settings icon
share icon
ጥያቄ፤

አራቱ መንፈሳዊ ህጎች ምንና ምን ናቸው?

መልስ፤


አራቱ መንፈሳዊ ህጎች በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘውን የድነት መልካም የምስራች የምንካፈልበትን መንገድ የሚያመለክቱ ናቸው። በወንጌል የሚገኘውን ጠቃሚ ዜና በአራት ነጥቦች በቀላሉ የሚቀርብበት ዘዴ ነው።

ከአራቱ መንፈሳዊ ህጎች ቀዳማይ የሆነው “ እግዚሐብሔር ይወድሃል፣ ለሕይወትህም አስደናቂ እቅድ አለው” የሚለው ነው። ዮሐ 3፡16 እንዲህ ይላል “ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚሐብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” ዮሐ 10፡10 ኢየሱስ የመጣበትን ምክንያት ሲያብራራ፡ “እኔ ህይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ” ይላል። ከእግዚሐብሔር ፍቅር የሚያግደን ማነው? ሕይወትስ እንዳይበዛልን የሚከለክለን ምንድ ነው?

ከአራቱ መንፈሳዊ ህጎች ሁለተኛው “የሰው ልጅ በኃጢያት የወደቀ ስለሆነ ከእግዚሐብሔት ተለይቷል” ይላል። ከዚህም የተነሳ እግዚሐብሔር ለኛ ህይወት ያለውን አስደናቂ ዕቅድ ማወቅ አልቻልንም። በሮሜ 3፡23 ይህንን የሚያጠናክር ሃሳብ አለ፡ “ሁሉም ኃጢያት ሰርተዋል፤ የእግዚሐብሔርም ክብር ጎድሏቸዋል።” ሮሜ 6፡23 የኃጢያትን ውጤት ያስገነዝበናል። “የኃጢያት ዋጋ ሞት ነው።” እግዚሐብሔር እኛን የፈጠረን ከርሱ ጋር ህብረት እንድናደርግ ነው። ስለሆነም የሰው ልጅ ኃጢያትን ወደዚህ ዓለም አመጣ፣ ስለዚህም ከእግዚሐብሔር ተለየ። እኛ ከእግዚሐብሔር ጋር ሊኖረን የሚገባውን ግንኙነት አበላሽተነዋል። መፍትሔው ምንድ ነው?

ሦስተኛው መንፈሳዊ ህግ፡ “ለኃጢያታችን ክፍያ ወይም ካሳ እግዚሐብሔር ያቀረበው ብቸኛ ነገር ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ የሚል ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ኃጢያታችን ይቅር ተብሎልን ከእግዚሐብሔር ጋር የሚኖረን ትክክለኛ ግንኙነት ይታደስልናል።” ሮሜ 5፡8 እግዚሐብሔር ለኛ ያለውን ፍቅር ሲያረጋግጥልን እንዲህ ይነግረናል፡ “ነገርግን ገና ኃጢያተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለኛ ሞቷአልና።” ድነታችንን ለማረጋገጥ ምን ማወቅ እንዳለብንና ማመን እንደሚገባን 1ኛ ቆሮ 15፡ 3-4 እንዲህ ያስረዳናል “…መጽሐፍም እንደሚል ክርስቶስ ስለኃጢያታችን ሞተ፣ተቀበረም። መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሳ።” የድነት ብቸኛ መንገድ መሆኑን ራሱ ኢየሱስ በዮሐንስ 14፡ 6 “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ። በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም” ሲል ተናግሯል። ይህንን የድነት አስደናቂ ስጦታ እንዴት ላገኘው እችላለሁ?

አራተኛው መንፈሳዊ ህግ ደግሞ እንዲህ ይቀርባል። “ የድነትን ስጦታ ለመቀበልና እግዚሐብሔር ለህይወታችን ያለውን አስደናቂ እቅድ ለማወቅ እምነታችንን በኢየሱስ ክርስቶስ መጣልና አዳኝነቱን ማወቅ አለብን።” ዮሐንስ 1፡ 12 በዚህ ሁኔታ ያብራራዋል፡ “ለተቀበሉት ሁሉ ግን፣ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚሐብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣን ሰጣቸው።” የሐዋርያት ሥራ 16፡ 31 በግልፅ እንዲህ ያስቀምጠዋል፣ “በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተሰቦችህም ትድናላችሁ።” እኛ የምንድነው በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ባለን እምነትና በፀጋው ነው(ኤፌሶን 2፡ 8-9)

ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኝህ አምነህ ለመቀበል ከፈለግህ እነዚህን ቃላት በእግዚሐብሔር ፊት ተናገር። እነዚህን ቃላት ስትናገር ድነት አታገኝም። በክርስቶስ ያለህ እምነት ብቻ ይህንን ያስገኝልሐል። ይህንን ፀሎት እግዚሐብሔር ድነትን ስለሰጠህ እምነትህን ለርሱ ለመግለጽና ምስጋናህን የምታቀርብበት ቀላሉ መንገድ ነው። “እግዚሐብሔር ሆይ እኔ ባንተ ላይ ኃጢያት ፈጽሜአለሁ፣ ቅጣትም ይገባኛል፤ ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስ እኔ መቀበል የነበረብኝን ቅጣት ከፍሎልኛል። በርሱ ባለኝ እምነትም ይቅርታ ተደርጎልኛል። ለድነቴ እምነቴን ባንተ ላይ አኖራለሁ። የዘላለም ሕይወት ስጦታ ስለሰጠኸኝ፣ ስለአስገራሚው ፀጋህና ይቅርታህ አመሰግንሐለሁ! አሜን!”

ኢየሱስ ክርስቶስን እንደግል አዳኝህ በመቀበል ዳግም ልትወለድ ከፈለግህ የሚከተለውን ፀሎት አብረኸን ፀልይ። አስታውስ ይህንን ፀሎት ወይም ሌላ አይነት ፀሎት ማቅረብ አያድንህም። ከኃጢያት የምትድነው በኢየሱስ ክርስትስ ብቻ ስታምን ነው። ይህ ፀሎት እግዚሐብሔር ድነትን ስለሰጠህ በርሱ መታመንህን ለማሳየትና ምስጋና ማቅረብ እንደሚገባህ የሚያመለክትህ ቀላል መንገድ ነው። “እግዚሐብሔር ሆይ አንተን ስለበደልኩ ቅጣት ይገባኛል። ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኔ የሚገባውን ቅጣት ስለከፈለልኝ በርሱ በማመኔ ይቅርታ ተደርጎልኛል፤ በምህረትህ እታመናለሁ፤ ስለአስደናቂው ፀጋህ እንዲሁም ስለዘላለም ሕይህወት ስጦታህ አመሰግንሐለሁ! አሜን!

እዚህ ባነበብከው ምክንያት ለክርስቶስ ውሳኔ ላይ ደርሰሃል? እንዲያ ከሆነ፣ “ዛሬ ክርሰቶስን ተቀብያለሁ” የሚለውን ቁልፍ ተጫን

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

አራቱ መንፈሳዊ ህጎች ምንና ምን ናቸው?
© Copyright Got Questions Ministries