settings icon
share icon
ጥያቄ፤

በፍጻሜው ዘመን ትንቢት መሠረት ምን ይሆናል?

መልስ፤


መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፍጻሜው ዘመን ብዙ የሚለው አለ። ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ሊባል በሚችል መልኩ ስለ ፍጻሜው ዘመን ትንቢት ይዟል። እነዚህን ሁሉ ትንቢቶች ወስዶ ማደራጀት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ቀጥሎ የተመለከተው በጣም አጭር የሆነ አጠቃሎሽ ነው፣ መጽሐፍ ቅዱስ በመጨረሻው ዘመን ምን እንደሚሆን ያወጀበት።

ክርስቶስ ዳግም የተወለዱትን አማኞች ሁሉ ከምድር ላይ ይወስዳል፣ መነጠቅ በሚባለው ሁነት (ተሰሎንቄ 4:13-18፤ 1 ቆሮንቶስ 15:51-54)። በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት፣ እነዚህ አማኞች ይሸለማሉ፣ ስለ መልካም ሥራቸውና ስለ ታመነ አገልግሎታቸው፣ በምድር ላይ በነበሩበት ጊዜ፣ ወይም አይሸለሙም፣ ግን የዘላለም ሕይወትን አይደለም፣ ከአገልግሎት እና ከመታዘዝ ማነስ (1 ቆሮንቶስ 3:11-15፤ 2 ቆሮንቶስ 5:10)።

የክርስቶስ ተቃዋሚው (አውሬው) ወደ ሥልጣን ይመጣል፣ ከእስራኤል ጋርም ለሰባት ዓመት ቃል ኪዳን ይገባል (ዳንኤል 9፡27)። ይህ የሰባት ዓመት ጊዜ “ታላቁ መከራ” በሚል ይታወቃል። በታላቁ መከራ ጊዜ አስፈሪ የሆነ ጦርነት ይካሄዳል፣ ራብ፣ ቸነፈር፣ እና የተፈጥሮ ጥፋቶች። እግዚአብሔር በኃጢአት፣ በክፉ፣ እና በክፋተኝነት ላይ መዓቱን ያፈስሳል። መከራው፣ ራዕይ ላይ ያሉትን አራቱን ፈረሰኞች፣ እና ሰባቱን ማኅተም፣ መለከት፣ እና የፍርድ ማሳያ ትዕይንቱንም ያካትታል።

በሰባቱ ዓመት ሂደት አጋማሽ ላይ፣ የክርስቶስ ተቃዋሚው ከእስራኤል ጋር የገባውን ቃል ኪዳን ያፈርስና ጦርነት ያካሂዳል። የክርስቶስ ተቃዋሚው “የጥፋት ርኵሰትን” ይፈጽማል፣ የራሱምን ምስል አበጅቶ በኢየሩሳሌም ቤተ-መቅደስ እንዲሰገድ ያደርጋል (ዳንኤል 9፡27፤ 2 ተሰሎንቄ 2፡3-10)፣ እሱም ዳግመኛ የተገነባው። የመከራው ሁለተኛው አጋማሽ “ታላቁ መከራ” በመባል ይታወቃል (ራዕይ 7፡14) እና “የያዕቆብ የመከራ ጊዜ” (ኤርምያስ 30፡7)።

በመከራው ሰባተኛ ዓመት መጨረሻ ላይ፣ የክርስቶስ ተቃዋሚ በኢየሩሳሌም ላይ የመጨረሻ ጥቃቱን ይከፍታል፣ በአርማጌዶን የመጨረሻ ውጊያ። ኢየሱስ ክርስቶስ ይመለሳል፣ የክርስቶስን ተቃዋሚና ሠራዊቱን ይደመስሳል፣ ወደ እሳት ባሕርም ይጥለዋል (ራዕይ 19፡11-21)። ከዚያም ክርስቶስ በጥልቁ ሰይጣንን ለ1000 ዓመት ያስረዋል፣ እናም በዚህ አንድ ሺ ዓመት ጊዜ በምድር ላይ መንግሥቱ ይገዛል (ራዕይ 20፡1-6)።

በአንድ ሺ ዓመቱ መጨረሻ ላይ ሰይጣን ይፈታል፣ እንደገናም ይሸነፋል፣ ከዚያም ወደ እሳት ባሕር ይጣላል (ራዕይ 20፡7-10) ለዘላለም። ከዚያም በማያምኑት ሁሉ ላይ ይፈርዳል (ራዕይ 20:10-15) በታላቁ ነጭ የፍርድ ዙፋን ላይ ሆኖ፣ ወደ እሳት ባሕር ይጥላቸዋል። ከዚያም ክርስቶስ በአዲሱ ሰማይና በአዲሱ ምድር እና በአዲሲቷ ኢየሩሳሌም ይገለገላል— የአማኞች የዘላለም መኖርያ ስፍራ። ከዚያም በኋላ ኃጢአት አይኖርም፣ ኀዘንም፣ ወይም ሞት (ራዕይ 21-22)።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

በፍጻሜው ዘመን ትንቢት መሠረት ምን ይሆናል?
© Copyright Got Questions Ministries