settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጸሐፍ ቅዱስ ከርስቲያ ወደ ብድር ለመበደር ስለመሄዱ ምን ይላል?

መልስ፤


ጳውሎስ ከፍቅር በቀር ምንም እዳ እንዳይኖርብን እግዚአብሔር በምንም አይነት መልኩ በትክክለኛ ጊዜ ያልተከፈለ የተኛውንም አይነት አዳ እንዳይኖርብን ያስታውሰናል (ሮሜ 13፡8) (መዝ 37፡21)፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ እግዚአብሔር በግልጽ ሁኔታ ሁሉንም አይነት በድር አልከለከለለም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ብድርን በመቃወም ያስጠነቅቃል፤ እና ወደ ብድር አለመሄድን ያበረታታል ግን ብድርን አልከለከለም፡፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በእዳ የያዙአቸውን ተበዳሪዎችን ለሚያሰቃዩ ጠንካራ የፍርድን ቃል ይናገራል ግን ተበዳሪዎችን አይፈርድባቸውም፡፡

ሌላው አንዳነድ ሰዎች በብድር ስላለው ወለድ ይጠይቃሉ ግን አገባብ ያለው ወለድ በብድር ከተገኘ ገንዘብ መውሰድ በመጸሐፍ ቅዱስ የሚጠበቅ ሊሆን የሚችል እንደሆነ እናያለን፡፡(ምሳ 28፡4፤ ማቲ 25፡27)፡፡ በጥንታዊ እስራኤል ህጉ በአንድ ነገር ላይ ብቻ ወለድን ይከለክላል እርሱም ከድሆች (ዘሌ 25፡35-38)፡፡ ህጉ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና መንፈሳዊ ጠቋሚዎች አሉት፤ ሁለቱን ግን በተለይ ማንሳት አስፈላጊ ነው፡፡ በመጀመሪያ ህጉ ድሆች የሆኑ የባሰ ችግር ውስጥ እንደይገቡ ያደርጋል፡፡ በድህነት ወስጥ መውደቃቸው የከፋ መጥፎ ነገር መሆኑ ሳያንስ እነደገና እርዳታን መፈለጋቸው እጅግ የሚያሳፍራቸው ነው የሚሆነው፡፡ ግን በተጨማሪ ብድርን መልሶ ለመከፈል ቢሆን ድሃው የማይችለውን ወለድ መክፈል አለበት ይህ ደግሞ ህጉ ከሚጠቅመው ይልቅ የሚጎዳው ይሆናል፡፡

ሁለተኛ ህግ አስፈላጊ የሆነ መንፈሳዊ ትምህርትን ያስገነዝባል፡፡ ለአበዳሪ ከአበደረው ላይ ወለዱን ማንሳት ምህረት ማድረግ ነው፡፡ በድሩን ባበደረበት ሰዓት ከገነዘቡ ሊያገኝ የሚችለውን ጥቅም ያጣል፡፡ ይሁን እንጂ እዳቸውን ሳይቆጥር ለህዝቡ ስለበዛው ምህረቱ እግዚአብሔርን ለማመስገን ተጨባጭ መንገድ ሊሆን ይችላል፡፡ እግዚአብሔርን ልክ እስራኤላዊያንን በምህረቱ ከገብጽ ባርነት ነጻ እንዳወጣቸው እንዲሁ በጭቆና በባርነት ውስጥ ሆነው የራሳቸውን ምድር ሰጣቸው (ዘሌ25፡38) ተመሳሳይ የሆነን ቸርነትን ለሃገራቸው ህዝቦች እንዲያሳዩ ይፈልጋል፡፡

ክርስቲያኖች ትይዩ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ነው ያሉት፤ የክርስቶስ ኢየሱስ ህይወት ሞትና ትንሳኤ ለእግዚአብሔር የኃጢያታችንን እዳ ከፍሎልናል፡፡ እኛም እድሉ ካለን ሌሎች በችግር ውስጥ ያሉትን በተለይ አማኞችን በብድር ጭንቀት መውጣት ያልቻሉትን መርዳት እንችላለን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ መስመር ላሉ ስለ ምህረት ያላቸወችን አመለካከት በሚመለከት ምሳሌን ተናግሮአል (ማቲ 18፡23-35)፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ገንዘብ መበደርን በግልጽ አልከለከለም ወይንም አልኮነኮነም፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥበብ ሲያስተምረን በአብዛኛው ጊዜ ወደ ብድር መሄድ ጥሩ ልምድ አይደለም፡፡ በድር በመሰረቱ ላበደረን ሰው ባሪያዎች ያደርገናል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በአንዳንድ ሁኔታዎች ወደ ብድር መሄድ ክፉ አይደለም፡፡ ገንዘብ በጥበብ እስከተያዘ እና በድሩ በስርአት ጥቅም ላይ ከዋለ ክርስቲያኖች የብድር ኃላፊነት የግድ አስፈላጊ ሲሆን መግባት ይችላሉ፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጸሐፍ ቅዱስ ከርስቲያ ወደ ብድር ለመበደር ስለመሄዱ ምን ይላል? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries