settings icon
share icon
ጥያቄ፤

እኔ እንዴት ሐሰተኛ መምህራንና ሐሰተኛ ነብያትን መለየት እችላለው?

መልስ፤


ኢየሱስ ክርስቶሰ ሐሰተኛ ክርስቶሶችና ሐሰተኛ ነብያት እንደሚመጡና የተመረጡትን እንኳ ሊያስቱ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል (ማቲ 24:23-27; እንዲሁም 2 ጴጥ 3:3 እና ይሁዳ 17-18). ከሐሰተኛ ልምምድ ከስህተት አሰተምህሮ ራስህን የምትጠብቅበት ትልቁ መንገድ እውነትን ማወቅ ነው፡፡ አስመስሎ የተሰራውን ውሸት ለይቶ አውቆ ለመቃወም እውነተኛውን ማወቅ፡፡ ማንኛውም አማኝ እውነትን ‹‹በትክክል የያዘ›› (2 ጢሞ 2:15) እና ቃሉን በጥንቃቄ የሚያጠና ሐሰተኛ አስተምህሮን ለይቶ ማወቅ ይችላል፡፡ ለምሳሌ በማቲ 3፡16-17 ያለውን የአባትነት(የእግዚአብሔርን) የልጅ (የኢየሱስ ክርስቶስን) እና የመንፈስ ቅዱስን ስራ ያነበበ ሰው ማንም የስላሴን ትምህርት ቢክድ ወዲያውኑ ጥያቄን ይጠይቃል፡፡ እንግዲያው የመጀመሪያው እርምጃ መጽሐፍ ቅዱስ በማጥናት ሁሉንም ትምህርት ቃሉ እንደሚለው መዳኘት ነው፡፡

ኢየሰስ እንዲህ ብሎአል ‹‹ዛፍ በፍሬው ይታወቃል›› (ማቲ 12:33). ፍሬን በሚለከት ማንኛውም አስተማሪ የትምህርቱን ተክክለኝነት ለመመዘን ሊጠቅምባቸው የሚችልባቸው ሶስት መመዘኛዎች፡-

1) ይህ አስተማሪ ስለ ኢየሱስ ምን አለ? በማቲ 16፡15-16 ኢየሱስ ‹‹ስለ እኔ ምን ትላላችሁ‹‹ ብሎ ጠየቀ፤ ጴጥሮስ ሲመልስ ‹‹አንተ የህያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ›› አለ፡፡ ጴጥሮስ ለዚህ መልሱ የተባረክህ ነህ ተባለ፡፡ በ 2ኛ ዮሐ 9 ይህን እናነባለን፡- ‹‹ ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት።›› በሌላ አባባል ኢየሱስ ክርስቶስና የእርሱ የመዋጀት ስራ የመጨረሻው ዋና ነገር ነው፡ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋረ እኩል አይደለም ብሎ የሚክደውን የኢየሱስን የመስዋዕትነት ሞት የሚያቃልለውን የኢየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን የሚቃወመውን ነቅተን እንጠብቀው፡፡ 1ኛ ዮሐ 2፡22፡- ‹‹ክርስቶስ አይደለም ብሎ ኢየሱስን ከሚክድ በቀር ውሸተኛው ማን ነው? አብንና ወልድን የሚክድ ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።››

2) ይህ አስተማሪ ወንጌልን ነው የሚሰብከው? እንደ እግዚአብሔር ቃል የወንጌል ትርጓሜ የኢየሱስ ሞት መቀበር እና መነሳት መልካም ወሬ ነው(1 ቆሮ 15:1-4)፡፡ መልካም ጥሩ ቢመስሉም ‹‹እግዚአብሔር ይወድሃል›› ‹‹እግዚአብሔር የተራቡትን እንድናበላ ይፈልጋል›› እና ‹‹እግዚአብሔር ባለጠጋ እንድትሆን ይፈልጋል›› የሚሉ አረፍተ ነገሮች ሙሉ የወንጌል መልዕክት አይደሉም፡፡ ጳውሎስ በገላቲያ 1፡7 አስጠንቅቆአል፡- ‹‹እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ።›› ማንም ሰው ምንም አይነት የታወቀ ሰባኪ እግዚአብሔር የሰጠንን መልዕክተ መለወጥ መብት የለውም፡፡ ገላ 1፡9፡- ‹‹አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።››

3) ይህ አስተማሪ እግዚአብሔርን የሚያከብር ባሕሪ ይታይበታል? ስለ ሐሰተኛ አስተማሪዎች ይሁዳ 11 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ወዮላቸው፥ በቃየል መንገድ ሄደዋልና ስለ ደመወዝም ለበለዓም ስሕተት ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል በቆሬም መቃወም ጠፍተዋል።›› በሌላ አባባል የሐሰተኛ አስተማሪ በትእቢት ተለይቶ ይተወቃል፤ (ቃየን የእግዚአብሔርን እቅድ ተቃወመ) ስስታምነት (በልአም ለገንዘብ ብሎ ተነበየ) አመጽ (የቆሬ ልጆች ራሳቸውን ከሙሴ በላይ ከፍ ማድረግ ፈለጉ) ኢየሱስ ክርስቶስ ከእነዚህ ሰዎች እንዲጠበቁ እና በፍሬያቸው እንደሚታወቁ ተናግሮአል፡፡ (ማቲ 7፡15-20)

ለተጨማሪ ጥናት በቤተክርስቲያን ውስጥ የስህተት አስተምሮዎችን ለመወጋት የተጻፉ የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍትን እንደነዚህ ያሉትን ተመልከቱ ገላቲያ፤2ኛ ጴጥ፤ 1ኛ ዮሐ፤ 2ኛ ዮሐ፤ እና ይሁዳ፡፡ በአብዛኛው የሐሰተኛ ነብያትን ትንቢት ለይቶ ማወቅ አስቸጋሪ ነው፡፡ ሰይጣን ራሱን የብርሃን መልአክ እስኪመስል ራሱን ይለውጣል(2 ቆሮ 11:14) የእርሱ አገልጋዮች የጽድቅ አገልጋዮች መስለው ራሳቸውን ይለውጣሉ (2 ቆሮ 11:15)፡፡ ከእውነት ጋር በመቀራረብ ብቻ ማስመሰሉን ልንለየው እንችላለን፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

እኔ እንዴት ሐሰተኛ መምህራንና ሐሰተኛ ነብያትን መለየት እችላለው?
© Copyright Got Questions Ministries