።

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የታላቁ ነጭ ዙፋን ፍርድ ምንድነው?
© Copyright Got Questions Ministries