settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ በአጋንንት ስለመያዝ/ አጋንንታዊ መያዝ ምን ይላል? በአሁን ዘመንም ይሆናልን? ከሆነስ፣ ምልክቶቹ ምንድናቸው?

መልስ፤


መጽሐፍ ቅዱስ በአጋንንት ስለተያዙ ወይም ተጽዕኖ ስላደረባቸው ሰዎች አንዳንድ ምሳሌዎች ይሰጣል። ከእነዚህ ምሳሌዎች አንዳንድ የአጋንንት ተጽዕኖ ምልክቶችን አግኝተን አጋንንት በአንዱ ላይ እንዴት እንደሚያድሩበት ጠልቀን ማየት እንችላለን። ቀጥሎ ያሉት አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦች ናቸው፡ ማቴዎስ 9:32-33፤ 12:22፤ 17:18፤ ማርቆስ 5:1-20፤ 7:26-30፤ ሉቃስ 4:33-36፤ ሉቃስ 22:3፤ ሐዋርያት ሥራ 16:16-18። በአንዳንዶቹ በእነዚህ ምንባቦች፣ የአጋንንት ማደር አካላዊ ሕመምን ይፈጥራል፣ እንደ ለመናገር አለመቻል፣ የሚጥል በሽታ ምልክት፣ ዕውርነት፣ ወዘተ። በሌሎቹ ደግሞ፣ ግለሰቦች ክፉ እንዲሠሩ ያደርጓቸዋል፣ ይሁዳ ዋነኛ ምሳሌ ይሆናል። በሐዋርያት ሥራ 16:16-18 መንፈሱ ለአገልጋይዋ ልጃገረድ አንዳንድ ነገሮችን እንድታውቅ ችሎታ ሰጥቷታል፣ ከምትረዳው በላይ። አጋንንት ያደረበት የጌርጌሴኖን ሰውዬ እጅግ በርካታ አጋንንት (ሌጌዎን) ያደረበት፣ ከሰብዓዊ ተፈጥሮ በላይ የሆነ ጥንካሬ ነበረው፣ ራቁቱንም በመቃብር ስፍራ ይኖር ነበር። ንጉሥ ሳኦል፣ በጌታ ላይ ካመጸ በኋላ፣ በክፉ መንፈስ ይቸገር ነበር (1 ሳሙኤል 16:14-15፤ 18:10-11፤ 19:9-10) በግልጽ በሚታይ የመጫጫን ስሜት እና ዳዊትን ለመግደል እየጨመረ በሚሄድ መሻት።

እንግዲህ፣ ሰፊና የተለያየ ታሳቢ በአጋንንት የመያዝ ምልክቶች ይኖራሉ፣ የአካል ዝለት እሱም እንደ አካላዊ ችግር የማይታይ፣ የስብእና መለወጥ፣ መጫጫን ወይም ጠበኝነት፣ ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ጥንካሬ፣ መልካም ያለመሆን፣ ማኅበራዊነትን የመጻረር ባሕርይ፣ እና መረጃ የመቀያየር ችሎታ፣ ማንም ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ ሊያውቅ የማይችለውን። መገንዘብ ጠቃሚ የሚሆነው ሁሉም ማለት በሚቻል መልኩ ካልሆነም ባብዛኛው እነዚህ ባሕርያት ሌላ ማብራሪያ ሊኖራቸው ይችላል፣ ስለዚህም እያንዳንዱን የተጫጫነውን ሰው ወይም የሚጥል በሽታ ያለበትን ግለሰብ አጋንንት ያደረበት ብሎ መፈረጅ አይገባም። በሌላ በኩል፣ ምዕራባዊ ባህል በሰዎች ሕይወት ውስጥ የሰይጣንን ጣልቃ ገብነት ከምር አይቀበለውም።

ከእነዚህ አካላዊ ወይም ስሜታዊ ልዩነቶች በተጨማሪ፣ መንፈሳዊ ሁኔታዎችንም መመልከት ያስፈልጋል፣ ሰይጣናዊ ተጽዕኖዎችን የሚያሳዩትን። እነዚህም የሚያካትቱት ይቅር ለማለት እምቢተኝነት (2 ቆሮንቶስ 2፡10-11) እና ሐሰተኛ ዶክትሪንን ማመንና ማሰራጨት፣ በተለይም ኢየሱስ ክርስቶስንና የንስሐ (የማስተሥረይ) ሥራውን በተመለከተ (2 ቆሮንቶስ 11:3-4፣ 13-15፤ 1 ጢሞቴዎስ 4:1-5፤ 1 ዮሐንስ 4:1-3)።

