settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ምንድነው?

መልስ፤


ገላትያ 5፡22-23 ይነግረናል “የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው” በማለት። የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ፣ በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ መገኘትውጤት ነው።መጽሐፍ ቅዱስ ግልጽ እንዳደረገው፣ እያንዳንዱ መንፈስ ቅዱስን ይቀበላል፣ በኢየሱስ ክርስቶስ በሚያምንበት ወይም በምታምንበት ጊዜ (ሮሜ 8:9፤ 1 ቆሮንቶስ 12:13፤ ኤፌሶን 1:13-14)።አንደኛው ቀዳሚ የመንፈስ ቅዱስ ወደ ክርስቲያን ሕይወት የመምጣት ዓላማ ያንን ሕይወት ለመለወጥ ነው። ክርስቶስን ወደ መምሰል የሚያበጀን የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ነው፣ በተሻለ ሁኔታ እሱን እንድንመስል።

የመንፈስ ፍሬ ከኃጢአተኛ ተፈጥሮ ድርጊቶች ጋር ቀጥተኛ ተቃርኖ አለው፣ ገላትያ 5፡19-21 ላይ፣ “የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥ መዳራት፥ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኝነት፥ መለያየት፥ መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።” ይህ ምንባብ ሁሉንም ሰዎች ይገልጻል፣ በተለያየ ደረጃ፣ ክርስቶስን በማያውቁበት ጊዜ፣ እና ስለዚህ በመንፈስ ቅዱስ ተጽዕኖ ሥር አይደሉም። ኃጢአተኛ ሥጋችን የተወሰኑ ፍሬዎችን ያፈራል፣ ተፈጥሯችንን የሚያንጸባርቁ፣ መንፈስ ቅዱስም የተወሰኑ ፍሬዎችን ያፈራል፣ የእርሱን ባሕርይ/መልክ የሚያንጸባርቁ።

የክርስቲያን ሕይወት በኃጢአተኛ ሥጋችንና በክርስቶስ በተሰጠን አዲስ ተፈጥሮ መካከል የሚደረግ ውጊያ ነው (2 ቆሮንቶስ 5፡17)። እንደ ወደቀው የሰው ልጅ፣ እኛ ገና በሥጋ ወጥመድ ውስጥ ነን፣ ኃጢአተኛ ነገሮችን በሚፈልግ (ሮሜ 7፡14-25)። እንደ ክርስቲያኖች፣ መንፈስ ቅዱስ አለን፣ በውስጣችን የእርሱን ፍሬ የሚያፈራ እና የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይኖረናል፣ የኃጢአተኛ ተፈጥሮን ሥራዎች ድል ለማድረግ (2 ቆሮንቶስ 5፡17፤ ፊሊጵስዩስ 4፡13)። ክርስቲያን ፈጽሞ ሙሉ ለሙሉ ድል አድራጊ ሊሆን አይችልም፣ ዘወትር የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎችን ተግባራዊ በሚያደርግበት ጊዜ። እሱ ከክርስቲያን ሕይወት ዋነኛ ተግባራት መካከል አንዱ ነው፣ መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን የበዛና የተትረፈረፈ ፍሬውን በዳበረ መልኩ ያፈራ ዘንድ ለመፍቀድ — እንዲሁም መንፈስ ቅዱስ ተቃዋሚውን ኃጢአተኛ ፍላጎቶች ድል እንዲያደርግ ለመፍቀድ። የመንፈስ ፍሬዎች ማለት እግዚአብሔር በሕይወታችን እንዲገለጥ/ማስረጃ እንዲሆን የሚፈልገው ነው፣ እናም በመንፈስ ቅዱስ ርዳታ ይቻላል!

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ምንድነው?
© Copyright Got Questions Ministries