settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ግብረ-ሰዶማዊነት ጋብቻ ምን ይላል/ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ?

መልስ፤


መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ግብረ-ሰዶማዊነት ሊገልጽ፣ ስለ ስለ ግብረ-ሰዶማዊ ጋብቻ/የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ለይቶ አይጠቅስም። እሱ ግልጽ ነው፣ ሆኖም፣ መጽሐፍ ቅዱስ ግብረ-ሰዶማዊነትን እንደ ኢ-ሞራላዊና ተፈጥሯዊ እንዳልሆነ ኃጢአት ይኮንናል። ሌዋውያን 18፡22 ግብረ-ሰዶማዊነትን እንደ ርኩሰት ይወስደዋል፣ እንደ ጸያፍ ኃጢአት። ሮሜ 1፡26-27 የግብረ-ሰዶማዊነት ሐሳብና ድርጊትን እንደ አሳፋሪ፣ ተፈጥሯዊ እንዳልሆነ፣ ሴሰኝነት፣ እና ወራዳነት አድርጎ ይገልጸዋል። አንደኛ ቆሮንቶስ 6፡9 እንደሚያስቀምጠው ግብረ-ሰዶማውያን ርኩሶች ናቸው እናም የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። ሁለቱም የግብረ-ሰዶማዊነት ሐሳብና ድርጊቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ተኮንነዋል፣ የግብረ-ሰዶማውያን “ጋብቻ” የእግዚአብሔር ፍቃድ አለመሆኑ ግልጽ ነው፣ እናም በእውነቱ ኃጢአት ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጋብቻ በሚጠቅስበት ጊዜ ሁሉ፣ በወንድና በሴት መካከል ነው። በመጀመሪያ የተጠቀሰው ጋብቻ፣ ዘፍጥረት 2፡24፣ ሰው ወላጆቹን ትቶ ከሚስቱ ጋር እንደሚተባበር ይገልጻል። ጋብቻን በተመለከተ መመሪያ የሚሰጡ ምንባቦች፣ እንደ 1 ቆሮንቶስ 7፡2-16 እና ኤፌሶን 5፡23-33 ያሉት፣ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስቀመጠው ጋብቻ በወንድና በሴት መካከል መካሄዱን ነው። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አባባል፣ ጋብቻ የሕይወት ዘመን ኅብረት ነው፣ በወንድና በሴት መካከል፣ በቅድሚያ ቤተሰብን ለመገንባትና ለእዚያ ቤተሰብ አመቺ የሆነ አካባቢ ለመስጠት።

ሆኖም፣ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ይህንን የጋብቻ መረዳት ለመፈጸም ጥቅም ላይ የሚውል አይደለም። የመጽሐፍ ቅዱስ የጋብቻ አተያይ ሁለንተናዊ የሆነ የጋብቻ አተያይ ሆኗል፣ በእያንዳንዱ የሰዎች ሥልጣኔ፣ በዓለም ታሪክ ላይ። ታሪክ የግብረ-ሰዶማዊነትን ጋብቻ ተቃውሞ ይሞግታል። ዘመናዊው ሃይማኖታዊ ያልሆነው ሥነ-ልቦና እውቅና እንደሰጠው ወንድና ሴት በሥነ-ልቦናም ሆነ በስሜት የተፈጠሩት እርስ በርሳቸው እንዲቀባበሉ ነው። ቤተሰብን በተመለከተ፣ የሥነ-ልቦና ሰዎች የሚሉት በወንድና በሴት መካከል የሚደረግ ኅብረት፣ ሁለቱ ተጋቢዎች መልካም የሆነውን ጾታዊ ሚናቸውን እንዲወጡ ያስችላቸዋል፣ በተሻለ ስፍራ በመልካም የተቀረጹ ልጆችን ለማሳደግ። ሥነ-ልቦና የግብረ-ሰዶማዊ ጋብቻን ተቃውሞ ይሞግታል። በተፈጥሮ/በአካል፣ ወንድና ሴት የተፈጠሩት በግብረ-ሥጋ ግንኙነት አንድ ላይ “እንዲገጥሙ” መሆኑ ግልጽ ነው። በግብረ-ሥጋ ግንኙነት “ተፈጥሯዊ” አሠራር ልጆችን ለመውለድ፣ በግልጽ የተቀመጠው ብቸኛ መንገድ በወንድና በሴት መካከል የሚደረግ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ነው ይሄንን ዓላማ የሚያሳካ። ተፈጥሮ የግብረ-ሰዶማዊነትን ጋብቻ ተቃውሞ ይሞግታል።

ስለዚህ፣ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ታሪክ፣ ሥነ-ልቦና፣ እና ተፈጥሮ ሁሉ የሚሞግቱት ጋብቻ በወንድ እና በሴት መካከል መካሄድ እንደሚኖርበት ነው— ታዲያ ዛሬ ይህ ሁሉ ውዝግብ ለምን ሆነ? የግብረ-ሰዶማዊነትን/የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን የሚቃወሙት ለምን በጥላቻ ይታያሉ፣ እንደማይታገሡ ፍርደ-ገምድሎች፣ ምንም ያህል ተቃውሞው በወጉ ቢቀርብም? የግብረ-ሰዶማውያን መብት እንቅስቃሴ ለምን በከፋ መልኩ ለግብረ-ሰዶማውያን/ተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ጠንክሮ ይሠራል፣ አብዛኛው ሰው ሃይማኖታዊም ሆነ ሃይማኖታዊ ያልሆነ ለምን ይደግፉታል ወይም ቢያንስ ከመቃወም ርቀው ይቆማሉ— ግብረ-ሰዶማዊ ጥንዶች ተመሳሳይ የሆነ ሕጋዊ መብት እንዲያገኙ፣ እንደ ተጋቡ ጥንዶች፣ በሲቪል ኅብረት (ሕግ) ባለው መልኩ?