አጋንንት በክርስቲያኖች ሕይወት ስለሚኖራቸው ጣልቃ-ገብነት በተመለከተ፣ ሐዋርያው ጴጥሮስ አንድ መገለጫ ሐቅ ነው፣ ማለትም አማኝ የሰይጣን ተጽዕኖ ሊያርፍበት እንደሚችል (ማቴዎስ 16፡23)። አንዳንዶች ጠንከር ባለ ሰይጣናዊ ተጽዕኖ ሥር የሆኑ ክርስቲያኖችን ይጠቅሳሉ፣ “ዲያብሎሳዊ” እንደሆኑ፣ ነገር ግን በቅዱስ ቃሉ ፈጽሞ የተጠቀሰ አንድም ምሳሌ የለም፣ በክርስቶስ ያመነ ሆኖ በሰይጣን የተያዘ። አብዛኞቹ ሥነ-መለኮታውያን የሚያምኑት፣ ክርስቲያን ሊያዝ አይችልም፣ ምክንያቱም በውስጡ መንፈስ ቅዱስ ስለሚያድር (2 ቆሮንቶስ 1:22፤ 5:5፤ 1 ቆሮንቶስ 6:19)፣ የእግዚአብሔርም መንፈስ ከአጋንንት ጋር ማደሪያ ስለማይጋራ።

አንዱ እንዴት ራሱን ማደሪያ ለማድረግ ክፍት እንደሚሆን በትክክል አልተነገረንም። የይሁዳ ጉዳይ የሚወክል ከሆነ፣ ልቡን ለክፉው ክፍት አድርጓል— በሱው ጉዳይ በገዛ ስግብግብነቱ (ዮሐንስ 12፡6)። ስለዚህ ሊሆን የሚችለው አንዱ በተለምዷዊ ኃጢአት እንዲገዛ ልቡን ከከፈተ፣ አጋንንት እንዲገባ መጋበዙ ነው። ከሚሲዮናውያን ልምድ፣ በአጋንንት መያዝ የሚዛመደው ከአሕዛብ ጣዖታት አምልኮ ጋር ነው፣ እንዲሁም ከተፈጥሮ በላይ በሆኑ ነገሮች መያዝ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ጣዖት አምልኮን ከአጋንንት አምልኮ ጋር በተደጋጋሚ ያያይዘዋል (ሌዋውያን 17፡7፤ ዘዳግም 32፡17፤ መዝሙር 106፡37፤ 1 ቆሮንቶስ 10፡20)፣ ስለዚህ፣ በዝሙት ውስጥ መግባት ወደ አጋንንት አምልኮ ማምራቱ ሊያስገርም አይችልም።

ከላይ ባሉት የቅዱስ ቃሉ አንቀጾች ላይ እና በአንዳንድ ሚሲዮናውያን ልምድ በመመሥረት፣ አብዛኞቹ ሰዎች ሕይወታቸውን ለሰይጣን ጣልቃ ገብነት የሚከፍቱት አንዳንድ ኃጢአትን በመታቀፍ ነው ወይም በአጋንንት አምልኮ በመሳተፍ (አውቀውም ሆነ ሳያውቁ) ብሎ መደምደም ይቻላል። ምሳሌዎችም፣ አመንዝራነት፣ በአደንዛዥ-ዕፅ/ አልኮል መጠጥ መበለሻሸት፣ እሱም ሕሊናን የሚያስት፣ ዐመፀኝነት፣ መራርነት፣ እና መናፍስት ጠሪነትን ያካትታሉ።

በተጨማሪ ግምት ውስጥ የሚገባ ጉዳይ አለ። ሰይጣንና ክፉ ሠራዊቱ ምንም ነገር ሊያደርጉ አይችሉም ጌታ እንዳያደርጉ የማይፈቅደውን (ኢዮብ 1-2)። ጉዳዩ ይህ ሆኖ ሳለ፣ ሰይጣን፣ የገዛ ራሱን ዓላማ እንደሚፈጽም በማሰብ፣ የእግዚአብሔርን መልካም ዓላማ ይፈጽማል፣ ልክ እንደ ይሁዳ ክህደት። አንዳንድ ሰዎች ከተፈጥሮ በላይ በሆነና በአጋንንት ድርጊት ጤናማ ያልሆነ መደሰትን እያዳበሩ ይመጣሉ። ይህ ተገቢ ያልሆነና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ነው። እግዚአብሔርን ብንከተል፣ የእርሱን የጦር ዕቃ ብንለብስ እና በእርሱ ጥንካሬ ብንታመን (ኤፌሶን 6፡10-18)፣ ክፉውን የምንፈራበት ምንም ምክንያት አይኖርም፣ እግዚአብሔር ሁሉንም ይገዛልና!

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ በአጋንንት ስለመያዝ/ አጋንንታዊ መያዝ ምን ይላል? በአሁን ዘመንም ይሆናልን? ከሆነስ፣ ምልክቶቹ ምንድናቸው?
© Copyright Got Questions Ministries