settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ዘላለማዊ ዋስትና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው?

መልስ፤


ሰዎች ክርስቶስን እንደ አዳኛቸው ወደ ማወቅ ሲመጡ የዘላለማዊ ዋስትናቸውን አስተማማኛ ወደሚያደርግ ከእግዚአብሔር ጋር ወደሆነ ህብረት መጥቷል፡፡ የይሁዳ መልዕክት 24 “ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ፥ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚችለው” እያለ ያውጃል፡፡ የእግዚአብሔር ኃይል አማኞችን ከውድቀት ሊጠብቃቸው ይችላል፡፡ እኛን በክብሩ ፊት ማቆም የእሱ እንጂ የእኛ ፈንታ አይደለም፡፡ የእኛ ዘላለማዊ ዋስትና እግዚአብሔር እኛን የመጠበቁ ውጤት እንጂ እኛ የራሳችንን ድነት የማቆየቱ ጉዳይ አይደለም፡፡

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ “እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም። የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም።” (የዮሐንስ ወንጌል 10፤28-29) አብም ኢየሱስም ሁለቱም በእጃቸው ውስጥ አጥብቀው ይዘውናል፡፡ ከአብ እና ከልጁም ከሁለቱም እጅ ውስጥ ሊለየን የሚችል ማነው?

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፤30 አማኞች “ለቤዛ ቀን እንደታተሙ” ይነግረናል፡፡ አማኞች ዘላለማዊ ዋስትና ካልነበራቸው በእውነት ማህተሙ ለቤዛ ቀን ሊሆን አይችልም ነገር ግን ኃጥአት ለሚደረግበት ፤ክህደት ወይም አለማመን ቀን ብቻ ይሆናል፡፡ በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያምን ማንም ሰው “የዘላለም ህይወት እንዳለው” የዮሐንስ ወንጌል 3፤15-16 ይነግረናል፡፡ አንድ ግለሰብ ዘላለማዊ ህይወት ተስፋ የተገባው ከሆነ ነገር ግን ደግሞ ቢወሰድበት ለመጀመር ያህል ፈጽሞ “ዘላለማዊ” አልነበረም፡፡ መንፈሳዊ ዋስትና እውነት ካልሆነ በመጽሐፍ ቅዱ ውስጥ ያሉ የዘላለም ህይወት ተስፋዎች ስህተት ይሆናሉ፡፡

ለዘላለማዊ ዋስትና በጣም ኃይለኛው ክርክር ሮሜ 8፤38-39 ነው፤ “ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።” የእኛ ዘላለማዊ ዋስትና እርሱ ለተበዣቸው መሠረት ያደረገው በእግዚአብሔር ፍቅር ላይ ነው፡፡ የእኛ ዘላለማዊ ዋስትና በክርስቶስ ተገዛ፤ በአብ ተስፋ ተገብቷል፤ እና በመንፈስ ቅዱስ ታትሟል፡፡

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ዘላለማዊ ዋስትና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው?
© Copyright Got Questions Ministries