መልሱ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ እያንዳንዱ በግልጽ እንደሚያውቀው ግብረ-ሰዶማዊነት ኢ-ሞራላዊና ተፈጥሯዊ ያልሆነ ነው፣ ይህንን ተፈጥሯዊ የሆነ እውቀት ለመጨቆን ብቸኛው መንገድ ግብረ-ሰዶማዊነትን ተገቢ ማድረግና እሱን የሚቃወሙትን በሙሉ ማጥቃት ነው። ግብረ-ሰዶማዊነትን ተገቢ ለማድረግ የተሻለው መንገድ የግብረ-ሰዶማውያንን ጋብቻ/የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ከተለመደው የተጻራሪ ጾታ ጋብቻ ጋር እኩል የሆነ ዕድል መስጠት ነው። ሮሜ 1፡18-32 ይህን ያመለክታል። እውነቱ የታወቀ ነው፣ እግዚአብሔር ግልጽ ስላደረገው። እውነቱ ተትቶ በውሸት ተተክቷል። ውሸቱ እንግዲህ እየተዋወቀ እውነቱ ይሸሸጋል ይጠቃልም። የተጠናከረ ተቃውሞና ቁጣ በብዙዎች የግብረ-ሰዶም መብት አስከባሪ እንቅስቃሴዎች፣ ለሚቃወሟቸው ሁሉ፣ በርግጥ የያዙት አቋም መከላከል የማይችሉት መሆኑን ያመለክታል። ደካማ የሆነውን አቋም ድምጽን በማሰማት አሸናፊ እንዲሆን መሞከር ያረጀ ብልሃት ነው፣ በክርክር መጽሐፍ። ምናልባት የተሻለ ገለጻ አይኖርም፣ ለዘመናዊው የግብረ-ሰዶማውን መብት አጀንዳ፣ ከሮሜ 1፡31 የሚበልጥ፣ “ስሜት የሌላቸው ናቸው፣ እምነት የሌላቸው፣ የማያስተውሉ፣ ምሕረት ያጡ።”

ለግብረ-ሰዶማውያን ጋብቻ/ለተመሳሳይ ጋብቻ ውሳኔ መስጠት፣ የግብረ-ሰዶማዊነትን የሕይወት ስልት ማጽደቅ ነው፣ ይኸውም መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽና በጽናት እንደ ኃጢአት የሚኮንነው። ክርስቲያኖች የግብረ-ሰዶማውያንን/የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን ተቃውመው በጽናት መቆም ይኖርባቸዋል፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ ፈጽመው ከተለዩ ዐውዶች። አንዱ ወንጌላዊ ክርስቲያን መሆን አይጠበቅበትም፣ ጋብቻ በወንድና በሴት መካከል መሆኑን እውቅና ለመስጠት።

እንደ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ጋብቻ በእግዚአብሔር የተመሠረተ ነው፣ በወንድና በሴት መካከል እንዲሆን (ዘፍጥረት 2፡21-24፤ ማቴዎስ 19፡4-6)። የግብረ-ሰዶማውያን/የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ የጋብቻ ተቋም የተገላቢጦሽ ነው፣ እንዲሁም እግዚአብሔርን መቃወም ነው፣ ጋብቻን የመሠረተውን። እንደ ክርስቲያኖች ኃጢአትን ሰበብ ልናበጅለት ወይም ችላ ልንለው አይገባም። ይልቁንም፣ የእግዚአብሔርን ፍቅርና የኃጢአትን ይቅርታ፣ ለሁሉም የሚገኘውን ልንካፈል ይገባል፣ ለግብረ-ሰዶማውያን ጨምሮ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል። እውነትን በፍቅር ልንናገር ይገባል (ኤፌሶን 4፡15) እንዲሁም ለእውነት ልንከራከር ይገባል “በጨዋነትና በአክብሮት” (1 ጴጥሮስ 3፡15)። እንደ ክርስቲያኖች ለእውነት ስንቆም፣ እና ውጤቱ የግል ጥቃት፣ ስድብ፣ እና ስደት ሲሆን የኢየሱስን ቃል ልናስታውስ ይገባል፡ “ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ እወቁ። ከዓለምስ ብትሆኑ ዓለም የራሱ የሆነውን ይወድ ነበር፤ ነገር ግን እኔ ከዓለም መረጥኋችሁ እንጂ ከዓለም ስለ አይደላችሁ ስለዚህ ዓለም ይጠላችኋል” (ዮሐንስ 15፡18-19)።

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ግብረ-ሰዶማዊነት ጋብቻ ምን ይላል/ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ?
© Copyright Got Questions Ministries