በፍቅር ስለመያዝ / የትዳር ጓደኛን ስለመፈለግ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?


ጥያቄ፤ በፍቅር ስለመያዝ / የትዳር ጓደኛን ስለመፈለግ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መልስ፤
ምንም እንኳ “በትዳር መፈላለግ” እና “መፋቀር” በመጽሐፍ ቅዱስ ባይገኙም፣ አንዳንድ መርሖዎች ተሰጥተውናል፣ ክርስቲያኖች ከጋብቻ በፊት ባሉት ጊዜያት የሚራመዱባቸው። የመጀመሪያው ስለ ማፍቀር ከሆነው የዓለም አተያይ የግድ መለየት ይኖርብናል፣ ምክንያቱም የእግዚአብሔር መንገድ ከዓለም ጋር ስለሚቃረን (2 ጴጥሮስ 2፡20)። የዓለም አተያይ ሊሆን የሚችለው እኛ እንዳሻን እንድናፈቅር ነው፣ ጠቃሚው ነገር የሰውየውን ባሕርይ ማወቅ ነው፣ ማንኛውንም ውሳኔ ከማድረጋችን በፊት፣ ለእርሱ ወይም ለእርሷ። ግለሰቡ በክርስቶስ መንፈስ ዳግም መወለዱን ማወቅ አለብን (ዮሐንስ 3፡3-8) እንዲሁም እሱ ወይም እሷ ክርስቶስን ወደ መምሰል ተመሳሳይ የሆነ ፍላጎት የሚካፈሉ ከሆነ (ፊሊጵስዩስ 2፡5)። የማፍቀር ወይም የትዳር ጓደኛን የመፈለግ የመጨረሻ ግብ የሕይወት ሙሉ ጓደኛ መፈለግ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፣ እንደ ክርስቲያኖች፣ የማያምን ፈጽሞ እንዳናገባ (2 ቆሮንቶስ 6፡14-15) ምክንያቱም ይህ ከክርስቶስ ጋር ያለንን ግንኙነት ስለሚያዳክመው እና ሞራላችንንና አቋማችንን ስለሚያወርደው።

አንዱ ግንኙነት ሲፈጽም፣ የማፍቀርም ሆነ የትዳር ማግባቢያ፣ ማስታወስ ጠቃሚ የሚሆነው ጌታን ከሁሉም በላይ ማፍቀርን ነው (ማቴዎስ 10፡37)። ማለትም ሆነ ማመን፣ ሌላ ሰው “ሁሉንም ነው” ብሎ ወይም በአንዱ ሕይወት ውስጥ እጅግ ጠቃሚው ነገር እንደሆነ፣ አመንዝራነት ነው፣ እሱም ኃጢአት (ገላትያ 5፡20፤ ቆላስያስ 3፡5)። ደግሞም፣ ሰውነታችንን ማርከስ የለብንም፣ ቅድመ-ጋብቻ ወሲብ በማድረግ (1 ቆሮንቶስ 6፡9፣ 13፤ 2 ጢሞቴዎስ 2፡22)። ወሲባዊ ኢሞራላዊነት በእግዚአብሔር ላይ ብቻ የተደረገ ኃጢአት አይደለም ግን ደግሞ በገዛ ራሳችንም አካል ላይ ነው (1 ቆሮንቶስ 6፡18)። ሌሎችን ማፍቀርና ማክበር ያስፈልጋል፣ ራሳችንን እንደምንወድ (ሮሜ 12፡9-10)፣ ይህም በርግጥ እውነት ነው በትዳር ማግባቢያ ወይም በፍቅር ግንኙነት። ማፍቀርም ሆነ የፍቅር ማግባቢያ፣ እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ መርሖዎች ተከትሎ መጓዝ እጅግ የተሻለው መንገድ ነው የጋብቻን መሠረት ደኅንነት ለማስጠበቅ። ከሁሉም እጅግ የላቀው ውሳኔ ነው፣ እኛ የምናደርገው፣ ምክንያቱም ሁለት ሰዎች ሲጋቡ፣ እርስ በርስ ተጣምረው አንድ ሥጋ ስለሚሆኑ፣ እግዚአብሔር እንደሚፈልገው የጸናና የማይፈርስ በመሆኑ (ዘፍጥረት 2፡24፤ ማቴዎስ 19፡5)።

English
ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ
በፍቅር ስለመያዝ / የትዳር ጓደኛን ስለመፈለግ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

እንዴት ማድረግ እንደሚችሉ ይወቁ ...

ዘላለማዊነትን ከእግዚአብሔር ጋር ያሳዩከእግዚአብሔር ዘንድ ይቅርታን ተቀበሉ