settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጭንቀት ምን ይላል? ክርስቲያን ጭንቀትን እንዴት ማሸነፍ ይችላል?

መልስ፤


ጭንቀት እየተስፋፋ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፤ አማኞችን እና አማኝ ያልሆኑትን በብዙ ሚሊዩኖችን እየጎዳ ነው፡፡ በጭንቀት የሚሰቃዩ የሚታዩባቸው ምልክቶች ሃዘን ቁጣ ተስፋ መቁረጥ ግራ መጋባት እና ሌሎች የተለያዩ ምልክቶች ይታዩባቸዋል፡፡ እንደማይጠቅሙ መሰማት ሊጀምራቸው እና ራስን ማጥፋት ሊፈልጉ አንድ ወቅት ይደሰቱባቸው የነበሩ ነገሮችንና ሰዎችን ፍላጎት ሊያጡ ይችላሉ፡፡ ጭንቀት ስራ በማጣት የሚወዱት ሰው በሞት ሲለይ በፍቺ ወይም በአምሮ ቀውስ ችገር እንደ እንደ ግራ መጋባት በዝቅተኝነት ስሜት ሊመጣ ይችላል፡፡

ሌላው መጽሐፍ ቅዱስ በደስታ እና በምስጋና እንድንሞላ ይነግረናል (ፊሊ 4፡4፤ ሮሜ 15፡11) እግዚአብሔር ለሁላችንም ደስተኛ ህይወት እንድንኖር እንዳቀደልን ያመለክታል፡፡ ወቅታዊ የሆነ ጭንቀት ውስጥ ላለ ይህ ቀላል አይደለም ግን እግዚአብሔር በጸሎት ውስጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በህይወት ተዛምዶ በአጋዥ ቡድኖች በአማኞች ህብረት በንስሃ እና ይቅርታ በምክር ሊድን ይችላል፡፡ በራሳችን እየተዋጥን እንዳይሆን ስለምናደርገው ጥረት እርግጠኞች መሆን አለብን፡፡ የጭንቀት ችገር ያለባቸው ትኩረታቸውን ከራሳቸውን ላይ በማንሳት ወደ ጌታ እና ወደ ሌሎች በመመልከት ሊወገድ ይችላል፡፡

የህክምና ጭንቀት በባለሞያ ሃኪሞች መታከም ያለበት አካላዊ ሁኔታ ነው፤ ባልተጠበቀ የህይወት ገጠመኝ የተከሰተ ላይሆን ይችላል ወይንም የበሽታው ምልክት በአንድ ሰው የግል ፈቃድ እየጨመረ የመጣ ላይሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ ክርስቲያን ማህበረሰብ ከሚያምኑት በተጻረረ ሁኔታ የህክምና ጭንቀት ሁል ጊዜ በኃጢያት ምክንያት የሚመጣ ላይሆን ይችላል፡፡ ጭንቀት አንዳንድ ጊዜ በመድሃኒት እና በአማካሪዎች አገልግሎት መታከም ከሚችል ከአካለዊ ቀውስ ሊመጣ ይችላል፡፡ እርግጥ ነው እግዚአብሔር የተኛውንም የተዛባ የጤና አክል መፈወስ ይችላል፡፡

በጭንቀት ወስጥ የሚሰቃዩ ጭንቀታቸውን ቀለል ሊያደርጉአቸው የሚችሉአቸው ነገሮች አሉ፡፡ እንርሱ አንደሚፈልጉት ባይሰማቸውም በቃሉ ላይ መቆየት አለባቸው፡፡ ስሜት ወደ ጥፋት ሊመራን ይችላል፤ የእግዚአብሔር ቃል ያለለወጥ አጽንቶ ያቆማል፡፡ በእግዚአብሔር ላይ ጠንካራ እምነትን መገንባት በፈተና እና በመከራ ወስጥ ስናልፍ ወደ አረሱ መጠጋት አለብን፡፡ እግዚአብሔር በህይወታችን ልንሸከመው ከምንችለው በላይ መከራ እንዲሆንብን እግዚአብሔር እንደማይፈቅድ ቃሉ ይነግረናል (1ቆሮ 10፡13)፡፡ ሆኖም መጨነቅ ኃጢያት አይደለም፤ አንድ ሰው በሚገጥመው ግጭት አስፈላጊውን ሞያዊ እርዳታን መውሰድን ጨምሮ ስለሚሰጠው ምላሽ ኃላፊነት መውሰድ አለበት፡፡ ‹‹እንግዲህ ዘወትር ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት፥ ማለት ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ፥ በእርሱ እናቅርብለት።›› ዕብ 13፡15

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጭንቀት ምን ይላል? ክርስቲያን ጭንቀትን እንዴት ማሸነፍ ይችላል? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries