settings icon
share icon
ጥያቄ፤

አማኝ መንፈስ ቅዱስ እንደሚሰማው መገመት ይችላልን?

መልስ፤


አንዳንድ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች ስሜትን ሊያካትቱ ይችላሉ፣ ለአብነትምየኃጢአኝነት ፍርድ፣ መጽናናት፣ እና ኃይልን መሞላት፣ ቅዱስ ቃሉ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለን ግንኙነት እንዴት ወይም ምን እንደሚሰማን በሚለው ላይ እንዲመሠረት አያዘንም። እያንዳንዱ ዳግም የተወለደ አማኝ የሚያድርበት መንፈስ ቅዱስ አለው። ኢየሱስ ነግሮናል፣ አጽናኙ ሲመጣ፣ እሱ ከእኛ ጋር እና በእኛ ውስጥ ይሆናል። “እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውስጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ” (ዮሐንስ 14፡16-17)። በሌላ አባባል ኢየሱስ እሱን የመሰለውን ይልክልናል፣ ከእኛ ጋር እና በእኛ ውስጥ እንዲሆን።

መንፈስ ቅዱስ ከእኛ ጋር መሆኑን እናውቃለን፣ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል እንደዛ እንደሆነ ስለሚነግረን። እያንዳንዱ ዳግም ልደት ያገኘ ክርስቲያን መንፈስ ቅዱስ ያድርበታል፣ ነገር ግን እያንዳንዱ አማኝ በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር አይደለም፣ እናም ትርጕም ያለው ልዩነት አለ። በሥጋችን በወጣን ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር አይደለንም፣ ምንም እንኳ የእርሱ ማደሪያዎች ብንሆንም። ሐዋርያው ጳውሎስ በእውነታው ላይ የሚለው አለ፣ እሱም መረዳት እንድንችል ማሳያ/ማብራሪያ ይጠቀማል። “መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና” (ኤፌሶን 5፡18)። ብዙ ሰዎች ይሄንን ቁጥር የሚያነቡትና የሚተረጉሙት ሐዋርያው ጳውሎስ የወይን ጠጅን በመቃወም እንደተናገረው አድርገው ነው። ሆኖም፣ የዚህ ምንባብ ዐውደ-ጽሑፍ የሚለው መንፈስ የተሞላ አማኝ ርምጃና ውጊያ ነው። ስለዚህ፣ እዚህጋ የወይን ጠጅን በብዛት ስለመጠጣት ከማስጠንቀቂያ ይልቅ የበለጠ ነገር አለው።

ሰዎች ብዙ የወይን ጠጅ ጠጥተው ሲሰክሩ አንዳንድ ባሕርያት ይታዩባቸዋል፡ ግርማቸውን ያጣሉ፣ ንግግራቸው ይተሳሰራል፣ ፍርዳቸው የማይረባ ይሆናል። ሐዋርያው ጳውሎስ እዚህጋ ማነጻጸሪያ ያስቀምጣል። እዚያጋ በብዙ የወይን ጠጅ ቁጥጥር ሥር የሆነ አንዱን የሚገልጹ የተወሰኑ ባሕርያት እንዳሉ፣ እንዲሁ ደግሞ የተወሰኑ ባሕርያት ይኖራሉ፣ በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር የሆነ አንዱ የሚለይበት። ገላትያ 5፡22-24 ላይ ስለ መንፈስ ፍሬዎች እናነባለን። ይህ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ነው፣ እሱም ዳግም ልደትን ባገኘ አማኝ ላይ የሚታዩ፣ በእርሱም ቁጥጥር ሥር የሆነ።

ኤፌሶን 5፡18 ላይ የግሡ ጊዜ የሚያመለክተው በመንፈስ ቅዱስ “የመሞላትን” ቀጣይነት ሂደት ነው። እሱም ማሳሰቢያ/ማግባቢያ እስከሆነ ድረስ፣ እሱን ተከትሎ በመንፈስ አለመሞላት ወይም ቁጥጥር ሥር አለመሆን ይቻላል። ቀሪው ኤፌሶን 5 በመንፈስ የተሞላ አማኝን ባሕርያት ይሰጠናል። “በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ፤ ሁልጊዜ ስለ ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንንና አባታችንን ስለ ሁሉ አመስግኑ። ለእያንዳንዳችሁ በክርስቶስ ፍርሃት የተገዛችሁ ሁኑ” (ኤፌሶን 5፡19-21)።

በመንፈሱ የተሞላን አንሆንም፣ እንደተሞላን ቢመስለንም እንኳ፣ ነገር ግን ይህ የክርስቲያን ዕድል ፈንታ እና ውርስ ነው። በመንፈስ መሞላትና ቁጥጥር ሥር መሆን ከጌታ ጋር በመታዘዝ የመጓዝ ውጤት ነው። ይህ የጸጋ ስጦታ ነው እንጂ የስሜታዊነት ስሜት አይደለም። ስሜቶች ሊያስቱን ይችላሉ፣ እኛም ራሳችን በስሜታዊነት አእምሮን በሚያናውጥ ሁኔታ ውስጥ ልንገኝ እንችላለን፣ እሱም በግልጽ ከሥጋ የሆነ፣ ከመንፈስ ቅዱስ ሳይሆን። “ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ… በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ” (ገላትያ 5፡16፣ 25)።

ይሄንን ካልን በኋላ፣ በመንፈስ ኃይል መገኘት ውስጥ የምንጥለቀለቅበት ጊዜያት ሊኖር እንደሚችል መካድ አንችልም፣ ይህም ዘወትር ስሜታዊ ልምምድ ነው። ያ ሲሆን፣ እንደ ሌላው ዓይነት ደስታ አይደለም። ንጕሥ ዳዊት “በሙሉ ኃይሉ ጨፈረ” (2 ሳሙኤል 6፡14) የኪዳኑን ታቦት ወደ ኢየሩሳሌም በሚያመጡበት ጊዜ። በመንፈስ የሆነ ደስታን መለማመድ እንደ እግዚአብሔር ልጆች በእርሱ ጸጋ መባረካችንን መረዳት ነው፤ ስለዚህ፣ ፍጹም በሆነ መልኩ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት የእኛን ስሜትና ቀልብ ያካትታል። በተመሳሳይ ጊዜ፣ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የመሆናችንን ዋስትና እንዴት እንደሚሰማን በሚለው ላይ መመሥረት አይኖርብንም።

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

አማኝ መንፈስ ቅዱስ እንደሚሰማው መገመት ይችላልን?
© Copyright Got Questions Ministries