settings icon
share icon
ጥያቄ፤

በተሰጥዖ እና በጸጋ ስጦታ መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው?

መልስ፤


በተሰጥዖ እና በመንፈሳዊ ስጦታ መካከል ተመሳሳይነቶችና ልዩነቶችአሉ። ሁለቱም ከእግዚአብሔር የሆኑ ስጦታዎች ናቸው። ሁለቱም በውጤታማነት እያደጉ የሚሄዱት በአጠቃቀም (በተግባር) ነው። ሁለቱም ጥቅም ላይ የሚውሉት ከሌሎች አኳያ ታሳቢ በማድረግ ነው፣ ለግል ዓላማ ሳይሆን። አንደኛ ቆሮንቶስ 12፡7 እንዳስቀመጠው፣ መንፈሳዊስጦታዎች የሚሰጡት ሌሎችን ለመጥቀም ነው፣ ራሳችንን ሳይሆን። ሁለቱ ታላላቅ ትዕዛዛት የሚሉት እግዚአብሔርንና ሌሎችን መውደድ ነው፣ ይህንን ተከትሎ አንዱ ተሰጥዖውን መጠቀም የሚኖርበት ለእነዚህ ዓላማዎች መሆን ይኖርበታል። ነገር ግን ለማንና መቼ ነው ተሰጥዖና መንፈሳዊ ስጦታዎች እንደሚሰጡይለያያሉ። ግለሰብ (በእግዚአብሔር ወይም በክርስቶስ ላይ ያለው እምነት ምንም ዓይነት ቢሆን) የተፈጥሮ ስጦታ ይሰጠዋል፣ ከጀነቲክ (አንዳንዶች በሙዚቃ፣ በኪነ ጥበብ፣ ወይም በሒሳብ) እና ከአካባቢያቸው (ሙዘቀኛ በሆነ ቤተሰብ ማደግ አንዱን የሙዚቃ ተሰጥዖውን ሊያጎለብትለት ይችላል)፣ ወይም እግዚአብሔር የተለዩ ግለ ሰቦችን በተወሰነ ተሰጥዖ ኃይል ሊያስታጥቃቸው ይችላል (ለምሳሌ፣ ባስልኤል ዘጸአት 31፡1-6)። መንፈሳዊ ስጦታዎች ለሁሉም አማኞች በመንፈስ ቅዱስ ይሰጣሉ (ሮሜ 12፡3፣ 6) በክርስቶስ ላይ እምነታቸውን በጣሉ ጊዜ፣ ለኃጢአታቸው ስርየት። በዛን ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ለዛ አዲስ አማኝ መንፈሳዊ ስጦታ(ዎች) ይሰጠዋል፣ አማኙ እንዲኖረው የፈቀደውን (1 ቆሮንቶስ 12፡11)።

ሮሜ 12፡3-8 መንፈሳዊ ስጦታዎችን በሚከተለው መልኩ ይዘረዝራል፡ ትንቢት መናገር፣ ሌሎችን ማገልገል (በአጠቃላይ መልኩ)፣ ማስተማር፣ መምከር፣ መስጠት፣ መምራት፣ እና መማር (ምሕረት ማድረግ)። አንደኛ ቆሮንቶስ 12፡8-11 ስጦታዎችን እንደ ጥበብ ቃል ይዘረዝራል (መንፈሳዊ ጥበብን የማስተላለፍ ችሎታ)፣ የእውቀት ቃል (ተግባራዊ እውነትን የማስተላለፍ ችሎታ)፣ እምነት (በእግዚአብሔር ላይ በተለየ መልኩ መታመን)፣ ተአምራትን ማድረግ፣ ትንቢት መናገር፣ መናፍስትን መለየት፣ ልሳናት (የማያውቀውን ቋንቋ የመናገር ችሎታ)፣ ልሳናትን መተርጎም። ሦስተኛው ዝርዝር የሚገኘው ኤፌሶን 4፡10-12 ላይ ሲሆን፣ እሱም የሚናገረው እግዚአብሔር ለቤተ-ክርስቲያኑ ሐዋርያትን፣ ነቢያትን፣ ወንጌላውያንን፣ እና እረኞችንና አስተማሪዎችን መስጠቱን ነው። ምን ያህል የጸጋ ስጦታዎች እንዳሉ ደግሞ ጥያቄ አለ፣ ልክ ሁለት ዝርዝሮች ተመሳሳይ እንደማይሆኑ። ደግሞም የመጽሐፍ ቅዱስ ዝርዝሮች የተጠቃለሉ አይደሉም፣ ማለትም ሌሎች ተጨማሪ መንፈሳዊ ስጦታዎች ይኖራሉ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ከጠቀሰው በላይ።

አንዱ ምናልባት ተሰጥዖውን አዳብሮ ኋላም ሙያውን ወይም ዝንባሌውን በእነዚህ መስመሮች ላይ ሲያደርግ፣ መንፈሳዊ ስጦታ በመንፈስ ቅዱስ ይሰጣል፣ የክርስቶስን ቤተ-ክርስቲያን ለማነጽ። በዚያም፣ ሁሉም ክርስቲያኖች የክርስቶስን ወንጌል ለማሰራጨትንቁ ድርሻ ይጫወታሉ።ሁሉም የተጠሩትና ብቁ የሆኑት “በአገልግሎት ተግባር” ላይ እንዲሳተፉ ነው (ኤፌሶን 4፡12)። ሁሉም ተሰጥዖ አላቸው፣ ለክርስቶስ ጉዳይ አስተዋጽዖ ማድረግ እንዲችሉ፣ እሱ ለእነርሱ ላደረገው ሁሉ ከምስጋና የተነሣ። ይህን በማድረግም በሕይወት ፍጻሜን ማግኘት ይችላሉ፣ ለክርስቶስ በሚያደርጉት ተግባር። እሱም የቤተ-ክርስቲያን መሪዎች ሥራ ነው፣ ቅዱሳንን ለማብቃት በመርዳት ረገድ፣ እግዚአብሔር ለጠራቸው አገልግሎት በተሻለ ብቁ መሆን እንዲችሉ። የመንፈሳዊ ስጦታዎች ታሳቢ ውጤት፣ ቤተ-ክርስቲያን በሙላትዋ እንድታድግ ነው፣ በእያንዳንዱ የክርስቶስ አካል ብልት የተዋሐደ አቅርቦት እየጠነከረች እንድትሄድ።

በመንፈሳዊ ስጦታዎች እና በተሰጥዖ መካከል ያለውን ልዩነት ለማጠቃለል፡ 1) ተሰጥዖ የጀነቲክስ እና/ወይም የልምምድ ውጤት ሲሆን፣ መንፈሳዊ ስጦታ ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ውጤት ነው። 2) ተሰጥዖ በማንም ሰው ላይ ሊያድር ይችላል፣ በክርስቲያን ወይም ክርስቲያን ባልሆነ፣ መንፈሳዊ ስጦታ ግን የሚያድረው በክርስቲያኖች ላይ ብቻ ነው። 3) ሁለቱም፣ ተሰጥዖ እና መንፈሳዊ ስጦታ ጥቅም ላይ መዋል የሚኖርባቸው ለእግዚአብሔር ክብር እና ሌሎችን ለማገልገል መሆን አለበት፣ መንፈሳዊ ስጦታዎች በእነዚህ ተግባራት ላይ ሲያተኩሩ፣ ተሰጥዖ ደግሞ ባጠቃላይ መንፈሳዊ ላልሆኑ ዓላማዎች ሊሆን ይችላል።

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

በተሰጥዖ እና በጸጋ ስጦታ መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው?
© Copyright Got Questions Ministries